Friday 5 December 2014

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ክፍል ሁለት





Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
Preaching Ministry



ክፍል ሁለት


ወበከመ ደክመ ከማሁ ነአምር ከመ ውእቱ አዕረፈ
ሥሩሐነ ወክቡዳነ ፆር 



    ትርጉም      እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም  የከበደባቸውን
                       እንዳሳረፈ እናውቃለን ይላል
   
            ሃይማኖተ አበው  ዘሄሬኔዎስ ምዕራፍ ቁጥር ፳፫


የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ  Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry



 በሚለው አገልግሎት ዙርያ ለአማኞችና ለአገልጋዮች የሚሆን ትምህርት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌል ሃሳብ እንድትመለስ የሚያስችሉ መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች በተለያዩ መጻሕፍቶችዋ ላይ ሠፍረው ስላሉ እነዛን እውነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በማገናኘትና በማመሳከር የተለያዩ ትምህርቶችን ማቅረባችን ይታወሳል አሁንም እንደሚከተለው እናቀርባለን ይህንን ትምህርት መከታተል ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ አገልግሎት የኔ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሁላችሁንም የሚመለከት አገልግሎት ስለሆነ የዚህ አገልግሎት ተባባሪና ደጋፊ በመሆን አገልግሎቱ ለብዙዎች እንዲደርስ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ማድረግ የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ


              

በዚህ በክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው ኢየሱስ እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም  የከበደባቸውን ያሳረፈ ብቻ ሳይሆን ዛሬ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናችን ስለሆነ ምህረትን የሚሰጠን በሚያስፈልገንም ጊዜ ጸጋን የሚለቅልን መሆኑን ከክፍሉ መጽሐፍ ሄደን እንመለከታለን ለዚህ ነው በግዕዙ ቃል ወብነ ሊቀ ካህናት ዐቢይ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ዘተለዐለ እምሰማያት ናጽንዕ እንከ አሚነ ቦቱ እስመ ኢኮነ ሊቀ ካህናቲነ ዘኢይክል ሐሚመ ለድካምነ ዳዕሙ ምኩር በኲሉ አምሳሊነ ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ  ያለን ስንተረጉመው እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም ያለን የኢየሱስን ሊቀካህናትነት እንደገናም ከኃጢአት በቀር እንደኛ የተፈተነ በመሆኑ በድካማችን ሊራራልን የሚችል መሆኑ የሚገባን እኛ የሰው ልጆች በድካም ውስጥ በፍርድና በጠላት ክስ ውስጥ በገባን ጊዜ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚያወጣንና የሚያስጥለንም ባጣን ጊዜ ነው አለበለዚያ ይሄ ሁኔታ ለእኛ ግልጽ አይሆንም ሊገባንም አይችልም ለዚህ ነው የሰዎች ነፍስ አባት ይዘን ከነፍስ አባቶቻችን ሥርዓትና የግዝት ማስፈራራት መላቀቅ የሚያቅተን ታድያ እነዚህ ነፍስ አባቶቻችን እኔ ነፍስ አባት  ስለሆንኩ ኃጢአትሕን ለእኔ ባለመናዘዝሕ ምክንያት ሥርዓት አፍርሰሃል ሃይማኖትን ጥሰሃል ኑፋቄም ውስጥ ገብተህ መናፍቅ ሆነሃል ስለዚህ ወደ እኔ ወደ ነፍስ አባትሕ ተመልሰህ የነፍስ ልጄ ካልሆንክ ኃጢአትሕንም ለእኔ ተናዘህ እግዚአብሔር ይፍታህ ካልተባልክ የተፈታህ አትሆንም እንደገናም ነፍስ አባትሕና ካህንህ ስለሆንኩ የጥምጣሜን መግዣና ያስለመድከኝ የዓመት የአባትነት ስጦታዬን ካላደረክልኝ ምኑን ነፍስ ልጄ ሆንሕ እያሉ በግዝታቸው ከሚያስፈራሩንና ከሚያውኩን ጸንተን ሃይማኖታችንን የምንጠብቅበት በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናት ስላለን ይህንን ሊቀካህናችን የሆነውን ኢየሱስን ቢያሳዩን ለኃጢአታችን ኑዛዜ የምንሰጠው ምንም ነገር ሳያሻን መገዘትና መወገዝ መነቀፍም ሳያስፈልገን በዚሁ ባየነው በሰማያት ባለፈልን ትልቁ ሊቀካህናችን ጸንተን ሃይማኖታችንን መጠበቅ ይሆንልናል ይኸው በሰማያት ያለፈው ሊቀካህናችን  የእምነታችን ራስና ፈጻሚ የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀካህናት  ነው ከእርሱ ውጪ ሃይማኖት የለም ይህንኑ ሃሳብ በይበልጥ ለመረዳት የክፍሉን ሃሳብ ሄደን እንድንመለከት እጋብዛለሁ በመጀመርያ ኢየሱስ የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የተባለበትን ክፍል እንመልከት በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ወይእዜኒ አኀዊነ ቅዱሳን ወጽዉዓን እምሰማይ በጽዋዔ ርእይዎ ለዝንቱ ሐዋርያክሙ ሊቀካህናት ዘኪያሁ ትትአመኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ የሚል ነው ዕብራውያን በመሆኑም በዚሁ የጌታችን የማዳኑ ሥራ አማካኝነት ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች መሆናችንን ካመንን ልንመለከት የሚገባው ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች እንድንሆን ያበቃንን የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀካህናት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው እንደገናም በዕብራውያን ፲፪ እና ላይ በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ወበእንተ ዝንቱ ንሕነኒ እለ ብነ እሙንቱ ሰማዕት ኩሎሙ ዘየዐውዱነ ከመ ደመና ንግድፍ እምላዕሌነ ኲሎ ክበደ ወሁከተ ኃጢአት ወንሩጽ በትዕግሥት ኀበ ዘጽኑሕ ለነ ተስፋነ ዘሃይማኖት  ወንትልዎ ለፍጹም መልአክነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተዐገሠ ኀፍረተ መስቀል አናኅሲዮ በእንተ ፍሥሓሁ ዘጽኑሕ ሎቱ ወመነነ ለኀፍረት ወነበረ በየማነ መንበረ እግዚአብሔር ትርጉም እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና የሚል ነው ስለዚህ ኢየሱስ በድካማችን የሚራራልን ኃጢአታችንንም ይቅር የሚለን በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናችን ከመሆኑም ባሻገር የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀካህን የሃይማኖታችን ራስና ፈጻሚም ነው ከእርሱ ውጪ የእምነት ሐዋርያ የለም ከእርሱም ውጪ ሊቀካህናት የለም ክርስቶስ የሌለው ሃይማኖት የለውምና ከእርሱ ውጪ ራስ ከእርሱም ውጪ የሃይማኖት ፈጻሚ የለም ይህ ማለት ክርስቶስ ኢየሱስ ብቸኛ የእምነት ሐዋርያ ብቸኛ ሊቀካህን እና ብቸኛው የሃይማኖት ራስና ፈጻሚ ነው ክርስቶስ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀካህናት በመሆኑ ዮሐንስ በመልዕክቱ ከዚህ የተነሳ  ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤  በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት ሲል ነገረን ፪ኛ ዮሐንስ ስለዚህ በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ በድካም ሊራራ ኃጢአትንም ይቅር ሊል በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናት እንዳለ ከሚጠቁሙን ውጪ ኃጢአትን አናዞና ይህን ያህል ስገድ ብሎ እግዚአብሔር ይፍታህ የሚል ካህን መኖሩን ግን አያስተምረንም አይነግረንም እንደውም ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ በማለት የኃጢአትን ሸክም ከላያችን ላይ ሊጥልልን እና ሊያሳርፈን የሚጠራን ጌታ እያለ ለዚሁ ለኃጢአታችን ዕረፍት እኛ ወዳዘጋጀናቸው ነፍስ አባቶች መሄዱና መናዘዙ መፈታትም ሳይኖር እግዚአብሔር ይፍታህ መባሉም ሙሉ ለሙሉ ሊፈታን የሞተልን ሞትንም አሸንፎ የተነሣልን ጌታ አለንና ፍጹም ሥህተት ነው ከኃጢአቱ መፈታት የሚፈልግ ሰው ከኃጢአቱ ለመፈታት የሰዎችን ነፍስ አባት ከሚፈልግ ይልቅ  ሙሉ በሙሉ ሊፈታው ወደሚችል ጌታ መጥቶ ለዚህ ታማኝ ጌታ ሕይወቱን ቢሰጥ እርሱ ይፈታዋል ኢየሱስ ነፍስ አባትና ፈቺ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ይፍታ የሚለውን እንደገናም ነፍስ ልጅ ነኝና ታስሬአለሁ ስለዚህ ለነፍስ አባቴ መናዘዝ እግዚአብሔር ይፍታህም መባል ያስፈልገኛል የሚለውን  ሁሉ ሊፈታ የታመነ ነው ለዚህ ነው እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ሲል ሁላችንንም እንደ አመጣጣችን ሊፈታንና ሊያሳርፈን ጥሪ ያቀረበው የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፩ ፳፰ _ የተጻፈውን ተመልከቱ ደራሲውም የነፍስ ልጅ ወይም የነፍስ አባት የመሆንን ነገር ወደ ጎን ተወት በማድረግ በመልክአ ኢየሱስ ሰላም ለመላትሂከ በሚለው የጸሎት ድርሰቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ አበ ነፍስየ አንተ በሎሙ ለመላዕክት ትፈስሑ ሊተ ረከብክዎ ለወልድየ በከንቱ ዘሞተ አለ ትርጉም ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ የነፍስ አባቴ ነህ በከንቱ የሞተውን ልጄን አግኝቼዋለሁና ደስ ይበላሁ በማለት ኢየሱስ እውነተኛ ነፍስ አባታችን መሆኑን ነገረን ካህናቱም በቅዳሴው ማጠቃለያቸው ሠርዎተ ሕዝብ ሲያደርጉ ማለት ሕዝብን ሲያሰናብቱ ይፍታህ ይህድግ ያንጽሕ ወይቀድስ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ካህን ሊቀ ካህናት ሠራዬ ኃጢአተ ዓለም ወደምሳሴ አበሳ ይስረይ ለክሙ ኃጢአተ ዘገበርክሙ እምንእስክሙ እያሉ ጸለዩ ስንትረጉመው ኢየሱስ ክርስቶስ የካህናት አለቃ ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ይቅር ባይ ለአባቶቻችን ለሐዋርያት ሥልጣንን የሰጣቸው ይፍታን ያንጻን ይቀድሰን አበሳችንንም ይደምስሥልን ኃጢአታችንንም ይቅር ይበለን ማለታቸውን የሚያመለክት ነው እንዲህ እያሉ እየጸለዩ ግን ኃጢአትን ለማናዘዝ መነሳትና እግዚአብሔር ይፍታህ ለማለትም መበረታታት ራስን ማታለል ነው በቅዳሴው ፍጻሜ ሰዎችን በማሰናበት ውስጥ ያለው ኢየሱስ ሰዎችን ከፈታ አበሳን ከደመሰሰ ይቅር ካለ ካነጻና ኃጢአትን ካስተሰረየ የቀዳስያን ካህናት ምዕመኑን ኃጢአት ማናዘዝ ይቅር ማለት መቀደስና ማንጻት ለምንም የሚሆን ነገር አይደለም  እያልን ነው ይህንን ትምህርት አሁንም ያላጠቃለልኩት በመሆኑ በክፍል ሶስት ትምህርቴ ላይ እቀጥለዋለሁ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮም ላስፈጸመኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን



ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment