Friday 5 December 2014

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል ሁለት



የቤተክርስቲያን ተልዕኮ

ምዕራፍ ሁለት

ክፍል ሁለት



ከሐሰተኛ ነቢያት ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ራስንና መንጋውን መጠበቅ



የሐሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎች መነሻ ሃሳብ







የአንድ ትንቢት እውነተኛነት የሚታወቀው ትንቢቱ እንደተነገረው ሲፈጸም ነው ዘዳግም 18 21 _ 22 ሆኖም በልዩ ችሎታ መጪውን ዘመን ከወዲሁ ከሚተነብዩ በአጋጣሚ ከሚፈጸም የሐሰተኛ ነቢያት ትንቢት እንድንጠበቅ ክፍሉ ያሳስበናል በዘዳግም 13 ፥ 1 _ 5 ላይ በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ አምላክህ እግዚአብሔር ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ፥ ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ ተናግሮአልና ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ አርቅ ይላል  ሐሰተኛ ነቢያትም ሆነ አስተማሪዎች የተመሠረቱበት ትክክለኛና መነሻ  የእግዚአብሔር ሃሳብ ስለሌላቸው እውነተኛ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል የላቸውም ስለዚህ ሁልጊዜ ለተሳሳተው አሠራራቸው እንደመነሻ አድርገው የሚጠቀሙት በአገልግሎታቸውም ሆነ በትንቢታቸው በአጋጣሚ የተፈጸሙትን ጥቂት እውነቶች ይዘው ራስ ወዳድ በመሆናቸው በሁሉም ነገር ከማንም ይልቅ ለራሳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸውና እንደገናም በሁሉም ነገር ራሳቸውን ከሌሎች የተሻሉ አድርገው የሚቆጥሩ በመሆናቸው ራሳቸውን ቆልለው ጋራም አሳክለው በመቅረብ ከሌላው ይልቅ እነርሱ ጋር የተሻለ ነገር እንዳለ ሰዎች ሁሉ ወደ እነርሱ ቢመጡ ትክክለኛ መፍትሔ እንደሚያገኙ  ከማንም ይልቅ በዘመኑ የተቀቡ ሰዎች እግዚአብሔርም ለይቶ ለተለየ ክብር ያስነሳቸው እነርሱ ብቻ እንደሆኑ በመናገር ይህንንም ነገራቸውን ለሰዎች ሁሉ የሚናገሩላቸውን አዋጅ ክተት ብለውም የሚያውጁላቸውን  በየከተማው በየመንደሩ  ትልቅነታቸውን በመግለጥ ፖስተር ሳይቀር የሚለጥፉላቸውን ሰዎች በማዘጋጀት ማንነታቸውን ለሕዝብ ይበልጥ ለመግለጥ የሚጥሩና የሚታገሉ ሰዎች ናቸው ባላቸው ነገር ሳይሆን በሌላቸው ነገር ላይ ሳይቀር መንጠራራትን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል  በእነርሱ ውስጥ እኔ እሻላለሁ እኔ እበልጣለሁ የሚል ቃላት እንጂ ወንድሜ ከእኔ ይልቅ ይሻላል እስቲ እርሱን ላስቀድም የሚባል ነገር የለም መጽሐፉ የሚለው ግን ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው የሚለን ፊልጵስዩስ 2 3 _ 11 ለወንጌል ሥራ ሲባል ፖስተር መለጠፉ የጌታንም ሥራ በጀማ ክሩሴድና በአደባባይ መስራቱ አስፈላጊ ቢሆንም የራስን ጥቅም ለማግኘትና ከንቱ ውዳሴን በመፈለግ ታዋቂ ለመሆን የተሻልኩም እኔ ብቻ ነኝ ለማለት የሚደረገውን እውቅናን የማግኘት ሩጫን ግን እግዚአብሔር ፈጽሞ ይቃወመዋልና አይሆንም ይህ ደግሞ የሐሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎች መገለጫ ምልክታቸው ነው በዘመኑ ጊዜውን ጠብቆ በመገለጡ ምክንያት በአይሁድ በሮማ ወታደሮችና ቄሳሮች በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ካህናትና ሌዋውያን እንደ ትልቅ ትንግርት እውቅናን አግኝቶ የተገለጠው ዮሐንስ ኢየሱስን በእርሱነቱ ሊሸፍነው ሊደብቀውም አልወደደም አይሁድም አንተ ማን ነህ ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው ይለንና መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ በማለት ምስክርነቱ እውነተኛ እና ክህደት የሌለበት መሆኑን ገለጸልን አያይዞም እንኪያስ ማን ነህ ? ኤልያስ ነህን ?  ብለው ጠየቁት አይደለሁም አለ ነቢዩ ነህን ? አይደለሁም ብሎ መለሰ እንኪያስ ማን ነህ ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራሥህ ምን ትላለህ ? አሉት እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ ይለናል ዮሐንስ ወንጌል 1 19 _ 23 ይህንን ሃሳብ ወደ ዘመናችን አምጥተነው ብንመለከተው ዛሬ አንተ ማንነህ ? ተብለን በሥርዓት ተጠይቀን ሳይሆን ስለማንነታችን የምንናገረው እግዚአብሔር ይቅር ይበለንና ሳንጠየቅ ማንም ምንም ሳይለን ብዙዎቻችን እንዲህና እንዲያ ነን ብለን የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን ገናም ምንም ያልያዝነውንና ያልደረስንበትን ነገር ሁሉ የምንናገር ነን ታድያ ይህ ዘመናችንን ከዮሐንስ ዘመን ጋር ስናስተያየው ምን ያህል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ከምንሰጣቸው ራስ ወዳድ መልሶቻችን ማወቅና መገመት እንችላለን ዮሐንስ ግን እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ እውነተኛ ምስክርነቱን ቢሰጥም እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብሎ ራሱን ከማንም ጋር ሳያነጻጽር በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ እኔ ነኝ አለ ዛሬ በዘመናችን አንዳንዱ ራሱን ከፍ የሚያደርገውም የሚያሳንሰውም የሆነ ነገር ፈልጎ ነው ዮሐንስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር የለም ክርስቶስ አይደለሁም ኤልያስም አይደለሁም አለ ነገር ግን በምድረበዳ የሚጮህ የሰው ድምጽ ነኝ አለ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁንለት ለዮሐንስ የጠቀመው ክርስቶስ መሆንም አይደለም ኤልያስም መሆን አይደለም ለዮሐንስ የጠቀመው በምድረበዳ የሚጮህ የሰው ድምጽ መሆን ነው ወገኖቼ ለዮሐንስ ብቻ ሳይሆን ለእኛም የሚጠቅመን ይኼው ነው እኛ ግን ከማን አንሼ በሚል ሰበብ ወይም ከአንዱ ባንስ ከሌላው አላንስም በሚል ሥጋዊ የፉክክር ጉልበት ተይዘን በተፎካካሪነት መንፈስ ጎን በመቆም ያለ የሌለውን ስም ተሸክመን እንዲሁ ያለ ሥራ በከተማው ስንንቀዋለል ከተማውንም ስናካልል እንገኛለን የተጠቀምነው ነገር በጥቂቱ ቢኖርም እንኳ ከከንቱ ውዳሴ በስተቀር ሌሎችን የጠቀምንበት ነገር በፍጹም የለም እግዚአብሔር ከዚህ ከንቱ ከሆነ ውዳሴ እና የታይታ ጉዞ አውጥቶ ለትክክለኛው የክብሩ መገለጫ ይጠቀምብን የሐሰት ነቢያትና አስተማሪዎች ችግር እንግዲህ ይሄ ነው ተፎካካሪዎች ናቸው ያለ የሌለ ስም ያለው እነርሱ ነው በወሬያቸውና በከንቱ ውዳሴያቸው ከተማውን ሞልተውታል ነገር ግን ከልማታቸው ይልቅ ጥፋታቸው የጎላ ነው ሐናንያ የተባለው የሐሰት ነቢይ ኤርምያስን በመፎካከር  የኤርምያስን እውነተኛ አገልግሎትና መልዕክት በመቃወሙ የተጠቀመው ነገር አልነበረም  ይልቁንም ተቃውሞው ለሞት ሲዳርገው እንመለከታለን ለዚህም ነው ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ ሐናንያ ሆይ፥ ስማ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ አለው ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ የሚለን ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 28 በሙሉ እናንብብ ዛሬም ሐሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎች በጊዜ መመለስ ካልሆነላቸው የመጨረሻ ዕጣ ፈንታቸው የሐናንያ ዕጣ ፈንታ ነው እግዚአብሔር ምሕረቱ የበዛ ቢሆንም ለሃሳቡና ለመንግሥቱ ሥራ የጨከነ በመሆኑ በንስሐ መመለስ ከሌለ ይህንኑ ከማድረግ አይመለስም ወደኋላም አይልም በዘዳግም 13 1 _ 5 በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረትም በአጋጣሚ የተፈጸመውን መልካም ነገር ወይንም በመልካሙ ዘመናቸውና ባልተበላሸው ማንነታቸው የሠሩትን ጥቃቅን ነገራቸውን ዛሬ ላይ ላለው ጥፋታቸው መረጃና ሽፋን በማድረግ ሰዎችን ወደ ተሳሳተ ነገር የሚወስዱ ናቸው ለዚህ ነው ይኸው የዘዳግም መጽሐፍ በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ አምላክህ እግዚአብሔር ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ፥ ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ ተናግሮአልና ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ አርቅ የሚለን ስለዚህ ዛሬም መስማት የሌለብንን ቃል መስማት የለብንም በዚህ ላይ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት   የተነሣ የጸና አቋም ሊኖረን ይገባል እንደገናም እግዚአብሔርን ልንከተል እርሱን ልንፈራ ትዕዛዙንም ልንጠብቅ ቃሉን ልንሰማ እርሱን ልናመልክና  ከእርሱም ጋር ልንጣበቅ ይገባል በ1ኛ ቆሮንቶስ 5 13 ላይ በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት ስላለን  ክፉውን ነገር ከመካከላችን ማውጣትና ማራቅም አለብን ይህ በሚሆንበት ጊዜ በሐዋርያት ሥራ 9 31 መሠረት በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር ይለናልና ለእኛም እንደግለሰብ ብቻ ሳይሆን እነደ ቤተክርስቲያን በሰላም መኖር መታነጽ በእግዚአብሔር ፍርሃትና በመንፈስቅዱስ መጽናናት እየበዙ መሄድ ይሆንልናል  ትምህርቱ የሚቀጥል ስለሆነ ለማንበብ እንዳይበዛ በዚሁ እጠቀልላለሁ ተባረኩልኝ


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment