Sunday 7 December 2014

ምሥጋና ! ምሥጋና !

 






የሚያመሰግን ሰው ሁልጊዜ በጸሎት 
የድል ሰው ይሆናል ደግሞም የነፃነት 
ከማጉረምረም ይልቅ ምሥጋና ይበልጣል
አንደበት ዝማሬን ዕልልታን ይሞላል 
ማጉረምረም ለምኔ ማለት ሲገባቸው 
እሥራኤል በሙሉ በድንኳኖቻቸው 
በማመስገን ፈንታ እሮሮን ተሞሉ 
ማመን ተስኗቸው በተጻፈው ቃሉ 
ዛሬስ የእኛ ድንኳን ጓዳችን ምን ይላል ?
ምስጋናን ተሞልቷል ? ወይስ ጌታን ያማል ?
አልታይ ብሎአቸው የእግዚአብሔር ሥራ 
ንቀት በልባቸው ገብቶ በየተራ 
ከእግዚአብሔር ይልቅ ጥጃ አማራቸው
ቀልጦ ለተሠራ ምስል መስገድ ሽተው
አሮንም ተስማማ ከእስራኤል ጋራ
አምልኮ ሊሰዋ ቀልጦ ለተሠራ 
የእግዚአብሔር በዓል ነው ብሎ ተናገረ
ለእስራኤል አወጀ አንድም አላስቀረ
በሃሳቡ ፍጹም የማይለወጠው 
ጌታ እግዚአብሔር በላይ የሚኖረው
ይህን ሕዝብ አየሁት አንገተ ደንዳና 
ለእውነት ያልታዘዘ ልቡን ያላቀና
ብሎ ተናገረ ቁጣው ተቃጥሎበት 
ለባርያው ለሙሴ ለተማመነበት
እግዚአብሔር አምላክ ከላይ ከጸባኦት

No comments:

Post a Comment