Friday 5 December 2014

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል ሰባት



የቤተክርስቲያን ተልዕኮ


ምዕራፍ ሁለት



ክፍል ሰባት



ከሐሰተኛ ነቢያት ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ራስንና መንጋውን መጠበቅ


የመጽሐፉ አለመዘጋት እና ውጤቱ

እርሱም እንዲህ አለኝ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ
ትንቢተ ዳንኤል 12 ፥ 9 _ 11



በዚህ የክፍል ሰባት ትምህርታችን ላይ መጽሐፉ ያልተዘጋ መሆኑን የሚያሳዩ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች አውጥተን በየተራ እንመለከታቸዋለንና ተከታተሉ በትንቢተ ዳንኤል 12 4 ላይ ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል ይለናል እንደገናም በትንቢተ ዳንኤል 12 9 _ 11 ላይ እርሱም እንዲህ አለኝ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ ይላል አሁንም  በትንቢተ ዳንኤል 12 13 ላይ ደግሞ አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ የሚል ቃል እናገኛለን ስለዚህ እስከ ፍጻሜ ድረስ መሄድ የሚችሉ ያልተዘጋውን የመጽሐፉን ሃሳብ ያገኙ አግኝተውም የበሉና ያላመጡ ከሕይወታቸውም ጋር በማገናኘት የሕይወታቸው መመርያ ያደረጉ ሰዎች በመሆናቸው ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው በማለት መዝሙረኛው ተናገረ ስለዚህ ለእነዚህ ሰዎች እና ይህንንም እውነት ለተቀበልን ለሁላችን ሕጉ ለእግራችን መብራት ለመንገዳችንም ብርሃን ነው መዝሙር 119 105 ከዚህም ሌላ  የእግዚአብሔር ሕግ ለሁላችን ተድላችንና ደስታችን  ትዝታችን ብዙ የሆነም ሰላማችን ነው መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር 119 70 77 92 97 165 ላይ ልባቸው እንደ ወተት ረጋ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ  ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥ ቀድሞ በጐስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ፦ ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም የሚሉ ሃሳቦች ሰፍረው እናገኛለን የእግዚአብሔር ሕግ በልባችን ውስጥ ሲሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ይረዳናል ሕጉን ስንተው ግን ከኃጢአተኞች የተነሳ ሃዘን ይይዘናል በመሆኑም በመዝሙር 40 8 በመዝሙር 119 53 ላይ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ስለዚህ መጽሐፉ ያልተዘጋና እስከ ፍጻሜ ድረስ የታተመ በመሆኑ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ በማለት በሕጉ ቃል ልንጸና ይገባል እንጂ በሕይወታችን ሐዘን እንዲመጣብን ሕጉንም ልንተው አይገባንም መዝሙር 119 34 ዳንኤል በትንቢቱ እንደተናገረው የመጽሐፉ ቃል ያልተዘጋ በመሆኑ ክፋት ለምኔ ብለው አለማስተዋልንም አስወግደው ወደዚሁ ቃል ለተጠጉ ሰዎች ለብዙዎች ተድላና ደስታ ብዙ የሆነም ሰላም ከመስጠቱ ባሻገር ሕይወትን የሚያጠራ የሚያነጣ እና የሚያነጥርም ነው በመዝሙር 11 (12) 6 ላይ በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ  ናቸው ስለሚል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚህ ጉዳይ ላይ እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ አለ ዮሐንስ ወንጌል 15 3  እንደገናም በዮሐንስ ወንጌል 17 17 ላይ በእውነት ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው የሚል ቃል እናገኛለን በመሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ለዘለዓለም የሚኖርና በዘመናት መካከልም የማይለወጥ በመሆኑ ሕይወታቸውን ለዚህ ቃል ያስገዙትንና አሳልፈው የሰጡትንም ሁሉ ሲለውጣቸውና ሲያነጻቸው ሲቀድሳቸውም እንመለከታለን ሐዋርያትም ያመኑትን ሰዎች ለጸጋው ቃል የሰጡት ከዚህ የተነሳ ነው ለዚህም ነው  በሐዋርያት ሥራ 4 32 ላይ አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ ሲሉ የተናገሩት ይህ መጽሐፍ አሁንም ያልተዘጋ መሆኑን በራዕይ 22 10 _  13 ላይ ለእኔም ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ታድያ ዓመፀኛው ወደ ፊት ቢያምጽም ርኩሱም ወደፊት ቢረክስም የዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቃል ግን አልተዘጋም አልፋና ኦሜጋ የሆነው እግዚአብሔርም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የሚከፍለው በቃሉ ነውና በመሆኑም በትንቢተ ኢሳይያስ 29 10 _ 12 ላይ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል ራእዩም ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል ማንበብንም ለሚያውቅ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል ይለናል በሰቆቃወ ኤርምያስ 2 9 ላይ ጤት በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ ሰበረም ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ ነቢያቶችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም ይለናል በትንቢተ ሕዝቅኤል 7 26 እና 27 ላይ ደግሞ ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ይላልና የነዚህ ነቢያት መጨፈን የባለ ራዕዮች መሸፈን እንደገናም ከካህኑ ዘንድ ትምህርት ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር መጥፋቱ የንጉሥ ልቅሶ የአለቃም ውርደትን መልበስ እና የመሳሰሉት የራሳቸው የነቢያቱና የባለ ራዮቹ እንዲሁም የካህናቱ ችግር እንጂ የመጽሐፉ ችግር እንዳልሆነ ከሰፈረው ሃሳብ መረዳት እንችላለን ነቢያቱና ባለራዕዮቹ ካህናቱም ጭምር ቃሉን ለማገልገልና ለጸሎት የተጉ ቢሆኑ ያልተዘጋውንም መጽሐፍ ልባቸውን ከፍተው ቢያነቡና ቢያጠኑ ቢማሩትም መጽሐፉ ዓይንን የሚከፍትና ትክክለኛውንም ራዕይ የሚሰጥ ነውና የዓይን መጨፈን  የራዕይ መሸፈን የትምህርትም መታጣት ለነዚህ ካህናት ነቢያትና ባለ ራዕዮች ባላጋጠማቸውም ነበር ስለዚህ ጉድለቱ የእነርሱ እንጂ የመጽሐፉ አይደለም ደግሞም እነርሱ አንብበው ያልፈቱትን ያልተረዱትንም መጽሐፍ ለሌሎች ሰጥተው ፍቱ አንብቡ ተረዱ ቢሊ አይሆንም መጽሐፉ ለሁላችንም ስለሆነ ሁላችንም አንብበን እንድንረዳው ተደርጎ በመንፈስቅዱስ አማካኝነት የተጻፈልን መጽሐፍ ነው ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ይሁን መጽሐፍቅዱስ በ2ኛ ጴጥሮስ 3 16 _ 18 ላይ በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን ስለሚል ይህንኑ የጸጋ ቃል አንብቦ ያወቀና ያደገ ሰው በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስቦ ከራሱ ጽናት እንዳይወድቅ የተጠነቀቀ ነው በመሆኑም ለዚህ መጽሐፍ ማንነታችንን የሰጠን ሁላችን ይህ መጽሐፍ ከማንም ይልቅ በሕይወታችን ዕድገትን እንዲሁም ለውጥን ያመጣል ባደገ ሰው መካከል ደግሞ የዓይ መጨፈን የራዕይ መሸፈን የትምህርትም መጥፋትና የምክር መታጣት የለም ከዚህም ሌላ መጻሕፍት አይጣመሙም የሐሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎች የዓመጽ ሥህተትና ጥፋትም አይገኝም ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር በዚሁ ቃል ወደ ሙላቱ እንዲያደርሰን በጸጋውና በእውቀቱም ቃል ዕድገት እንዲባርከን ምኞቴም ጸሎቴም ነው ተባረኩልኝ አሜን


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment