Friday 5 December 2014

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ክፍል ሦስት



ክፍል ሦስት


የተወደዳችሁ ወገኖች አሁንም ያለነው Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
Preaching Ministry
በሚለው አገልግሎት ዙርያ ለአማኞችና ለአገልጋዮች የሚሆን ትምህርት ለማቅረብ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌል ሃሳብ እንድትመለስ የሚያስችሉ መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች በተለያዩ መጻሕፍቶችዋ ላይ ሠፍረው ስላሉ እነዛን እውነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በማገናኘትና በማመሳከር የተለያዩ ትምህርቶችን በመንደፍ በማዘጋጀትና በማቅረብ ውስጥ ነው ስለሆነም በዚህ የክፍል ሦስት ትምህርታችን ላይ እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም  የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን በማለት የሃይማኖተ አበው መጽሐፍ በገለጸልን መሠረት የደከመና ድካምንም የሚያውቅ በመሆኑ ለሌሎችም ሆነ ዛሬ ላይ ላለን ለእኛ የሚራራልን የማይፈርድብንም ታማኝ ሊቀካህን መሆኑን ከመጽሐፍቅዱሳችን በስፋት እንመለከታለን በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይ ነቢዩ ኢሳይያስ ሃሳቡን በትኩረት እንድንመለከተው እንዲህ ይለናል የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም አለን ትንቢተ ኢሳይያስ 53 3 በመሆኑም ለእኛ ለሰው ልጆች ይህ ጌታ የተጠላ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ስለሆነ በሥጋው ወራት በነበረው የምልልስና የማስተማር ዘመኑ ለብዙዎች ራርቷል ብዙዎችንም ኃጢአታቸውን ይቅር ብሏል ፈውሶአቸዋል ከእስራቶቻቸውም ፈቶአቸዋል ዛሬም ይሄ ሊቀካህናችን በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናት ሆኖ ለዘላለም የሚኖር የማይለወጥ ክህነት አለውና ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ስለሚኖር ሊራራልን ይቅር ሊለንና ሊፈውሰን የታመነ ሊቀካህን ነው በሥጋው ወራት በነበረው አገልግሎት የራራና የማረ ያልፈረደ መሆኑን ከተጻፉልን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ሄደን መመልከት እንችላለን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 7 11 _ 17 ላይ ኢየሱስ ልጇ ለሞተባት ለዚች መበለት ያዘነላትና አታልቅሺ ያላት ቀርቦም ቃሬዛውን በመንካት አንተ ጐበዝ እልሃለሁ ተነሣ በማለት የሞተውም ቀና ብሎ እንዲቀመጥና እንዲናገር በማድረግ ለእናቱ መልሶ እንደሰጣት መጽሐፉ ይናገራል ኢየሱስ በሃዘን ውስጥ ያለፈ በመሆኑ እንዲህ በሃዘን ውስጥ ላሉ መበለቶች ያዝናል ሙታናቸውንም ያነሳል እንባዎቻቸውንም ከዓይኖቻቸው ላይ ያብሳል ይህ ነው እንግዲህ ሊቀካህንነት እንደገናም በዚሁ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 7 36 _ 50 ላይ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት ውስጥ ኃጢአተኛ የተባለችዋ ሴት በኢየሱስ እግር ላይ በመውደቅ የኢየሱስን እግር በእንባዋ አራሰች በጸጉርዋም አበሰች በዚህን ጊዜ ስምዖን አይቶ እንዲህ ሲል ፈረደባት ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ ይለናል ወገኖቼ ኃጢአተኛ ናት ብሎ በልብ ከማሰብ አንድ ፊቱን ተናግሮ ማረፍ ይሻላል ትልቁ ኃጢአት ኃጢአተኛ ናት ብሎ በልብ ማሰብ ነውና ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን ይህቺን ሴት ታያታለህን ?  በማለት እኔ ወደ ቤትህ  ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል በእንተ ዝንቱ እብለከ ተኀድገ ላቲ ኃጢአታ ብዙኅ እስመ ብዙኀ አፍቀረተኒ ወዘሰ ውኁደ አፍቀረኒ ውኁድ ኃጢአቱ ይትኀደግ ሎቱ ወይቤላ ለይእቲ ብእሲት ተኀድገ ለኪ ኀጢአትኪ ወአኀዙ እለ ይረፍቁ ይበሉ በበይናቲሆሙ መኑ ውእቱ ዝንቱ ዘየኀድግ ኀጢአተ ወይቤላ ለይእቲ ብእሲት ሃይማኖትኪ አድኀነተኪ እትዊ በሰላም ወደ አማርኛ ስንተረጉመው እንዲህ የሚል ነው  ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል እርስዋንም ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል አላት ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው ? ይሉ ጀመር ሴቲቱንም እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት ይለናል ወገኖቼ የራሱን ነገር እንኳ በቅጡ ያላወቀው ስምዖን ዘሎ እዚች ምስኪን ሴት ሕይወት ውስጥ በመግባት በልቡ ኃጢአተኛ ናት ቢላትም ኢየሱስ ግን እንደ ስምዖን አልፈረደባትም ይልቁንም ከስምዖን ይልቅ የተሻለ ነገር በማድረግ ብዙ የሆነ መሻትዋን በፊቱ በማቅረቧ ይኸው ስምዖን ከእርስዋ ጋር ያለውን ሕይወት በንጽጽር ከራሱ ሕይወት ጋር እንዲመለከት ካደረገው በኋላ ብዙ ሽታለችና ብዙ ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል ጥቂት የሚሠረይለት ጥቂት ይወዳል  ሲል አስተማረው መከረው በመሆኑም ኢየሱስ ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም ትንቢተ ኢሳይያስ 11 3 ስለዚህም ብዙ ሽታለችና ብዙ ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል በማለት ኃጢአትዋን ይቅር ካላት በኋላ ሴቲቱንም እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ ሲል አሰናበታት ታድያ ኢየሱስ ሊቀካህን ባይሆን ኖሮ ኃጢአትሽ ተሠርዮልሻል ባላላትም ነበር እውነተኛና ታማኝ ሊቀካህን ስለሆነ ኃጢአትዋን ይቅር አላት እንደገናም ኢየሱስ ስምዖን አይደለም ስለዚህ የሰዎችን ድካም የሚያውቅ ስለሆነ እንደ ስምዖን አልፈረደባትም ይልቁኑም ራራላትና ኃጢአትሽ ተሠርዮልሻል አላት ለዚህ ነው እንግዲህ የሃይማኖተ አበው ጸሐፊም እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም  የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን በማለት የጻፈልን ኢየሱስን በዕብራውያን 2 17 እና 18 በተጻፈልን ቃል መሠረት ወእንበይነ ዝንቱ ርቱዕ ይትመሰሎሙ ለአኀዊሁ በኲሉ ከመ ይኩኖሙ መሐሬ ወሊቀ ካህናት ምእመነ ዘመንገለ እግዚአብሔር ከመ ይሥረይ ኃጢአተ ሕዝብ እስመ በዘአመከርዎ ወአሕመምዎ ክህለ ረዲኦቶሙ ለሕሙማን ትርጉም ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው ያለን ከእነዚህ እውነቶች የተነሳ ነው እንደኛ የደከመና የተፈተነ በመሆኑ በድካማችን የሚራራልን ኃጢአታችንንም ይቅር የሚለንና የማይፈርድብን መሆኑን መገንዘብ የሚገባን ይህ ብቻ አይደለም እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች ይለናል ስለዚህም ኢየሱስ ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን ? አለው ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው ይለናል ኃጢአተኞችን በመውደድ ከኃጢአት ከድካም ከጉብጥናና ከሰይጣን እስራት ፈቶ ከመንፈስ የሆነ የአብርሃም ልጅነትን የሚሰጥ ጌታ ስሙ ይባረክ የሉቃስ ወንጌል 13 ፥ 10 _ 17 19 1 _ 10 በዚያን ዘመን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሰዎች ከኃጢአታቸው ተፈተው ለእርሱ ይሆኑ ዘንድ የእርሱ ፈቃድ ነው ስለዚህም ነው ስለ ጐባጣዋ ሴት ሲናገር ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን ? ያለው ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው ይለናል ስለ ዘኬዎስ ሲናገር ደግሞ የመጽሐፉ ክፍል እንደሚለን ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው ሁሉም አይተው ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው አንጐራጐሩ ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው ኢየሱስ ግን እንደ ፈሪሳውያን ሳይሆን የጠፋውን ሊፈልግ የመጣ ጌታ ነውና የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና አለው እኛም ከዚህ ቃል ጋር ተስማምተን አሜን እንላለን ጌታችን ኃጢአተኞችን ሊጸየፍ ሊንቅና ሊፈርድባቸው የመጣ ሳይሆን እነርሱን ተቀብሎ ኃጢአታቸውን ይቅር ሊል ሊያድናቸውም የመጣ ነው ይሄ ጌታ ታድያ ለነዘኬዎስ በጒብጥና ለምትቸገረዋ ሴት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ለእኛ ያው ነው ሰዎች ሲፈርዱብን ሲጸየፉን ሲያጥላሉንና ሲንቁን ከእኛም ጋር ሳይተባበሩ ሲቀሩና የእኛም ነገር ግድ ሳይላቸው ሲቀር እርሱ ግን ሳይጸየፈን ቤታችን ድረስ ገብቶ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል ጒብጥናችንንም ተመልክቶ ሳያልፈን ይፈውሰናል እስራታችንንም ይፈታዋል ይህ ነው እንግዲህ ሊቀ ካህንነት ኃጢአትን ይቅር በማለት የአብርሃም ልጅ ማድረግ ብዙ የሆነውንም ኃጢአት ይቅር ማለትና አንቺ ሴት እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ ማለት ከሊቀ ካህኑ ከኢየሱስ ካልሆነ በቀር ማንም ሊያደርገው አይችልም ማለት ማንም ኃጢአጽህ ተሰርዮልሻል እምነትሽም አድኖሻል በማለት ኃጢአትን አስተስርዮ በሰላም የሚሸኝ ከኢየሱስ በስተቀር ሌላ ሊቀካህን የለም አለሁ  ይህ ነገር እኔንም ይመለከተኛል እኔም እንዲህ ማድረግ እችላለሁ የሚል ከኢየሱስ ሌላ ሊቀ ካህን እርሱ ሊቀካህን ሳይሆን ያልተገባውን ሥራ የሚሰራ አላዋቂና የሰንበቴን ጽዋ የሚናፍቅ ሆዱ አምላኩ የሆነና ክብሩም በነውሩ የሆነ ነው እንዲህ ካለው ሊቀ ካህን ነኝ ባይ የመንደር አውደልዳይ እግዚአብሔር ይጠብቀን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ _ ፲፩ ላይም ኃጢአተኛ ናት ትወገር ብለው በፊቱ ያመጡለትን ሴት ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት ይውገራት በማለት አሳፈራቸው በመቀጠልም ወደ ሴቲቱ ዘወር ብሎ አንቺ ሴት ካሳሾችሽ የት አሉ የፈረደብሽ የለምን አላት እርስዋም ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ አለች ኢየሱስም እኔም አልፈርድብሽም ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት ይለናል ሰዎች ኃጢአተኛ ናት ትወገር ብለው የፈረዱባትን ሴት ኢየሱስ ተስማምቶ ትወገር አላለም ከእነርሱ ጋር አብሮ  ሲወግርም አልተገኘም ይልቁኑም የሴቲቱን ከሳሾች አሳፍሮ አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የት አሉ አለ አያይዞም እኔም አልፈርድብሽም ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አለ ኢየሱስ ዛሬም ከሳሻችንን እንዲ አድርጎ ያሳፍራል ሳይከሰንም ደግመን ኃጢአት እንዳንሰራ ከነገረን በኋላ በሰላም ይሸኘናል ለዚህ ነው በራዕይ ፲፪ ላይ ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና ያለን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ በደላችን በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው ይለናል ቆላስያስ ፲፬ እና ፲፭ እንደገናም በዕብራውያን ፲፬ እና ፲፭ ላይ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ስለሚለን ዲያብሎስ በዚህ ጌታ ስልጣኑ የተሻረ የተገፈፈ እንደገናም አሁን የጌታ ማዳን ከመገለጡ የተነሳ እርሱ ራሱ ሳይቀር የተጣለ ነው ስለዚህ ወገኔ ኢየሱስ በዚህ ሁሉ ታማኝ ባለውለታችንና መልካም ሊቀካህናችን ነው ክህነቱም ብዙዎች እንደሚሉት በምድር ላይ በሥጋው ወራት የተጠናቀቀና ያበቃ ብቻ ሳይሆን በሰማይም የሚቀጥልና እየቀጠለ ያለ ነው ለዚህ ነው እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ የተባልነው ዕብራውያን ፲፬ ክህነቱ በሰማይ ባይቀጥል ኖሮ የዕብራውያን ጸሐፊም በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀካህናት ብሎ ባልጻፈልን ነበር ያውም ከካህንም ይልቅ ትልቅ ሊቀካህን የጌታችን ስሙ የተባረከ ይሁን ከዚህም ሌላ በዕብራውያን ፳፫ _ ፳፰ ላይ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ይለናል የኢየሱስ ክህነቱ በሞት ያልተሻረና የማይለወጥ ስለሆነ ዛሬም ሊያማልድ በሕይወት ይኖራል ስለዚህ ኢየሱስ በሰማይ ያለ ብቸኛ አማላጃችን ነው ማዳኑ አንገት አያስቀልስ ፊት አያስመልስ ነው ታድያ መዳን የሚፈልግ ሰው ቃሉ እንደሚነግረን በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ካልመጣ በስተቀር መዳን አይችልም ለመዳን የግድ በእርሱ በኩል መምጣት አለበት ስለዚህም ነው በዮሐንስ ወንጌል ፲፬ ላይ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለን ኢሱስ መንገድና እውነት ሕይወትም ባይሆን የዕብራውያን ጸሐፊም በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ብሎ አይጽፍልንም ነበር ጌታም ለመዳኛ ሌሎች መንገዶችን ተጠቀሙ ይለናል እንጂ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎ ቁርጡን አይነግረንም ነበር ስለዚህ ሌሎች መዳኛ ናቸው ብለን በራሳችን ያዘጋጀናቸውን መንገዶች ገደል መቧጠጡን በዋሻ መደበቅ መክረሙን ዳቤ ሣሊነክ አዘጋጅቶ ማነሽ ባለ ሳምንት ማለቱንና የመሣሠሉትን እርግፍ አድርገን ትተን በአዳኝነቱ አማራጭ በማይሰጠው በኢየሱስ አምነን በእርሱ በኩል ብቻ ወደ አብ እንግባ የመዳን ቀንም አሁን ነውና ፪ኛ ቆሮንቶስ ይሄ መዳን አሁን ይሁንልን ይህንን ትምህርት በክፍ ትምህርትም ላይ እቀጥለዋለሁ እስከዚያው የጌታ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment