Thursday 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ሃያ አምስት



ቤተክርስቲያን




ክፍል ሃያ አምስት




ለክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጥብቃ ታስተምራለች







ቅዱሳን ወገኖች ዛሬ ወደ እናንተ የቀረብኩት በአዲስ ትምህርት ነው ባለፈው ትምህርታችን ቤተክርስቲያን (  1ኛ  )የክርስቶስ  የመሆን ጥቅሙን ( 2ኛ ) በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጥብቃ ታስተምራለች በሚሉ ሃሳቦች ዙርያ ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶችን ማስተላለፌ ይታወሳል አሁን ደግሞ  ( በ3ኛ ) ደረጃ ለክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጥብቃ ታስተምራለች በሚል ሃሳብ እንደሚከተለው እንማማራለን የተወደዳችሁ ወገኖች ለክርስቶስ ስለሆንን የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን 2 ቆሮንቶስ 5 10 ለክርስቶስ ስለሆንን በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ አለን 2 ቆሮንቶስ 11 2 እና 3 ለክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው በማለት በኲራት የምንሆንበትን መንገድ አሳየን  1 ቆሮንቶስ 15 23 ለክርስቶስ ስለሆንን በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ከእስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ በማለት ሐዋርያው ተናገረን ሮሜ 16 5 ለክርስቶስ ስለሆንን ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ሲል ሐዋርያው ጻፈልን ኤፌሶን 4 12 _ 13 ለክርስቶስ ስለሆንን ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ አለን ፊልጵስዩስ 1 9 _ 11 ለክርስቶስ ስለሆንን ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ሲል ሐዋርያው መከረን ፊልጵስዩስ 1 27 ለክርስቶስ ስለሆንን ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ ሲል ሐዋርያው ጻፈልን ኤፌሶን 5 24 ለክርስቶስ ስለሆንን ባሪያዎች ሆይ፥ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ በማለት ሐዋርያው ተናገረን ኤፌሶን 6 5 ለክርስቶስ ስለሆንን እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው በማለት ለክርስቶስ በመገዛት ውስጥ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘትና በሰውም ዘንድ መመስገን እንዳለ ሐዋርያው ጠቆመን ሮሜ 14 18 ለክርስቶስ ስለሆንን ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ በማለት ሐዋርያው ለክርስቶስ መስቀል ያለውን ምጥ በእንባ ሳይቀር  ገለጸልን ፊልጵስዩስ 3 18 ለክርስቶስ ስለሆንን የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ ሲል ሐዋርያው ለፊልሞና ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ማደግና ማፍራት ያለውን የልመናውን ድምጽ አሰማን ፊልሞና 1 6 ለክርስቶስ ስለሆንን ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል ሲል የክርስቶስን በመንግሥታት ላይ የሚያገኘውን የፍጻሜ አገዛዝ አስታወቀን ራዕይ 11 15 ወገኖቼ እነዚህን ጥቅሶች ለክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን የሚገልጹ በመሆናቸው ለክርስቶስ በመሆናችን የሚያገኙንን በረከቶች የሚናገሩ ናቸውና አጥኗቸው ከሕይወታችሁም ጋር አዋሕዱና ተጠቀሙባቸው ለሌሎችም አስተላልፉ ይህንን ትምህርት በሚቀጥለው የክፍል ሃያ ስድስት ትምህርታችን ላይ እናጠቃልለዋለን እስከዚያው ተባረኩልኝ


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment