Thursday 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል አስራ ስምንት



ቤተክርስቲያን


ክፍል አስራ ስምንት


የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች


የተወደዳችሁ ወገኖች ባለፈው በክፍል አስራ ስድስትና አስራ ሰባት ትምህርታችን ላይ ገላትያ ፳፱ ላይ የተጻፈውን የመጽሐፍቅዱስ ክፍል መነሻ በማድረግ የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን በሰፊውና በዝርዝር ማቅረባችን ይታወሳል ዛሬ ግን ይህንኑ ገላትያ ፳፱ ላይ የተጻፈልንን ሃሳብ መደምደምያ አድርገን ትምህርታችንን እናጠቃልላለን ገላትያ ፳፰ እና ፳፱ እንዲህ ይላል አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ ይለናል  ወገኖች ይህ በጣም የሚደንቅ ቃል ነው መጽሐፉ የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ ይለናል የክርስቶስ ለመሆን ደግሞ ምስጢሩ በክርስቶስ መሆን ነው በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ ልዩነት ሳይኖር ባርያ ጨዋ ወንድ ሴት ሳይል የክርስቶስ ናቸው ስለዚህ የክርስቶስና በክርስቶስ በሆኑ ሰዎች መካከል አንድ ሰው መሆን እንጂ ልዩነት የሚባል ነገር የለም ለዚህም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ልዩነትን ከመጥላት ይመስላል ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ በማለት የተናገረው ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፪ ይህ ሐዋርያ በአንድ ወቅት የክርስቶስና በክርስቶስም ከመሆኑ በፊት የነበረውን የቀድሞ ሕይወቱን እንዲህ ሲል አብራርቶልናል በቅድሚያ በፊልጵስዩስ _ ፲፰ የተጻፈልንን የመጽሐፍቅዱስ ክፍል ሄደን እንመልከት እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና በማለት አሁን ላይ የደረሰበትን ትክክለኛ የክርስትና ማንነትን በግልጽ ከነገረን በኋላ ወደ ግል የቀድሞ የሕይወት ታሪኩ ይገባና እንዲህ በማለት ይጀምራል እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ  ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ በማለት ተናገረ እንግዲህ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ነው እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ ያለን እኔን የምትመስሉ ሁኑ የሚል ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ ቃሉን እንደሚከተለው በቅደም ተከተልና በረድፍ ያስቀመጥኩት ስለሆነ ለሁላችሁም ግልጽ ነውና ላብራራው አያስፈልገኝም በ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፩ ፳፪ _ ፳፱ የተጻፈውን ሃሳብ ስንመለከት ደግሞ እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ ዕብራውያን ናቸውን፧ እኔ ደግሞ ነኝ የእስራኤል ወገን ናቸውን፧ እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን፧ እኔ ደግሞ ነኝ። የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን፧ እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፤ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን፧ የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልናደድምን፧ ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ ወገኖቼ አሁንም የዚህ ሐዋርያ ጉዳይ ያለው ዕብራዊነት እስራኤላዊነት የአብርሃም ዘር መሆን የክርስቶስ አገልጋይነትና ስለስሙም የሆነውን ከባባድ መከራዎችን የመቀበል ሁኔታን ሳይሆን በውስጡ ሸክም ሆኖ የከበደበት ነገር የአብያተ ክርስቲያናት አሳብ ነው የአብያተ ክርስቲያናት ሃሳብ ደግሞ ሃሳባችን የተበላሸ ካልሆነ በክርስቶስና ለክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ሃሳብ ነው መጽሐፍ ሲናገር በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭጫችኋለሁና ነገር ግን እባብ በተንኰሉ ሔዋንን እንዳሳታት አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምንአልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ ይለናል ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፩ _ ስለዚህ የሚያስመካን ሐዋርያው ጳውሎስ ያነሳቸውን የመጽሐፍቅዱስ ሃሳቦች ልብ ብለን ተመልክተናቸው ከሆነ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ያለነቀፋ መሆናችን በክርስቶስ በሆነልን ጽድቅና ባገኘነውም ነገር ለማደግ ወደፊት ለመሄድና ለመዘርጋት መፍጠናችን የክርስቶስ አገልጋይ መሆናችን ዋጋ በመክፈልም ከሌሎች ይልቅ ብልጫ ማሳየታችን ሳይሆን የክርስቶስ መሆናችን ነው መቼም የክርስቶስ ሳንሆን እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሕይወታችን ሊያልፉ አይችሉም ምናልባትም ሳናቀውና ሙሉ ለሙሉም የክርስቶስ ሳንሆን እነዚህ ነገሮች አልፈውብን ከሆነ ይህ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ ልናፍርበት አይገባምና እንደገና ተመልሰን የክርስቶስ መሆናችንን ማረጋገጥ አለብን  በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም እንዲህ ይለናል ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ ፩ኛ ዮሐንስ መልዕክት ፲፪ _ ፲፭ ይለናል እንደገናም የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁም ይለናል ፩ኛ ዮሐንስ መልዕክት ፲፫ ምክንያቱም ትልቁ የሕይወት መሠረታችን አገልግሎታችን በጌታ ቤት ያሉ ትልልቅ የሆኑ የአገልግሎት ስሞቻችን በጌታ ቤት ያሳለፍነው ጊዜና የተቀበልነው መከራ ሳይሆን የክርስቶስ መሆናችን ነው የክርስቶስ ሳንሆን አቤት የጻድቃን መከራቸው ተብለው አንቱ ያሰኙን እነዚህ ነገሮች በፍጻሜው ሰዓት በእሳት ውስት ባለፉ ጊዜ የሚቃጠሉብን ይሆናሉና አይጠቅሙንም ፩ኛ ቆሮንቶስ _ ፲፭ ሐዋርያው እንግዲህ እነዚህን ሁኔታዎች ከመረዳት የተነሳ ነው እነዚህን እውነቶች ያሳየን ሐዋርያው አሁንም በዚህ ነገር ትምክህት የሌለውና ከድካሙ በሚሆነው ነገር ይመካል ወገኖቼ ይሄ ሐዋርያ ምን ዓይነት የበራለት ሰውና የተባረከ ሐዋርያ ነው ዛሬ እኮ የገደለን አገልጋዩንና ክርስቲያኑን ሁሉ የፈጀው ነገር ትምክህት ነው ከድካሙ በሚሆነው ነገር የተመካ ሰው ግን አንደኛ ማን መሆኑን የተረዳ ድካሙንና የድካሙንም ልክ ያወቀ ጌታ ከሠራው በቀር የኔ ብሎ የሚቆጥረው ነገር የሌለው ሰው ነው ነገር ግን ከዚህ ይልቅ በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን መድረኮቻችንን ያጣበበ ያደባባይና የጀማ ክሩሴዶቻችንን ያጨናነቀ የሰዎች ገድልና ገኖ የወጣው የፖስተር ስሞቻቸው ነው ታድያ ይሄ ሁኔታ ወዴት ይወስደን ይሆን ጥንት ጌታን ባላወቅንበት ዘመን ትተን ወደመጣነው ገድልና ድርሳን የሰዎች ስንክሳር ወይስ ወደ ሌላ እግዚአብሔር ወደ እውነተኛው የወንጌል ልብና የክርስቶስም ልብ ይመልሰን ሐዋርያው እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ፧ እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን ያለው እኮ ከዚህ የተነሳ ነው ሊያውም ይህንን ያለውና ያደረገው እንዲሁ ማለት ስላለበት ለማለትም ብሎ ሳይሆን ከበርናባስ ጋር በመሆን ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ በመሮጥም ጭምር ነው  የሐዋርያት ሥራ ፲፬ _ ፲፮ ተመልከቱ ወገኖች ሆይ ዛሬ መልካሙን ዘመን ጉሸማና መዋረድ መታሰርና መደብደብ አንተ ማነህ መባል የሌለበትን ጊዜ አገኘን ብለን በተዋቡት አደባባዮቻችን ላይ ተመቻችተንና ተነስንሰን የራሳችንን መልካምነት ገድላችንንም ጭምር የሌሎችን ደግሞ መጥፎነትና ብልሹነት  ብናወራም ነገ ከድካማችን በቀር ልንናገር የማንደፍርበት ጊዜም ሊመጣ እንደሚችል  ሐዋርያው እንዲህ ሲል ያስታውሰናል ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል በደማስቆ አርስጦስዮስ ከተባለ ንጉሥ በታች የሆነ የሕዝብ ገዥ ሊይዘኝ እየወደደ የደማስቆ ሰዎችን ከተማ ያስጠብቅ ነበር በቅጥሩም ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝና ከእጁ አመለጥሁ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፩ _ ፴፫ የዚህ ክፍል ቀጣይ ትምህርት ገና ያላለቀና የሚቀጥል በመሆኑ በክፍል ፲፱ ትምህርት ላይ እስክንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ እያልኩ የምሰናበታችሁ


በጌታ ወንድማችሁ የሆንኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment