Sunday 7 December 2014

ለፍፃሜህ ተስፋ አለ

ለፍፃሜህ ተስፋ አለ


ለፍፃሜሽ ተስፋ አለ…………


ለፍፃሜዎ ተስፋ አለ……………..

 

ለፍፃሜያችሁ ተስፋ አለ………………………

 

ለፍፃሜያችን ተስፋ አለ…………………………………….
 







የፍፃሜ ተስፋ ከሰው ሕይወት ጠፍቶ 
ሁሉም ግራ ገብቶት እልባቱን አጥቶ
ፍጥረት ሲተራመስ በስቃይ ጎዳና 
በልቅሶ በዋይታ እንዲያው በደፈና
ያውና ይታያል ግራ የገባው ሰው 
ሕይወት ጨልማበት መፍትሔ ከልክላው 
ለዚህ ለምስኪኑ ግራ ለተጋባው
መፍትሔ የሚሆን ካለበት ሊያወጣው 
በቃሉ ተጽፎአል አንብቦ ቢረዳው 
እኔም ዝቅ ብዬ የቃሉን እውነታ 
እስቲ ልናገረው በረድፍ በተርታ 
ወገኖች አድምጡ ሆናችሁ በእርጋታ
ራሔል አለቀሰች እጅግ ተመርራ 
ልጆችዋ ተወስደው ከያሉበት ሥፍራ
ወደ ምርኮ ሀገር ለጣር ለመከራ 
የዋይታ ልቅሶ ድምጽ በራማ ተሰማ 
በቅድስቷ ሀገር በጽዮን ከተማ
ራሔልም ደከመች መጽናናት እንቢ አለች 
ባጠገቧ ያሉ ልጆችዋን ስላጣች 
እግዚአብሔርም አለ በቃሉ መልሶ 
ድምጽሽን ከልክዪ ዓይንሽን ከልቅሶ 
በቃ አለቀለት አበቃለት ብለሽ
ለሥራሽ የሚሆን ደግሞም ለክፍያሽ
ተስፋ ብትቆርጪ ሁኔታው አታክቶሽ
ከእግዚአብሔር የሆነ ተስፋ ተቀጠለ 
ነገርን ሊለውጥ አምላክሽ ቸኮለ
የተስፋ ፍጻሜ ከእግዚአብሔር መጣ
የሰው ልጅ አረፈ ከመጣበት ጣጣ
ከጠላቶች ምድር ምርኮ ተመለሰ
የራሔል ሐዘንዋ እንባዋ ታበሰ
እግዚአብሔር ልጆቹን እንደዚህ ያጽናናል
የተወሰደውን ፈጥኖ ያስመልሳል
ስለዚህ ወገኖች በተስፋ ተጽናኑ
በሙሉ ኃይላችሁ በእግዚአብሔር እመኑ
እግዚአብሔር ተናግሮ መቼ ዋሽቶ ያውቃል
መልካሚቱን ቃሉን ይፈጽምልናል
ከራሳችን ሃሳብ ስንውጣ በፍጥነት
ፍጻሜና ተስፋ ሰላም ወዳለበት
ጌታ ያደርሰናል ይሰጠናል እረፍት

No comments:

Post a Comment