Thursday 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ሃያ



ቤተክርስቲያን



ክፍል ሃያ





በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች


ባለፉት ጊዜያት ቤተክርስቲያን የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች በሚል አርዕስት ለተከታታይ ሳምንታት ተከታታይ የሆኑ ሃሳቦችን በቅደም ተከተል ማስተላለፋችንና ማስተማራችን ይታወሳል በነዚህ ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በብዙ እንደተጠቀማችሁ አምናለሁ ተስፋም አደርጋለሁ አሁን ደግሞ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች በሚል አርዕስት እንዲሁ ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶችን ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ በትሕትናና በማስተዋል ሆናችሁ እንድትከታተሉም በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙ ብዙ ነው ከነዚህም መካከል መጽሐፍቅዱሳችን የሚያስተምረንን እውነት ከዚህ እነደሚከተለው አቀርበዋለሁ በክርስቶስ ስለሆንን እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ ተባልን ሮሜ 6 11 በክርስቶስ ስለሆንን የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው የሚል ቃል ተጻፈልን ሮሜ 6 23 በክርስቶስ ስለሆንን እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ የሚል ቃል ተነገረን ሮሜ 7 4 በክርስቶስ ስለሆንን እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም የሚል የድል ቃል ታወጀልን አሜን አሁንም እኛም በክርስቶስ ኢየሱስ ስለሆንን ኩነኔ የለብንም ያመነ ሁሉ ይህንን ቃል አሜን ብሎ ቢቀበል ኩነኔ የለበትም ሮሜ 8 1 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶናል ሮሜ 8 2 በክርስቶስ ስለሆንን ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድተናል ሮሜ 8 39 በክርስቶስ ስለሆንን ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል ሲል ጳውሎስ ተናገረን ሮሜ 9 1 እና 2 በክርስቶስ ስለሆንን እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን ሮሜ 12 5 በክርስቶስ ስለሆንን አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ ?  ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ ?  ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና ተብሎ ተጻፈልን ሮሜ 14 10  በክርስቶስ ስለሆንን እንግዲህ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚሆን ነገር በክርስቶስ ኢየሱስ ትምክህት አለን ሮሜ 15 17  በክርስቶስ ስለሆንን ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ እናንተም ስመጣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንድመጣ አውቃለሁ ሲል ጻፈልን ሮሜ 15 29 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ በማለት ጻፈልን ሮሜ 16 3 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ ለኢሩባኖን ለምወደውም ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ የሚል መልዕክትም ጻፈልን ሮሜ 16 9 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰዎች ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ በማለት ተናገረን ሮሜ 16 10 በክርስቶስ ስለሆንን በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ሲል ጻፈልን 1 ቆሮንቶስ 1 2 እና 3  በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ 1 ቆሮንቶስ 1 4 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው አለን 1 ቆሮንቶስ 1 30 _ 31 በክርስቶስ ስለሆንን እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም ሲልም ተናገረን 1 ቆሮንቶስ 3 1 በክርስቶስ ስለሆንን እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን በማለት ጻፈልን 1 ቆሮንቶስ 4 10 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና ሲል ተናገረን 1 ቆሮንቶስ 4 15 በክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ የምወደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፥ እኔም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚሆነውን መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል አለን 1 ቆሮንቶስ 4 17 በክርስቶስ ስለሆንን ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ህግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ በማለት ተናገረን 1 ቆሮንቶስ 9 21 በክርስቶስ ስለሆንን እንግዲያስ በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋላ ካለን በኋላም አያይዞ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና በማለት ተናገረን 1 ቆሮንቶስ 15 22 በክርስቶስ ስለሆንን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕለት ዕለት እሞታለሁ አለን 1 ቆሮንቶስ 15 31 በክርስቶስ ስለሆንን ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው አሜን ሲልም ተናገረን 1 ቆሮንቶስ 16 24 በክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና 2 ቆሮንቶስ 1 5 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው አለን 2 ቆሮንቶስ 1 21 በክርስቶስ ስለሆንን እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ በማለት ይቅርታን አስተማረን 2 ቆሮንቶስ 2 10  በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን በማለት እኛም አመሰገንን 2 ቆሮንቶስ 2 14 በክርስቶስ ስለሆንን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን 2 ቆሮንቶስ 2 17 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን 2 ቆሮንቶስ 3 4 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ  ብሉይ ኪዳን ሲነበብ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና ተባልን 2 ቆሮንቶስ 3 14 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ። በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና ሲል ሐዋርያው ጻፈልን 2 ቆሮንቶስ 4 6 በክርስቶስ ስለሆንን መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናል 2 ቆሮንቶስ 5 10 በክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል ሲል ሐዋርያው ተናገረን 2 ቆሮንቶስ 5 17 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው 2 ቆሮንቶስ 5 18 በክርስቶስ ስለሆንን እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ 2 ቆሮንቶስ 5 19 በክርስቶስ ስለሆንን በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለሚሆን መታዘዝ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና እግዚአብሔርን ያከብራሉ ሲል ተናገረን 2 ቆሮንቶስ 9 13 በክርስቶስ ስለሆንን እኔም ራሴ ጳውሎስ፥ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ግን ብርቅ የምደፍራችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ ሲል ሐዋርያው መከረን 2 ቆሮንቶስ 10 1 በክርስቶስ ስለሆንን ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ ሲል ሐዋርያው ተናገረን 2 ቆሮንቶስ 12 2 በክርስቶስ ስለሆንን ለእናንተ ስለ ራሳችን እንድንመልስ ሁልጊዜ ይመስላችኋልን ? በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን፤ ነገር ግን፥ ወዳጆች፥ እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን ሲል ሐዋርያው ነገረን 2 ቆሮንቶስ 12 9 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ በማለት ሐዋርያው ተገረመብን ገላትያ 1 6 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ማኅበሮች ፊቴን አያውቁም ነበር ሲል ተናገረን ገላትያ 1 22 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ ሲል ሐዋርያው አስረዳን ይህ ትምህርት በዚህ አላበቃም በክፍል ሃያ አንድ እንቀጥለዋለን እስከዚያው ሰላም ሁኑ ተባረኩ

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment