Friday 5 December 2014

መጽሐፈ አርጋኖን የአርጋኖን መጽሐፍ ክፍል ሁለት



መጽሐፈ አርጋኖን


የአርጋኖን  መጽሐፍ


ክፍል ሁለት


የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው በአርጋኖን መጽሐፍ ላይ ተዘግበው ወይም ሰፍረው ያሉ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጋጩትን ሃሳቦች ነውና እነዚህን ሃሳቦች ከዚህ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ ተከታተሉ ይህንን ስል ግን የአርጋኖን መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል ነው ከእግዚአብሔር ቃል ጋራም በእኩልነት የምናስተያየው መጽሐፍ ነው እያልኩ እንዳልሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ይገባል የአርጋኖን መጽሐፍ በክፍል አንድ ትምህርቴ ላይ እንደገለጽኩት ለጸሎት ብለው ሰዎች የጻፉት መጽሐፍ መሆኑን የኦርቶዶክስ መምህራን ይናገራሉ በማለት የመጽሐፉን ደራሲ ሳይቀር ጠቁሜአለሁ ይህንን መጽሐፍ ደግሞ የሚገለገሉበት በኦርቶዶክስ እምነት ዙርያ ያሉ ምዕመናን እንጂ እኛ በጌታ አምነን ዳግም የተወለድን ቅዱሳን አለመሆናችንን አውቀን በመጽሐፉ ውስጥ ያነሳኋቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ ተዘምዶ ያላቸው ለማስተምረውም የእግዚአብሔር ቃል አስረጂ ሆነው በዋቢነት የሚጠቀሱ በመሆናቸው እንደገናም በዛ ያለውን የኦርቶዶክስ ሕዝባችንን ካህናቱን ዲያቆናቱንና ምዕመናኑን ጭምር  ሊያስተምሩ ወደ ጌታ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ሊያመጡ ወደ እግዚአብሔር የቃሉ እውነትም ሊያደርሱ የሚችሉ በመሆናቸው  እየተጻፉና እየተሰጡ ያሉትን ትምህርቶች በማስተዋል እንድትከታተሉ ከወዲሁ በጌታ ፍቅር ላሳስብ እወዳለሁ እንግዲህ ዛሬ በክፍል ሁለት ትምህርቴ ላይ የማነሳው ሃሳብ ከዚህ እንደሚከተለው ነው  በዚሁ በመጽሐፈ አርጋኖን ላይ የማርያምን ስም እየጠራ ኤልያስን ከጌታ ጋር ያነጻጽራል አያይዞም ኤልያስ በእሳት ሠረገላ ወደ ብሔረ ሕያዋን ቢሻገርም ከራሱ አልፎ ማንንም ሊያሻግር አልቻለም ከአንቺ የተወለደው ክርስቶስ ግን መሐይምናንን ማለት በስሙ ያመኑትን አማኞችን ከሞት ወደ ሕይወት አሻገረ ካለማወቅ ወደ ማወቅ አመጣቸው ይለናል ይህ ብቻ አይደለም ኤልሳዕ ንዕማንን ከለምጹ እንዲድን ከማድረግ አንስቶ ብዙ ተአምራትን አሳየ መራራውንም ውሃ በጨው አጣፍጦ መካኖች ሴቶች እንዲወልዱ አደረገ አልጫ የሆኑትን ነፍሳት ግን ጣዕም እንዲኖራቸው ለማድረግ አልተቻለውም ክርስቶስ ግን የሥጋንና የነፍስን ለምጻሞችን አነጻ እያለ ይዘረዝራል አሁን ግን ለዛሬ በትኩረት የምንመለከተው ኤልያስ ከጌታ ጋር በንጽጽር የቀረበበትን ሃሳብ ነው በሚቀጥለው በክፍል ሦስት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ኤልሳዕ ከጌታ ጋር በንጽጽር የቀረበበትን ሃሳብ እንመለከታለን ኤልያስ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ መወሰዱን ብናምንም ወደ ብሔረ ሕያዋን ማለት ወደ ሕያዋን ሀገር እንደሄደ ግን የሚጠቁም የመጽሐፍቅዱስ ክፍል አናገኝም ደግሞም የለም ለምን ስንል አንደኛ ኤልያስ ያረገው በሥጋው ነውና ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ይህን እላለሁ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም ስለሚለን ቃሉ 1ኛቆሮንቶስ 15 50  ወደ ብሔረ ሕያዋን ማለት ወደ ሕያዋን ሀገር ሄደ ማለት አንችልም ሁለተኛው ማስረጃችን ደግሞ ወአልቦ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ እጓለ እመሕያው ዘውእቱ ይነብር ውስተ ሰማይ ትርጉም ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው ይለናል የዮሐንስ ወንጌል 3 13  ስለዚህ ከሰማይ የወረደ ሞትን አሸንፎ በሕያውነት ወደ ሰማይ የወጣ ኢየሱስ ብቻ ነው በመሆኑም የኢየሱስን ማረግና ወደ ሰማይ መውጣት ከምንም ከማንም ጋር የምናስተያየውና የምናነጻጽረው ጉዳይ አይደለም እርሱ ከሙታን በመነሣት በኩር ነው በመወለዱ በኩር ነው በትንሣኤውና በእርገቱ በኩር ነው ኤልያስ ወደ ሰማይ በእሳት ሠረገላ ቢወሰድም ይኸው ኤልያስ ተመልሶ መጥቶ እንደሚመሰክርና እንደሚሞት ለመግለጽ አንዳንድ ሰዎች በራዕይ 11 3  ላይ ከተገለጹት ከሁለቱ ምስክሮች አንዱ ኤልያስ ነው ይላሉ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ እርገት ግን ሞትን አሸንፎ ወደ ሰማይ መውጣትና የሕያውነት እርገት በመሆኑ ዳዊት በመዝሙሩ ግብኢ ነፍስየ ውስተ ዕረፍትኪ እስመ እግዚአብሔር ረዳኢኪ እስመ አድኀና ለነፍስየ እሞት ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ ወለእገርየኒ እምዳኅፅ ከመ አሥምሮ ለእግዚአብሔር በብሔረ ሕያዋን ትርጉም ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድኖአልና በሕያዋን አገር በእግዚአብሔር ፊት እሄዳለሁ መዝሙር 114 ( 116 ) 7 _ 9 ስላለን ኢየሱስ በማረጉና ወደ ሰማይ በመውጣቱ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልናል ነፍሳችን ወደ ዕረፍት ተመልሳለች ከአይኖቻችን ላይ እንባዎች ታብሰዋል እግሮቻችን ከመሰናክል ድነዋል በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ በማመናችን ምክንያት ሕያዋን ሆነናልና በሕያዋን ሀገር  በእግዚአብሔር ፊት መሄድ ችለናል ገናም እንሄዳለን በኢየሱስ በማመናችን ምክንያት ኃጢአት እንዳሸሸው እንደ መጀመርያው አዳም የምንሸሽና የምንሸሸግ አይደለንም እንደገናም ተቅበዝባዥ ተንከራታችና  እንቅፋት የበዛብን ሆነን የምናለቅስ አልሆንንም ከመቅበዝበዝ ወጥተን ወደ ነፍሳችን ጠባቂና እረኛ ተመልሰናል 1 ጴጥሮስ 2 25   ስለዚህ የኢየሱስን ማረግ ከማንም ጋር የማናስተያየውና የማናመሳስለው ፍጹም የተለየ እርገት ነው እንደገናም ይሄ ወደ ሰማይ የወጣልንና ያረገልን ጌታ ተመልሶ ይመጣል ተመልሶ የሚመጣውም ደግሞ ትላንት እንደሞተልን ዛሬም ሊሞትልን ሳይሆን  ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ያመነውን ለዘላለም ለሁልጊዜም ከራሱ ጋር ሊያደርገን ሊያኖረንና ሊወስደን ነው ዮሐንስ ወንጌል 14 1 _ 4 1 ተሰሎንቄ 4 13 _ 18  ወደ መጽሐፈ አርጋኖን ስንመጣ የመጽሐፈ አርጋኖን ጸሐፊ የጠቆመንን መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት ሳናደንቅ አናልፍም ይህንን ያልኩበት ምክንያት የመጽሐፈ አርጋኖን ጸሐፊ እንደነገረን ምንም እንኳ ኤልያስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወይም ወደ ሕያዋን ሀገር አረገ ተነጠቀ ባንልም በእሳት ሠረገላው ወደ ሰማይ ወጥቷል ታዲያ በእሳት ሠረገላ በአውሎ ነፋስም ወደ ሰማይ የወጣና የተሻገረ ቢሆንም በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የወጣው የመጽሐፈ አርጋኖን ጸሐፊ እንደዘገበልን ሌሎችን ለማሻገር ብሎ ሳይሆን ለራሱ ስለሆነ ከራሱ አልፎ ማንንም ሊያሻግር አልቻለም ከማርያም የተወለደው ኢየሱስ ግን ያመኑትን አማኞቹን ከሞት ወደ ሕይወት አሻገረ ካለማወቅ ወደ ማወቅ አመጣቸው ብሎናል ይህ እውነት ነው እንግዲህ ኤልያስ ብቻ ሳይሆን ማናቸውም ቅዱሳን ፣ ጻድቃንም ሆኑ ሰማዕታት የተወለዱት የሞቱት ለራሳቸው ነው ለእኔ ለአንተ ለአንቺ ለእርስዎ ለእኛና ለእያንዳንዳችንም ብሎ የተወለደም ሆነ የሞተ ማንም ጻድቅ ፣ ቅዱስም ሆነ ሰማዕት የለም  የእኛ ጌታ ኢየሱስ ግን የተወለደው ለእኛ ነው የሞተውም ሆነ የተነሣው ያረገው ዳግመኛም የሚመጣው ለእኛው  ነው ለዚህ ነው መጽሐፍ ሲናገር እስመ ፍቅረ ክርስቶስ ያጌብረነ ናጥብዕ ውስተ ዝንቱ ሕሊና እስመ አሐዱ ሞተ ቤዛ ኩሉ በዘወድአ ሞተ ኩሉ ውእቱ ሞተ በእንተ ኩሉ አመ እለሂ የሐይዉ አኮ ለርእሶሙ ዘየሐይዉ ዘእንበለ ለዝኩ ዘበእንቲአሆሙ ሞተሂ ወሐይወሂ ትርጉም ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና ፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ ያለን 2 ቆሮንቶስ 5 14  እና  15  የተወደዳችሁ ወገኖች መጽሐፈ አርጋኖን እንደገናም የእግዚአብሔር ቃል እውነት አጠንክሮ በእንዲህ መልኩ ከነገረን እኛን ስለማጽደቅ በሞቱና በትንሣኤው ብቸኛ በሆነው በዚህ ጌታ አምነንና ዛሬውኑ ወስነን ለዚህ ጌታ ሕይወታችንን ብንሰጠው የመዳን ቀን አሁን ነውና 2 ቆሮንቶስ 6 2 አሁኑኑ መዳን ለሕይወታችን ይሆናል በዚህ ውስጥም እውነተኛ የሆነውን ማወቅ ልቡናንም ማግኘት ለእኛ ይሆናል ይበዛልናል ደግሞም ይጨመራል የዮሐንስ ወንጌል 17 3 1 ዮሐንስ መልዕክት 5 20  እና  21 ይህ እውነት ተጽፎልን ሳለ ግን ከዚህ ይልቅ ለደህንነታችን ፣ የዘላለምም ሕይወት ለማግኘታችን ከሞት ወደ ሕይወትም ለመሻገራችን  ኤልያስን እንዲሁም እርሱን መሰሎች ነቢያት ጻድቃን ቅዱሳን ሰማዕታት የተባሉትን ብንከተል ስማቸውን ብንጠራና በስማቸውም አሻሮ ብንቆላ ፣ ጠላ ብናስጠምቅና ዝክር ብናዘክር አድኑኝ ፣ አትርፉኝ ብለን ብንማጸንም አዳኙ ጌታችን ኢየሱስ ያለ አማላጅ ያለዝክርና ያለጸበል ጸዲቅ ብቻውን አዳኝ ሆኖ ከሚያድነን ወጪ የምናተርፈው  አንድም ነገር የለም ስለዚህ አድኑኝና አትርፉኝ አትርፉኝ እያልን በጸበል ጸዲቃችን በዝክራችንና ዲል ባለው ድግሳችን ከኤልያስ ከመሰሎቹም ጻድቃን ሰማዕታት ጀርባ እንዲሁ በድካማና ከንቱ በሆነ ጥረት እንዳንቀር ዛሬውኑ ቀን ሳለ ሳይመሽብን ወደ ኢየሱስ እንምጣ

ኢየሱስ ያድናል


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment