Thursday 18 December 2014

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching...: Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ ክፍል ሦስት

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ ክፍል ሦስት

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ ክፍል ሦስት

የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ ክፍል ሦስት



የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ
 
ክፍል ሦስት
 
 
በክፍል ሦስት የአባ ዘውዱ ኪዳኑን ምስክርነት የምንመለከተው ስለ መብቃት ስለ መዝጋትና ወደ ጌታ ስለመጡበት ጉዳይ ነው የምንመለከተው ቅዱሳን በማስተዋል ሆናችሁ የምስክርነቱን መጨረሻ ተከታተሉ አባ ዘውዱ ኪዳኑ ምስክርነታቸውን ሲቀጥሉ እንዲህ ነበር ያሉት መገለጥ ለማግኘት ትንቢት ለመናገር መብቃት ይጠይቃል በእርግጥም ደግሞ እንደነዚህ ዓይነት ስጦታ ያላቸው ሰዎች በገዳሙ ውስጥ ከሃያና ከሰላሣ ዓመታት በላይ ያሳለፉ ናቸው ወደ ገዳሙ ለሚመጡ አዳዲስ መናንያንም በጸሎት ተጋድሎ ሲያደርጉና አቅጣጫን ሲያሳዩ የቆዩ ናቸው ሆኖም በገዳማት ውስጥ ትንቢት ከመናገር ያለፈ የብቃት ደረጃ አለ
 
ከሣቴ ብርሃን ምን ዓይነት ? የብቃቱ አረጋጋጭስ ማነው ?
 
አባ ዘውዱ የመብቃቱ እርግጠኛነት አስቀድሞ የሚመጣው ከራሱ ከግለሰቡ ነው ምክንያቱም አንድ ባሕታዊ የቱንም ያህል ዓመታት በገዳም ውስጥ ቢቆይ እርሱ ራሱ ልዘጋ ነው ብሎ ካልተናገረ ወደዚህ ብቃት መድረሱ አይታወቅም
 
ከሣቴ ብርሃን ልዘጋ ነው ማለት ምን ማለት ነው ?
 
አባ ዘውዱ አንድ ባሕታዊ ጭራሹኑ ከቤቱ ላለመውጣት የሚወስነው ውሳኔ ነው እነርሱ እንደ ኮሚቴ ዓይነት ናቸው አንድ ባሕታዊ የመዝጋት ጥያቄ ሲያቀርብላቸውም እገሌ ልዘጋ ነው ብሎ ጠይቋል ብለው ይሰበሰባሉ ኮሚቴዎቹ እንደ ዋና ነጥብ የሚወስዱትና የሚያጣሩትም ጾምና ጸሎት ማብዛቱን በጠባዩ ሸጋ ትሑትና የፍቅር ሰው መሆኑም ነው ይህ ሰው ሊዘጋ ይበቃል ? ወይስ አይበቃም ? ብለው መክረው ለመዝጋት ያልደረሰ የመሰላቸውን ሰው ግድየለም ትንሽ ቆይተህ ተጋደል ይሉታል ለመዝጋት ያልደረሰ ሆኖ ሳለ ቢዘጋ ግን የሰይጣን ጦርነት ሊመጣበትና እስከ እብደት ሊያደርሰው ይችላል ከዚህ የተነሳም አብደው የሚለፈልፉ ብዙ ናቸው
 
ከሣቴ ብርሃን ለመዝጋት የበቃው ሰው ጨርሶ ከቤቱ ሳይወጣ ለመኖር ሲወስን አኗኗሩ እንዴት ያለ ነው ?
 
አባ ዘውዱ በቃ ከማንም ጋር ሳይገናኝና ሳይነጋገር ቤቱን ዘግቶ ቁጭ ይላል በገዳሙ ውስጥ አርድዕት የሚባሉ ተለማማጅ መነኮሳት በቀን አንድ ጊዜ ምግቡን መስኮቱ ላይ ወይም በሩ ሥር ያስቀምጡለታል ዕዳሪው እንኳ የሚወጣው እዚያው ቤቱ ውስጥ ቆፍሮ ነው እስከ ዕለተ ሞቱም የቀን ጸሐይን ሳያይ ቤቱን ዘግቶ ኖሮ እዚያው ይሞታል
 
ከሣቴ ብርሃን ያሳዝናል
 
አባ ዘውዱ በጣም ይህ ሰው መኖር መሞቱ የሚረጋገጠው ሁለት ሦስት ቀን ደጃፉ ላይ የተቀመጠለትን ምግብ ያልተጠቀመ ከሆነ ነው ያኔም ቤቱ ተቆርቁሮ በሕይወት ያለና የሌለ መሆኑ ይጣራል መሞቱ ሲረጋገጥም በሩ ተሰብሮ አስከሬኑ ወጥቶ ይቀበራል ሌላው በገዳም ውስጥ በር ሳይዘጉ ነገር ግን ከመነኮሳቱ ጋር ሳይቀላቀሉ ብቸኛ መሆን የሚመርጡ ባሕታውያንም አሉ እነርሱ ደግሞ እልም ወዳለው በረሃ ውስጥ ገብተው የሚኖሩ ናቸው ለእነርሱ ሕይወት የሚባለው ነገር ዳዊት መድገምና ገድላትን ማንበብ ነው አንዳንዶቹም መጽሐፍ ገልጦ ማንበብ ሳያስፈልጋቸው ሁሉን በቃላቸው የሚወጡ ናቸው ሁሌም የሚገርመኝ ግን በገዳማት ከወንጌላት የዮሐንስ ወንጌል ተወዳጅና በቃል የሚንበለበል የመሆኑን ያህል ፊደሉን እንጂ ብርሃኑን የሚያስተውለው ማንም የለም
 
ከሣቴ ብርሃን የገዳም ኑሮ ዓለምን ንቆ ከኃጢአት እድፈት ራስን ጠብቆ የሚሹትን ሰማያዊ ጽድቅ የመቀዳጀት ጥረት እንደሆነ ነግረውኛል በነገ ሕልማቸው ውስጥ ጽድቅን ለማግኘት በዚያ ጎዳና መጓዝን አማራጭ አድርገው ለሚወስዱ ወገኖች ምን ዓይነት ምክር ይሰጣሉ ?
 
አባ ዘውዱ በመሠረቱ አንድ ሰው ወደ ገዳም የሚያስጉዘው ሃሳብ የጽድቅ ረሃብ ነው በከተማ ስትኖር እለት እለት ከሚያጋጥምህ የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ርቀህና ለእግዚአብሔር ተቀድሰህ ለመኖር መፈለግህንም አመልካች ነው ዘፈን ዝሙትና ስካር ከሞላበት ሠፈር ሸሽተህ ከእነዚህ እድፍ ራስን ለማንጻት መመኘትህን ገላጭ ነው ወደ ገዳም ብገባ ከእነዚህ ሁሉ እርቃለሁ ከሰው ጋር ስለማልገናኝም ከሃሜትና ከምኞት አመልጣለሁ ብለህ የምትወጥነው የጽድቅ ውጥን ነው እዚያ ጦርነቱ ሁሉ የሃሳብ እንጂ የግብር አይደለም ሆኖም በሥጋ ከመፈተንም የበለጠ ሊጠነክር ይችላል ገዳማዊነት ከኃጢአት ለመሸሽ በሕይወትህ የምትወስነው ከባዱ ምርጫ ነው ኃጢአት ግን ባንተ ሩጫ ብቻ ሸሽተህ የምታመልጠው አይደለም በኢየሱስ ደምና ጸጋ ካልተሸፈንክ በቀርም ሕሊናን ከሰይጣን ክስ የሚያላቅቅ ምንም ዓይነት ሌላ መንገድ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ እወዳለሁ
 
 
ከሣቴ ብርሃን ብዙ ወገኖች በገዳም ያሉ መነኮሳት ለጽድቅ እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ ሲመለከቱ ከተማ ቁጭ ብለው ያማራቸውን እየበሉና እየጠጡ በክርስቶስ ጸጋ መጽደቃቸውን በሚናገሩ ሰዎች ሲበሳጩና የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሲያጣጥሉ ተመልክቼ አውቃለሁና ሁለቱን ጎዳናዎች በማነጻጸር የሚነግሩኝ ይኖራል ?
 
አባ ዘውዱ ልክ ነው እኔም ቀደም ሲል ከተማ ቁጭ ተብሎ ቁርጥ እየተበላና ማኪያቶ እየተጠጣ ጸድቄያለሁ ብሎ የመናገር ድፍረት ከየት እንደሚመነጭ ለማወቅ ይቸግረኝ ነበር በገዳምም ቢሆን የበረሃው መነኩሴ የከተማውን የሚያጣጥለው በዚሁ መንፈስ ነው ፍትፍት እየበሉ ነጭ ልብስ እየለበሱና ጫማ እየተጫሙ መነኩሴ ነኝ ማለት የማይዋጥላቸው ባሕታውያን ብዙ ናቸው አየህ የክርስቶስ ጽድቅ ካልገባህ ሁሉን ከምግብና ከመጠጥ ጋር ነው የምታያይዘው
 
ከሣቴ ብርሃን ከምግብና ከመጠጥ ጋር ያልተያያዘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ለአባ ዘውዱ የታያቸው መቼና እንዴት ነው ?
 
አባ ዘውዱ ሮሜ 10 3 ላይ ያራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም የሚል ቃል አለ አየህ በሃይማኖት ሁልጊዜ የራስን ጽድቅ የማቆም ነገር ነው ያለው ሰው የራሱን ጽድቅ ማቆም በጀመረ ጊዜ ደግሞ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ለመገዛት ይሳነዋል እኔም ብሆን ሃይማኖቴ ባቆመልኝ የጽድቅ መንገድ ተመርቼ  ከገዳም ገዳም ከሀገር ሀገር ስንከራተት ከኖርኩ በኋላ የእግዚአብሔር ጽድቅ ክርስቶስ ኢየሱስ በርቶልኝ ሸክሜን ሁሉ በእምነት እርሱ ላይ አራግፌ ከሰይጣን የዕለት ከዕለት ክስ ነጻ ወጣሁ በማለት አባ ዘውዱ በአንድ እህት ቤት የጸሎት አዳር ነበረና ወደዚያ ተጋብዘው መሄዳቸውን ይናገራሉ በዚያም የጸሎት አዳር ውስጥ ጸሎቱን የሚመራው አባ ብዕሴ ነበርና ጌታችን በመስቀል ላይ የከፈለውን የሞት መከራ ሲተነትነው አሰማሜ ከዚህ ቀደም ጨርሼ ሰምቼ እንደማላውቀው ትንግርት ነበር ለኃጢአቴ የሞተልኝን ጌታ መከራና ስቃይ ቀደም ብዬ ባውቀውም በዚያ መልኩ ተረድቼው አላውቅም ነበር እናም ነፍሴ ወጥቼ ልብረር እስክትለኝ ውስጤ በአንዳች ኃይል ይላወስ ጀመር ቃሉ ኃይል ስለነበረውም እኔ ብቻ ሳልሆን ፕሮግራሙ ላይ የነበርነው ሁሉ ሌሊቱን ስንንሰቀሰቅ አደርን ከጥቂት የእንቅልፍ ጊዜ በኋላም በገድልና በኃይማኖታዊ ተረቶች ታጭቆ የነበረ አእምሮ ጨርሶ ባዶ ሆኖ ነበር በዚያም ውስጥ የሞትኩልህ እኔ ነኝ የማድንህ እኔ ነኝ የሚልን ክርስቶሳዊ አዋጅ ውስጤ ያዳምጥ ጀምሮ ነበር ሁኔታው ሁሉ አምላኬ ከእስትንፋሴ ይልቅ ቀርቦ ያለ መሆኑን የሚያስረዳ በመሆኑ ኡኡ ብዬ ጮኬ ዳግመኛ መንሰቅሰቅ ጀመርኩ ያን ዕለት አባ ብዕሴ የመዳን ምስጢሩ ያለው በዚህ መነካት ውስጥ እንደሆነ ሲያስረዳኝ ዋልን ከዚያን ዕለት አንስቶምም ተለወጥኩኝ ተለወጥኩኝ በማለት አባ ዘውዱ ታሪኩን ይጠቀልላል ከዚያን ጀምሮ አባ ዘውዱ ውጤታማ የሆኑ አገልግሎቶችን ሰጥቶአል በአገልግሎት ጉዞዎች ውስጥም ብዙ ዋጋ ከፍሎአል አሁንም ዋጋ እየከፈለ የሚያገለግል የጌታ ባርያ ነው የአባ ዘውዱን ምስክርነት በዚህ አጠቃልላለሁ
 
 
ምስክርነቱን አዘጋጅቼ ያቀረብኩላችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ