Friday, 5 December 2014

የትምህርት ርዕስ የአዋልድ መጻሕፍት የውስጥ ገበና ሲገለጥና በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሽ የትምህርት ርዕስ የአዋልድ መጻሕፍት የውስጥ ገበና ሲገለጥና በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሽ Part One



የትምህርት ርዕስ የአዋልድ መጻሕፍት የውስጥ ገበና ሲገለጥና በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሽ
የትምህርት ርዕስ

የአዋልድ መጻሕፍት የውስጥ ገበና ሲገለጥና በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሽ
 
Part One
 

የአዋልድ መጻሕፍትን ምንንነት በእግዚአብሔር ቃል እውነት አጣርቶ ካለመፈተሽ የተነሳና እነዚሁ መጻሕፍት እንዲሁ በሽፍን የተቀመጡ በመሆናቸው በብዙ ቤተ እምነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በእኩልነት ቦታ ተሰጥቶአቸው፣ እኩል ሥልጣን አግኝተውና ቅዱስ መጽሐፍ ተብለው የሰዎች የሕይወት መመርያም ሆነው ይኖራሉ ሰዎችም ሳያፍሩ እነዚሁኑ መጻሕፍት የእምነታቸው መሠረትና መመርያ አድርገው ስለቆጠሩ ብቻ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በእኩልነት እየጠቀሱ እምነታቸውን ሲያስተምሩበት ለሰዎችም ሲያስረዱበትና ሲያብራሩ እንሰማለን ነገር ግን እነዚህን የአዋልድ መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ ከተጻፈው የእግዚአብሔርም ቃል ከሆነው ከመጽሐፍቅዱስ ጋር በእኩልነት ልናስተያያቸው ቀርቶ መጽሐፉን በራሱ ስንመረምረው ከእግዚአብሔር ሃሳብ የወጣና ከእግዚአብሔር ቃል ጋርም የሚጋጭ ሆኖ እናገኘዋለን እንደገናም ማን እንኳ እንደጻፈው የማይታወቅ አባት የለሽ መጽሐፍ ነው የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱሳችን ግን በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ በመሆኑ አንዱ የአንዱን ቃል አያፈርስም እርስ በእርሱም አይጋጭም 2 ጴጥሮስ 1 20 እና 21 ስለዚህ አዋልድ መጻሕፍትንም ይሁን በእግዚአብሔር መንፈስ ያልተጻፈን ማንኛውንም መጽሐፍ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አንድ አድርገን በእኩልነት ቦታ ልንሰጠው እና እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርገን ልንቀበለው አንችልም ተጻፈ የምንለው መጽሐፍ ቢኖር እንኳ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት አድርጎ የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን በመፈተሽና በማረጋገጥ የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት በአስረጂነት ከምንጠቀምበት በስተቀር በመጽሐፍቅዱስ ቃል ሥልጣን ልክ ቅዱስ መጽሐፍ ነው ብለን አንቀበለውም መጽሐፍቅዱሳችን በራሱ ምንም ሳይጨመርበትና ሳይቀነስበት ብቸኛ የሆነ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው ዘዳግም 4 2 ራእይ 22 18 _ 21
ይህን እንግዲህ ለመግቢያ ያህል ከተመለከትን ወደ መጽሐፉ ውስጠኛው ክፍል በመግባት በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ የሰፈሩት ሃሳቦች ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በምን ያህል ልዩነት ውስጥ እንዳሉ እንዴትስ ደግሞ እንደሚጋጩ እንመለከታለንና በማስተዋል ተከታተሉ።

መነሻ ምንባብ

ከአዋልድ መጻሐፍትና ከመጽሐፍቅዱስ የተወሰደ

………..
የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል በትእዛዙም
ፀንተው ለሚኖሩ ሰዎች በደላቸውንና ኃጢአታቸውን
ያስተሠርይላቸዋል ባለማመን የልብ ደንቆሮዎችና ንፉጎች
አትሁኑ

2
መቃብያን 12 3 እና 4

ናሁ ርእዩ መጠነ አፍቀረነ እግዚአብሔር እንዘ
ኃጥአን ንሕነ ክርስቶስ ሞተ በእንቲአነ

ትርጉም፦ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ
እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን
የራሱን ፍቅር ያስረዳል

ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከ ምዕራፍ 5 8

2 መቃብያን ምዕራፍ 12 3 _ 4 ላይ የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል በማለት ይናገራል ሐዋርያው ጳውሎስ ደግሞ ናሁ ርእዩ መጠነ አፍቀረነ እግዚአብሔር እንዘ ኃጥአን ንሕነ ክርስቶስ ሞተ በእንቲአነ ይለናል ትርጉም ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል በማለት የሚናገር ነው ሮሜ 5 8 እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ሃሳቦች ማለት የመቃብያንን መጽሐፍ ሃሳብና ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ የጻፈልንን ሃሳብ እንዴት አድርገን ልናስታርቃቸው እንችላለን ? ሁለቱም ሃሳቦች ፈጽሞ የማይገናኙና የተለያዩም ናቸው እንደ መቃብያኑ ጸሐፊ እግዚአብሔር የሚወዱትን ሰዎች ብቻ ወደደ ከተባለ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዴት ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአል እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ሊለን ቻለ ? እነዚህ ሁለቱ ሃሳቦች ማለት የመቃብያኑ መጽሐፍ ሃሳብና ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ያስተላለፈልን ሃሳብ ፍጹም የማይገናኙ ናቸውና የትኛውን እንመን ? ሁለቱም ትክክል ናቸው ብለን እንዳንደመድም እግዚአብሔር ሁለት አፍ የለውም ስለዚህ የግድ ከሁለቱ አንዱ ስሕተት ነው ብለን እንዳቋጭ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍቅዱስ ከመጽሐፈ መቃብያን ተለይቶ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈና የእግዚአብሔርን ሃሳብ የያዘ በመሆኑ ሁልጊዜም ትክክል ነው ስለዚህ በእርግጠኝነት የተሳሳተው የመቃብያን መጽሐፍ ነው እንደመቃብያን ሃሳብ እግዚአብሔር የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል ካልን ክርስቶስ የሞተው ለኃጢአተኞች በመሆኑ የክርስቶስን ሞት ከንቱ እናደርጋለን እግዚአብሔርም ለእኛ ያለውንና የሰጠንንም ፍቅር እናስተባብላለን የሮሜ መጽሐፍ እንደሚናገረው ክርስቶስ ደግሞ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ነው የሞተልን ምንም የሚወደድ ነገር ሳይኖረን እግዚአብሔር የራሱን ፍቅር ነው ያሳየንና ያስረዳን ገና ኃጢአተኞች ነበርንና እግዚአብሔርን ለመውደድ የሚያበቃ ይሄ ነው የሚባል ነገር የለንም መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደውም ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን ይለናል ሮሜ 5 10 እና 11 መጽሐፍቅዱሳችን እንደገናም ጠላትነታችችን አጉልቶ በማሳየት በሃሳባችን ሳይቀር ጠላቶች እንደነበርን ይናገራል ቆላስያስ 1 21 _ 23 ታድያ የመቃብያን መጽሐፍ የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል ካለን ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜና በቆላስያስ መጽሐፉ በነገረን ሃሳብ መሠረት ጠላት የሆነ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ተወደደ ከተባለ በስተቀር እግዚአብሔርን እንዴት ሊወድ ይችላል ? ጠላት ከሚሆን በስተቀር የሰው ዘር ከተባለ እግዚአብሔርን የወደደ ማንም የለምና እግዚአብሔር ግን ጠላቶች የነበርነውን የሰው ዘር በሙሉ ወደደ ስለዚህ ጠላቶቹ ለሆነው ለእኛ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጡ ልንናገርውም ሆነ ልንገልጸው ከምንችለው በላይ በመሆኑ በተወደድንበት ፍቅር እርሱን ከመባረክ በቀር የምንለው የለንም ለዚህ ነው የተባረከው ወንድማችን ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ በዝማሬው

ለምን ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደኸኛል
የፍቅርህ መግለጫ ይሄ ነው ለእኔ ተወግተሃል
አንተ ለእኔ የሆንከውን ያህል እኔ ለአንተ አልሆንኩም
ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼም አላየሁም
ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ
አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ ሲል የዘመረልን
ወገኖቼ ከዚህ የቀጠለውን ሃሳብ በሚቀጥለው ጊዜ አቀርበዋለሁ እና ባለመሰልቸት ይህንን ትምህርት እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር እጋብዛችኋለሁ እስከዚያው ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ

በጌታ ፍቅር የምወዳችሁ አገልጋያችሁ

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ለምን ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደኸኛል
የፍቅርህ መግለጫ ይሄ ነው ለእኔ ተወግተሃል
አንተ ለእኔ የሆንከውን ያህል እኔ ለአንተ አልሆንኩም
ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼም አላየሁም
ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ
አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ

ተባረኩልኝ

No comments:

Post a Comment