ቤተክርስቲያን
ክፍል አስራ ሰባት
የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች
የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች የሚለውን ንኡስ አርእስት መነሻ አድርገን መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃ በመስጠት በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙ ምን እንደሆነ በክፍል አስራ ስድስት ላይ በዝርዝር ማቅረባችን ይታወሳል አሁንም ከዚህ የቀጠለውንና ተያያዥነት ያለውን ሃሳብ በዝርዝር እናቀርባለን የክርስቶስ ስለሆንን ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ስላለን ኤፌሶን 3 ፥ 18 _ 19 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን እንሆን ዘንድ ተፈለግን ኤፌሶን 4 ፥ 12 _ 13 የክርስቶስ ስለሆንን ሐዋርያው ጳውሎስ ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ ተማራችሁ፥ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው አለን ቆላስይስ 1 ፥ 7 የክርስቶስ ስለሆንን አሁንም ሐዋርያው እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው አለን ቆላስያስ 2 ፥ 17 የክርስቶስ ስለሆንን በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ የምታመሰግኑም ሁኑ አለን ቆላስያስ 3 ፥ 15 የክርስቶስ ስለሆንን ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል በማለት ተናገረን ቆላስያስ 4 ፥ 12 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም ተባልን 1ኛ ተሰሎንቄ 2 ፥ 6 የክርስቶስ ስለሆንን የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና ተብሎም ተነገረን ዕብራውያን 3 ፥ 14 የክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው የሚል ቃልም ተነገረን ዕብራውያን 6 ፥ 1 _ 2 የክርስቶስ ስለሆንን በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ? ወይም እንዴት ? ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር ተባልን 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 11 የክርስቶስ ስለሆንን ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ የሚለውን የእምነት ቃል አዎንና አሜን ብለን ተቀበልን 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 18 እና 19 የክርስቶስ ስለሆንን ሐዋርያው ጴጥሮስ እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ ሲል ነገረን 1ኛ ጴጥሮስ 5 ፥ 1 የክርስቶስ ስለሆንን ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው ? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው አለን 1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 2 ፥ 22 የክርስቶስ ስለሆንን ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው ተባልን 2ኛ ዮሐንስ 1 ፥ 7 የክርስቶስ ስለሆንን ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና የሚል የድል ቃል ሰማን ራዕይ 12 ፥ 10 የክርስቶስ ስለሆንን በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ የሚል ቃል ተጻፈልን ራዕይ 20 ፥ 6 ወገኖቼ የክርስቶስ በመሆን ውስጥ እነዚህን የመሰሉ የእውነት ቃሎች አሉልን ስለዚህ በእነዚህ የቃሉ እውነቶች ውስጥ ለመኖር ራሳችንን ለክርስቶስ ልንሰጥና የክርስቶስ ልንሆን ይገባል ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ በክፍል 18 ትምህርታችን ላይ በገላትያ 3 ፥ 29 የተጻፈውን ሃሳብ መሠረት አድርገን የክርስቶስ የመሆን ጥቅም የሚለውን ሃሳብ እንጠቀልላለን እስከዚያው ድረስ ጌታ እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ እያልኩ እሰናበታለሁ
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment