Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል አስራ አንድ



ቤተክርስቲያን


ክፍል አስራ አንድ


ቤተክርስቲያን ለኅብረት እንደ ረጋ ወደብ እንደ መጠጊያ ሥፍራ ሆና የምታገለግል ናት በእንግሊዘኛው እንዲህ ልንለው እንችላለን Port , Harbor , A place of safety , Refuge  or other sheltered place for shipping የጸጥታና የደህንነት ሥፍራ በመርከብ ውስጥ የመርከብ ወደብ መሸሸጊያ ቦታ ከአደጋ የሚያመልጡበት ተገን መከለያና መጠለያ ማለትን የሚያመለክት ነው ቤተክርስቲያን ለኅብረት ጠቀሜታን ልትሰጥ እንዲህ ዓይነቱን አስደናቂ ስያሜ ያገኘችው  ከምን አንጻር ነው ስንል በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 41 እና 42 የተጻፈው ቃል እንዲህ ይላል ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር ይለናል ስለዚህ ቤተክርስቲያን ቃሉን የመቀበያ የመጠመቅያ የነፍሳት መጨመርያና መባዣ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት የሆነውን እንጀራ መቁረሻ በጸሎትም የመትጊያ ሥፍራ ናት ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን የሚያሰኛት እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ዋና ዋና ነገሮች ናቸው እነዚህ ነገሮች የሌሏት ቤተክርስቲያን ደሃ ጐስቋላ ዕውርና የተራቆጠች ናት ራዕይ 3 15 _ 22 ጸጥታና የደኅንነት ሥፍራ የረጋ ወደብ መሽሽጊያ ቦታና ከአደጋ የሚያመልጡበት ተገን እንዲሁም መከለያና መጠለያ  የሆነችው በገላትያ 1 4 ላይ  በተጻፈው ሃሳብ መሠረት ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ ይለናልና ከዚህ ክፉ ዓለም ለመዳን ስለ ኃጢአታችን የሞተውን ኢየሱስን አምነው የተቀበሉ ሁሉ እነዚህን  ዋና ዋና ነገሮች የሚያገኙበት ቦታ ይህቺው ቤተክርስቲያን ስለሆነች ነው ራስ በሆነው በክርስቶስ ተገጣጥማ የክርስቶስ አካል ልትሆን በተጠራች ቤተክርስቲያን ውስጥ ቃሉን መቀበል መጠመቅ የነፍሳት መጨመር በሕብረት እንጀራ መቁረስና በጸሎትም መትጋት ስላለ የሰዎች ሕይወት በመረጋጋት በጸጥታና በደኅንነት የተሞላ ነው ሰዎች በዚህ ኅብረት ውስጥ ባለ ተሳትፎ የእግዚአብሔር ቃል እና ራሱ እግዚአብሔር ተገን መከለያና መጠለያ  ይሆናቸዋል ሕይወታቸውም ከአደጋ ያመልጣል ቤተክርስቲያን እንግዲህ  ሁሉ በሁሉ የሆነችና የክርስቶስ የአካሉ ሙላት ልትሆንም የተጠራች በመሆንዋ ኤፌሶን 1 23 በሕይወታቸው ሰላም ያጡ ያልተረጋጉ ሰዎች ተጽናንተውና ተረጋግተው በደኅንነትም ተጠብቀው ይገኙባታል ከዚህ ክፉ ዓለም ያመለጡና እግዚአብሔር ተገን የሆናቸው ከሰይጣን እስራት የተፈቱ ያመለጡም ብዙዎች ናቸው በማምለጥ በመዳንና በመፈታትም ላይ ይገኛሉ በዚህ ውስጥ አሁንም አንድ ነገር እንድናስብ እፈልጋለሁ እርሱም ጸጥታ ነው ሰዎች በደኅንነት እና በሰላም ተጠብቀው ለመኖራቸው ምልክቱ ጸጥታ ነው እግዚአብሔር የሰጠን ጸጥታ ደግሞ ውጪያዊ  ሳይሆን ውስጣዊ ነው ውስጣችን እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ነገር አግኝቶ ማረፍ ሲጀምር ውጪያዊው ነገራችን ሁሉ በጸጥታና በእረፍት የተሞላ ይሆናል መጽሐፍቅዱሳችን በተለያዩ ሥፍራዎች ላይ ስለ ጸጥታ የሚናገረው ነገር አለ በዘሌዋውያን 25 18 ላይ ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ ይለናል ስለዚህ በምንኖርበት በማንኛውም ምድር ይሁን ባለንበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን በምንሠራበት መሥርያ ቤት በተሰጠን የሃላፊነት ቦታና አገልግሎት በቤታችን በትዳራችን ከሚስቶች ወይም ከባሎቻችንና ከልጆቻችን ጋር ከምንኖርበት ኅብረተሰብና አካባቢ ጋር  በጸጥታና በሰላም ለመኖር የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ፍርዱን ማድረግ ማለት ቃሉን መፈጸም ከእኛ ይጠበቃል ያኔ በጸጥታ እንኖራለን የኬጢ ሰዎች አብርሃምን በመልካሙ ቦታ ሬሳህን ቅበር ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም ያሉት አብርሃም የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ፍርድ ያደርግ ቃሉንም ይፈጽም ስለነበረ ነው ዘፍጥረት 23 1 _ ፍጻሜ የተጻፈውን እንመልከት በ1ኛ ተሰሎንቄ 4 10 _ 12 ላይ ደግሞ እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን ይለናል ጸጥታ የመኖራችን ምልክት ነው ጸጥታ የሌለው ሰው ከእግዚአብሔርም ጋር ከራሱም ሆነ ከሌሎች ጋር መኖር የማይችል ማለት ነው ለዚህ ነው ሐዋርያው በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን እያለ የመቄዶንያን ወንድሞች የሚናገረው የመቄዶንያ ወንድሞች ደግሞ የዛሬዎቹ እኛ ክርስቲያኖች ነን ጸጥታ ኑሮ ስለሆነ በጸጥታ ልንኖር የምንቀናበት ፣ ጸጥታ ከሌሎች ወይንም በውጪ ካሉ  ሰዎች ብቻ የምንጠብቀው ሳይሆን ከራስ ከግልና ከውስጥ የሚጀምር ስለሆነ የራሳችንን ጉዳይ ልንጠነቀቅ ስንጀምር እንደ አብርሃም በውጪ ካሉ የኬጢ ሰዎች ዓይነት ሳይቀር መልካምን ምላሽ እናገኛለን አብርሃም በነበረው የውስጥ ጸጥታ ሰላምና በውጪ ካሉ ሰዎችም ጋር በነበረው አግባባዊ ምልልስ ምንም እንኳ እኔ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ ያለ ቢሆንም አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ አስብሎ ከኬጢ ሰዎች ዘንድ ከበሬታንና የመቃብር ሥፍራንም  አሰጥቶታል በጸጥታ ሊኖሩ መቅናት ለራስ ጉዳይ መጠንቀቅና በውጪ ባሉት ዘንድም በአግባብ መመላለስ ይህንን ያስገኛል ማለት የምናተርፈውና የሚያተርፍልንም ነገር አለ ማለቴ ነው ለዚህም ነው በ1ኛ ጴጥሮስ 2 12 ላይ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን የሚለን በጸጥታ ልንኖር ስንቀና በጸጥታም ስንሆን እንደ አብርሃም ኑሮአችን መልካም ይሆናል ደግሞም እንሰማለን እንደመጣለን  አብርሃም የኬጢን ሰዎች ስሙኝ ብሎ ጮሆና ተቆጥቶ አይደለም የተሰማው እንዲያማ ቢሆን ከቶውንም ቢሆን አይሰሙትም እንደገናም ከሀገራቸው ሳይቀር ያስወጡት ነበር አብርሃም ግን በጸጥታ ሊኖር የሚቀናና የራሱንም ጉዳይ የሚጠነቀቅ በውጪ ባሉትም በአግባብ የሚመላለስ ስለነበረ ድምጽ የሌለው አብርሃም በኬጢ ሰዎች ተሰማ ተለመነ የመቃብሩን ሥፍራ የሚከለክልህ የለም ተባለ ጸጥታ ጸጥታ ይምሰል እንጂ ላስተዋለው ሰው ትልቅ ድምጽና መልዕክት አለው ነገር ግን የዛሬዎቹ ክርስቲያኖች ከጸጥታ ይልቅ ጩኸትን ሁከትን ጥልንና ክርክርን የኔ ብቻ ይሰማ ባይነትን መርጠን የተቀመጥን በመሆናችን በኢሳይያስ 30 15 ላይ የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል እናንተም እንቢ አላችሁ፥ አለን እንደገናም በመክብብ 9 17 ላይ በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች በማለት ተናገረን ስለዚህ ጸጥታ ጥበበኝነትና አስተዋይነት ነው እንጂ ሞኝነትና ቂልነት አይደለም ሰው ጸጥ ስላለ የተሞኘ አይደለም በኬጢ ሰዎች ዘንድ የአብርሃም ጥበብ  የአብርሃም አለቅነት የታወቀው በጸጥታ ውስጥ ነው የሚጮሁ ሰዎች ግን ጩኸታቸው የስንፍናቸው መገለጫ ከሚሆን በስተቀር የሚያመጡት ለውጥ የለም በጩኸት ደግሞ የሚመጣ ምንም ነገር የለም ስለዚህ በጸጥታና በመታመን ኃይል እንዲሆንልን ዛሬውን እምቢ አሻፈረኝ ብለን ከተያያዝነው መደማመጥ ከሌለበት የመጯጯህ ሕይወት እንዲሁም ዛቻና ድንፋታ አጓጒል አድርጎ ከሚያስቀረንም ቀረርቶና ሽለላ አሁኑኑ  እንውጣ ሌላው የጸጥታ ትርጉሙ በሌላው ነገር ጣልቃ ሳይገቡ የራስን ሥራ መስራት የገዛ እንጀራንም መብላት ነው በ2ኛ ተሰሎንቄ 3 12 ላይ እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን ይለናል ሌላው ከዚህ ሃሳብ ጋራ እንድንይዘው የምፈልገው የክርስቶስ አካል በሆነችው በቤተክርስቲያን ውስጥ የአካል ብልት ሆነን ተገጥመን ስንኖር የነፍሳት መጨመር ቃሉን ተቀብሎ መጠመቅ በሐዋርያት ትምሕርትና በኅብረት እንጀራንም በመቁረስ መትጋት በየጸሎቱም መትጋት አለ ብያለሁ ታድያ ይህ ነገር ጤናማና እውነተኛ በሚሆንበት ጊዜ መመላለሳችን በብርሃን ይሆናል በ1ኛ ዮሐንስ 1 6 እና 7 ላይ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ይለናል ዛሬ ግን በተቃራኒው የብዙ ሰዎች ማለትም የክርስቲያኖች የአገልጋዮች ሳይቀር  የብዙ ጊዜ ምልልሳችን በብርሃን የማይሆነው የተቀበልነው የእግዚአብሔር ነገር ሙሉ ለሙሉ ጤናማና እውነተኛ ካለመሆኑ የተነሳ ነው አለበለዚያም የእራሳችን ጤናማ ያልሆነ  የሕይወት ምልልስ ስላለ ነው ይህ ሕይወት ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል ካልታደሰ እና ፍጹም አርነት ያልወጣ ካልሆነ  የራሱን ነገር ያስቀድማል ከወንድሜ እና ከእህቴ ይልቅ ለእኔ ለእኔ ማለትን ያበዛል በ1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 3 15 ላይ ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ ስለሚል ቃሉ ወንድምና እህትን ይጠላል ነፍሰ ገዳይም ይሆናል በብርሃን ስንመላለስ ግን ይሄ ሁሉ ይቀርና ወንድሞችን የምንወድ እንሆናለን ከሞት ወደ ሕይወትም እንደተሻገርንም በዚህ እናውቃለን ጌታ የምናነበውን ቃል ይባርክልን በሚቀጥለው የክፍል አስራ ሁለት ትምህርት ላይ እስክንገናኝ ሁላችሁንም ጌታ ይባርካችሁ


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment