Sunday, 7 December 2014

የባልና የሚስት የግንኙነት ምስጢር ክፍል አራት



የባልና የሚስት የግንኙነት ምስጢር

ክፍል አራት

በክፍል አራት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 19 4 _ 7 የተጻፈውን ሃሳብ ከዘፍጥረት 5 1 እና 2 ከተጻፈው ሃሳብ ጋር በማያያዝና በማገናዘብ ሊጣመሩ የሚገባቸው ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ ሰፋ አድርገን በመተንተን ይሆናል በማቴዎስ ወንጌል ላይ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ ፈጣሪ በመጀመርያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው ? ይለናል ማቴዎስ በወንጌሉ አላነበባችሁምን ? እያለ በጥያቄ መልክ ያነሳልንን ቃል በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ደግሞ የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ባረካቸውም ስለሚለን እግዚአብሔር ለማጣመርና ባልና ሚስት ለማድረግ ሴት እና ሴትን ወይም ወንድና ወንድን አለመፍጠሩን በሚገባ እንድንረዳ ያስቻለንና የደገፈን ሃሳብ ነው እግዚአብሔር ለማጣመር ወንድና ሴትን የፈጠረ በመሆኑ የዘፍጥረት መጽሐፍ ባረካቸውም ሲለን ማቴዎስ በወንጌሉ ደግሞ ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባሁምን ? በማለት ይህንን ጥያቄውን አሁንም እንደገና ሄደን በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ አዳም ከተናገረው ሃሳብ ጋር እንድናስተያይና አዳምም የተናገረውን ሃሳብ እንድንይዝ ይጠቁመናል አዳም ስለዚህ ጉዳይ ምን አለ ? ብንል ደግሞ እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ወደ አዳምም አመጣት አዳምም አለ ይህቺ አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል በሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ይለናል ዘፍጥረት 2 22 _ 25 ስለዚህ እግዚአብሔር የባረከው እና በረከቱንም ያሳረፈው እንዲህ አጥንት ከአጥንቴ ሥጋም ከሥጋዬ ናት በማለት እግዚአብሔር ከሰጣቸው እህቶች ጋር በቅዱስ ጋብቻ የተጣመሩትን ቅዱስንን እንጂ ከፆታ ውጪ በመሆን ያለፆታቸው ተዋደድን በማለት ሴት ሴት ጋር ወንድ ከወንድ ጋር ባልና ሚስት ሆነው የተጋቡትን አይደለም በእንዲህ ዓይንቱ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር ፈቅዶ ያጋባቸው ሰዎች ሳይሆኑ እግዚአብሔር ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ የሰጣቸው ናቸው ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶች መገናኘት ትተው እርስ በእርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለን ሮሜ 2 24 _ 28 የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ማለትም ሴቶች ከሴቶች ጋር ወንዶችም ከወንዶች ጋር መጋባት ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ መሰጠት ነውና ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ በመሰጠት ይጋቡ ዘንድ ለምን አሳልፎ ሰጣቸው ? ስንል እግዚአብሔርን ለማወቅ ያልወደዱና እግዚአብሔርንም ለማወቅ ፍጹም የማይፈልጉ ስለሆኑ ነው እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚፈልጉ ቢሆኑማ ኖሮ እግዚአብሔር ቅዱስ ወደ ሆነው በጥምረትም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ወደ ተባለው የወንድና የሴት ጋብቻ ይመራቸው ነበር ነገር ግን እግዚአብሔርን ለማወቅ ያልወደዱ በመሆናቸው ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው ይህ እንግዲህ በምድራችን ላይ ብዙ ጎልቶ ባይታይም በሰለጠነው ዓለም ግን በብዛት ሕጋዊ ሆኖ እየተደረገ ያለ ነገር በመሆኑ እጅግ በጣም የሚያሳዝን እግዚአብሔርንም ለቁጣው እንዲነሳሳ የሚያደርግ ትልቅ እርኩሰት ነውና በጉዳዩ እጅግ ተግተን በብዙ ልንጸልይበት ይገባል እላለሁ እግዚአብሔር ያጣምረውንና አንድ ሥጋ ይሆናሉ ያለውን ጋብቻ ሚልክያስ በትንቢታዊ መልዕክቱ እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን ? እርሱም የሚፈልገው ምንድነው ? ዘር አይደለምን ? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል መፋታትን እጠላለሁ ይላል የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይለናል ትንቢተ ሚልክያስ 2 14 _ 16 ስለዚህ በቅዱስ ጋብቻ ያለ የባልና የሚስት ትሥስር በወደድኩህና በወደድኩሽ ላይ ብቻ የተመሠረተ የጥምረት ትሥስር ሳይሆን አንድ ሥጋ የመሆን ትሥስር ነው ስለዚህ በሥጋ ተዋዶ ፍቅርን ከመቀባበል ባሻገር ባልና ሚስቱ በኪዳን ከተገናኙበት ወቅት አንስቶ በመካከላቸው የፈሰሰ አንድነታቸውን አጽንቶና አንድ አድርጎ የሚጠብቅ የሕይወት መንፈስ አለ ስለዚህ አይደለም መፋታት የልጅነት ሚስቱን ማታለል ኃጢአት በመሆኑ መንፈሳችሁን ጠብቁ ይለናል በዓለም ጋብቻ ግን ይሄ ነገር የለም ይኑር ብንል እንኳ በኪዳን የተጋቡ ባለመሆናቸው ምክንያት ትዳራቸውን የሚጠብቁበት አንድ ዓይነት መንፈስ የላቸውም በመሆኑም አብረው የሚኖሩት እስከተዋደዱ ድረስ ብቻ ነው በመካከላቸው ትንሽ ክፍተት ካለና አለመግባባቱም እየጨመረ ከመጣ ጋብቻቸውን ያፈርሳሉ አንዱ ለሌላው እራሱን አሳልፎ የሚሰጥበት የሚጠነቀቅበት የሚያዝንበትና የሚራራበት አካሌ ናት አካሉ ነኝ ስትልና ሲል ደግሞ የሚሸካከሙበትና የሚቻቻሉበት መንፈስ ስለሌላቸው መፋታታቸው የበዛ ነው መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም የባልና የሚስት ግንኙነት ወደድኩህ ወደድኩሽ ከመባባል ጊዜያዊና ወቅታዊ ፍቅር ያለፈ በመሆኑ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት ይመግበዋል ይንከባከበውማል ይለናል ኤፌሶን 5 28 _ 30 ስለዚህ ራሱን የሚወድ ባል ሚስቱን የሚወድ ሊሆን ይገባልና ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ባደረገው ልክ የገዛ ሚስቱን ሃላፊነት ወስዶ መመገብና መንከባከብ ከእርሱ በብዙ ይጠበቃል ታድያ ይህንን የማያደርግ ባል ሃላፊነቱን በትክክል ያልተወጣና ከሚስቱም ጋር የተጣመረበት ምስጢር በትክክል ያልገባው በመሆኑ ባለበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የጋብቻ ትምህርትን በተገቢው መንገድ ተምሮ ይህንኑ እውነት ይበልጥ እንዲረዳ እናበረታታለን የሚስትንም ሁኔታ በተመለከተ መጽሐፍቅዱስ ሳይደብቅ በእርግጠኝነት ይነግረናል ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደራሱ አድርጎ ይውደዳት ካለን በኋላ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ ይለናል ኤፌሶን 5 33 ይህንን ትፍራ የሚለውን ሃሳብ በአዲሱ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም ወይም በእንግሊዘኛው መጽሐፍቅዱስ ሄደን ስንመለከተው ባልዋን ታክብር ነው የሚለን ስለዚህ ሚስቶች የሆንን ቅዱሳን እህቶች ባሎቻችንን ልናከብራቸው እንጂ በሰው ፊት ልናሳጣቸው ልንኮንናቸው ልናዋርዳቸውና ልንዘረጥጣቸው አይገባም የጠፋ ነገር ቢኖር እንኳ በጓዳችን ማንም ሳይሰማ መመካከር ሲያስፈልግም መውቀስና መገሰጽ እንደገናም መፍትሄ ባለው ነገርና ሊያመጣ በሚችል ጉዳይም ላይ ተስማምቶ አብሮ መጸለይ አስፈላጊ ነው እንላለን የተወደዳችሁ ወገኖች የባልና ሚስትን ጉዳይ አስመልክቶ ከመጽሐፍቅዱሳችን ብዙ ሃሳቦችን አንስተን መነጋገር እንችላለን ለጊዜው ግን ቢያንስ እንደመንደርደርያ ሃሳብ እንዲሆናችሁ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት የተጻፉ ትምህርቶችን በጥቂቱም ቢሆን ላሰፍርላችሁ ወድጃለሁ ትምህርቱ ሰፊና ጥልቅም ስለሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ጌታ ሲመራኝ ወደፊት ልመለስበት እችላለሁ አሁን ግን ለጊዜው ይሄ ይበቅናል ወደፊት በሌላ ጌታ በሚሰጠኝ ትምህርት እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ የምላችሁ

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም

No comments:

Post a Comment