የመልዕክት ርዕስ
በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ፥ 26
ወምስለ ዝንቱ ኩሉ ጸድፍ ዐቢይ ይከልአነ ማእከሌነ ወማእከሌክሙ
ከመ እለሂ ይፈቅዱ እምለፌ ይኅልፉ ኢይክሃሉ መጺአ ኀቤክሙ
ወእለሂ መንገሌክሙ ይዕድዉ ኀቤነ
ትርጉም፦
ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደእኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል አለ
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ፥ 26
ሰዓሊ ለነ ማርያም ምዕዳው እምሠርም ዘጽድቅ ተንከተም
ትርጉም፦ ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሰላል የሆንሽ
ማርያም ሆይ ለምኚልን
ሰዓሊ ለነ ከሚባል ክፍል ገጽ 131 መጽሐፈ ሰዓታት የተወሰደ
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ምዕመናን አረጋውያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም የቸሩ መድኃኔዓለም ወዳጆች በሀልዎቱ በቸርነቱና በረድኤቱ ለዚህ ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን
ከዚህ በመቀጠል በመጽሐፍ ቅዱሱ ቃል ላይ የተጠቀሰውን ሃሳብና የመጽሐፈ ሰዓታቱን አባባል እንደሚከተለው በንጽጽር እንመለከተዋለን በመጀመርያ ግን ገደል መኖሩን የመጽሐፍ ቅዱሱ ቃልም ሆነ የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ አልሽሽጉንም ቁልፉ ሃሳብ ግን ከዚህ ገደል የምንሸጋገረው በማን ነው ? የሚለው ነው የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ ማርያም መሆንዋን ሊጠቁመን ስለወደደ ሰዓሊ ለነ ማርያም ምዕዳው እምሰርም ዘጽድቅ ተንከተም አለን ትርጉም ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሰላል የሆንሽ ማርያም ሆይ ለምኚልን ማለት ነው ይህንን ሃሳብ ስናየው ታድያ ከረግረግ ልታሸጋግረን ማርያም የኢየሱስ እናት የጽድቅ መሰላል ነችን ? መልሱን ከእግዚአብሔር ቃል እንመለከታለን የመጽሐፍቅዱሱ ቃል ግን ከዚህ ረግረግ ወይም ገደል ማምለጫው ሰዎች ገና በዚህ ምድር በሕይወት እያሉ የሙሴና የነቢያትን መጽሐፍ በመስማት እንደሆነ ቃሉ ይነግረናል ሙሴና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ ከሙታን እንኳ አንድ ቢነሳ አያምኑም በማለት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል ሙሉውን የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ ለማግኘት ከፈለግን የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ፥ 19_መጨረሻው ሄደን መመልከት እንችላለን እምነት የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት የሚመጣ ነው ሮሜ 10 ፥ 17 ለዚህ ነው የሙሴና የነቢያትን መጽሐፍ መስማት እንዳለብን የነገረን ከዚህ ውጪ ግን መስማትም ሆነ ማመን የሌለብንን ነገር መስማትም ሆነ ማመን የለብንም መጽሐፍቅዱሳችን ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሰላለ ማርያም እንደሆነች የሚነግረን ነገር የለም እንደገናም በዚህ ጉዳይ ማርያም ሆይ ለምኚልን እንድንል የእግዚአብሔር ቃል አያስተምረንም ይህ እንግዲህ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያልተጻፈ በመሆኑ ሰይጣን ሰዎችን በተንኮሉ ወደ ሲኦል ለማጋዝ የተጠቀመበት ዘዴና አሁንም እየተጠቀመበት ያለ ሥውር ደባ መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ ይለናል 1ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 7 የእግዚአብሔር ቃል የማይደግፈው ማንኛውም እምነት ነክ ጽሑፍ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በጥምረት ሊሄድ ስለማይችል ተረት ነውና ከእርሱ ልንጠበቅ ይገባል ወደ ዋናው ጉዳይ ስንመጣ በመጽሐፍቅዱሱ ቃል መሠረት ወደዚህ ሥቃይ ሥፍራ እንዳንመጣ ሊረዱን የሚችሉት የሙሴና የነቢያት መጻሕፍት ናቸው እነርሱ የጽድቅ መሰላሎቻችን ናቸውና እነርሱን በመስማት እናመልጣለን እነርሱ ደግሞ የሚመሰክሩት ስለ ኢየሱስ ነው ወረከቦ ፊልጶስ ለናትናኤል ወይቤሎ ረከብናሁ ለኢየሱስ ወልደ ዮሴፍ ዘእምናዝሬት ዘጸሐፈ ሙሴ ውስተ ኦሪት ወነቢያትኒ ተነበዩ በእንቲአሁ ትርጉም ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው ይለናል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ፥ 46 እንደገናም ጌታ ለኤማሁስ መንገደኞች እንዲህ አላቸው ወይቤሎሙ ኦ አብዳን ወጉንዱያነ ልብ ለኢአሚን በኩሉ ዘይቤሉ ነቢያት አኮኑ ከመ ዝ ሀለዎ ለክርስቶስ ይትቀተል ወይባእ ውስተ ስብሓቲሁ ወአኀዘ ይፈክር ሎሙ እምዘሙሴ ወዘነቢያት ወእምኩሉ መጻሕፍት ዘበእንቲአሁ ትርጉም እናንተ የማታስተውሉ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን ? አላቸው ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው ይለናል የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ፥ 24_27 ስለዚህ እኛም እንደ ናትናኤል በሰማነው የመጽሐፍ ቃል ሕጉና ነቢያቱ በመሠከሩልን እውነት ከበለሱ በታች ካለው ሕይወታችን ወጥተን ወደ ኢየሱስ ስንመጣ ከረግረግ መሸጋገርያ የሆነውን እውነተኛውን የጽድቅ መሰላል እናገኘዋለን እርሱም መሸጋገርያ ድልድይና መሰላል ሆኖ ወደ አብ መንግሥት የሚያስገባን ኢየሱስ ነው በእርሱ በኩል ካልሆነ አሁንም የሚያጋጥመን ረግረግና ገደል ነው የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ፥ 6 ፣ ዕብራውያን 10 ፥ 19_25 ፣ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ፥ 44_ 52 እርሱ እንደ ናትናኤል አሁን ካለንበት አስከፊ ህይወት ያወጣናል እንደገናም ወደዚህ ስቃይ እንዳንመጣ በረግረግና በገደሉ ውስጥም ሰጥመን እንዳንቀር ከዚያ ስቃይ ያድነናል ታድያ መዳኛው በሕይወት እያለን አሁኑኑ አምነን ስንቀበል ነው 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 በኋላ በምጽአቱ ይደርስ የለ እንዴ ብለን ብንናገር ግን ለሰዎች አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላ ፍርድ እንደተመደበባቸው ይታወቃልና ዕብራውያን 10 ፥ 27 ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል እንባላለንና አይሆንም መዳን ለሚፈልግ ሰው አዳኙ ኢየሱስ ብቻ ነውና በዕድሉ ዛሬ መጠቀም አለበት በክርስቶስ ቀኝ ለተሰቀለው ወንበዴ ጌታ የሰጠው መልስ ነበረ ይህ ሰው በጌታ ቀኝ የተሰቀለ ወንበዴ ሆኖ ጌታን የለመነው ልመና ነበር ወይቤሎ ለእግዚእ ኢየሱስ ተዘከረኒ እግዚኦ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎ አማን እብለከ እመን ፈድፋደ ከመ ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት ትርጉም ኢየሱስንም ጌታ ሆይ በመንግሥትሕ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ይለናል የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 23 ፥ 42 እና 43 ይህ ወንበዴ ዛሬ ከኢየሱስ ጋር በገነት ለመሆኑ የሚያበቃው የራሱ በጎ ተግባር የሌለው ሰው ነው የለመነውም ልመና በመንግሥትሕ በመጣህ ጊዜ የሚል ነው ኢየሱስ ግን ዛሬ በገነት ትሆናለህ አለው ይህ የሚያሳየን የእግዚአብሔርን ምሕረት ነው እግዚአብሔር ይህንን ወንበዴም ሆነ እያንዳንዳችንን የተቀበለን ክርስቶስ ለደህንነታችን በሠራልን ሥራ ነው እኛማ የሚቆጠር ጽድቅ ስለሌለን ጽድቃችን የመርገም ጨርቅ ነው ኢሳይያስ 64 ፥ 6 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲሁ በክርስቶስ ሥራ ተቀበለን ይህ ጌታ የተቀበለን ወይም የሚቀበለን ታድያ በምጽአቱ ጊዜ ሳይሆን አሁን እንደዚህ ወንበዴ አስበን ብለን እራሳችንን ለእርሱ በሰጠንበት ጊዜ ነው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ለማጽደቅ ብቃት አለው የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ይለናል 1ኛ ዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 1 ፥ 7 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን ? አትሳቱ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣኦትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም ከእናንተም አንዳንዶች እንደዚህ ነበራችሁ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል ተቀድሳችኋል ጸድቃችኋል ይለናል ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን አሜን 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 9_11 እንደገናም በእኛ ሥራ ሳይሆን በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ይለናል ኤፌሶን 2 ፥ 18 እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ ብቻውን በሠራልን ሥራ ብቻ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባታችን የሚያረጋግጡልን ቁልፍ ሃሳቦች ናቸው እና በደንብ አድርገን እናጥናቸው እንያዛቸው ጌታ ኢየሱስ እንደ ናትናኤል ወደ ዘላለም መንግሥት ላልመጡ ብቻ ሳይሆን የጽድቅ መሰላል የሆነው የጌታን ቸርነትና ማዳን ከቀመሱ በኋላም ጉዞአቸውን ወደቀድሞ የትውልድ መንደራቸው ላደረጉ የኤማሁስ መንገደኞች መልስ የሚሰጥ ነበረ እነዚህ ሰዎች በሕይወታቸው የጠወለጉ ተስፋቸው የጨለመ ዓይኖቻቸውም የተያዙባቸው ሰዎች ናቸው በጣም የሚያሳዝነው ግን በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው የኢየሩሳሌምን ሴቶች መተቸታቸው ነው ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን ሥጋውንም ባጡ ጊዜ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ አየን ሲሉ መጥተው ነበር ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደተናገሩት ሆኖ አገኙት እርሱን ግን አላዩትም እያሉ ሲያወሩ ጌታ በመካከላቸው ተገኝቶ ለወሬያቸው እሰይ እውነት ብላችኋል ጎሽ አበጃችሑ ሲል እልባት ማጣፈጫ መቋጫ ወይም ማከያና መደምድምያ አልሰጠም ያለው ነገር ቢኖር እናንተ የማታስተውሉ ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ከማመን የዘገያችሁ በማለት የራሱን ማንነት ነው የገለጸው አያይዞም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው ይለናል ኢየሱስ ደግፏቸው ቢሆን ኖሮ እነዚህን ሰዎች የሚችላቸው ሰው አልነበረም ኢየሱስ ግን አልደገፋቸውምና በሥህተት ውስጥ ነው ያሉት ሰው በመጀመርያ ስህተት ነው ብሎ ወደሚያስበው ወደ ሌላው ሰው ከመሄዱ በፊት የራሱን ነገር ነው ማስተካከል ያለበት ምክንያቱም ሌላውን ተሳስተሃል ሲል ራሱ ተሳስቶ ይገኛልና የኤማሁስ መንገደኞች የሆኑት እንደዚህ ነው የሴቶቹን ነገር አስገረሙን እያሉ በመተቸት ሲጓዙ የራሳቸው ጉድ ወጥቶ ልባችሑ ከማመን የዘገየ የማታስተውሉ ተባሉ ችግሩ ያለው ሴቶቹ ጋር ሳይሆን የኤማሁስ መንገደኞች ጋር ነው ሴቶቹማ ሴቶችም ቢሆኑ ትክክል ናቸው ያስገረሙትም በተገላቢጦሽ ሴቶቹ ሳይሆኑ የኤማሁስ መንገደኞች ናቸው ዛሬም ታድያ በዘመናችን ጥፋት በመሰለን ነገር መነጋገርያ ያደረግናቸው አስገረሙን ብለን ቅዠታሞች ናቸው በማለት የፈረጅናቸው ሰዎች ትክክል ሆነው እኛ አገልጋዮች በትልልቅ ሥፍራና ቦታ ያለን ሰዎች የምንሳሳትበት ሁኔታ አለ ስለዚህ ወደዚህ የተሳሳተ ፍርድ ከመሄዳችን በፊት እኔስ ማን ነኝ ? የት ጋር ነኝ ? ምን ተረድቻለሁ ? በዚህ በምለውና በምናገረው ነገር የተሳሳትኩት እኔው እሆንን ? ማለቱ አስተዋይነት ነው ለዚህ ጉዳያችን ደግሞ ጌታ ተገልጦ እናንተ የማታስተውሉ ብሎ እስኪነግረን ድረስ መጠበቅ የለብንም ከወዲሁ ነገራችንን አውቀንና ራሳችንን መርምረን ማስተካከል ያለብንን ነገር ራሳችን ማስተካከል አለብን አለበለዚያ እኛው የዘገየነው ሳያንሰን ሌላውንም እናዘገያለን ቅዱሳን ወገኖች በዘመናችንም የእግዚአብሔር ሥራ እንደሚገባ ተጣጥሞ መሄድ ያልቻለው በዚህ ምክንያት ነው መዘግየት ማንም ይዘገያል መጠውለግም ማንም ይጠወልጋል ይደክማል ሰው በኃይሉ አይበረታምና የምንኖረው በጸጋው ነው ችግሩ ያለው ሰው በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን እያወቀ ድካሙን አለመቀበሉ ከዚያም አልፎ ሄዶ ሌላውን መተቸቱ ነው ይህ ነው እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሥራ እተገቢው ቦታ ላይ እንዲደርስ የማያደርገው እኛ የቅርብ ደቀመዛሙርት ስለሆንን ወይም በሌላ አነጋገር መሪዎች መጋቢዎች ሃላፊዎች ተናጋሪዎች መስካሪዎች ስለሆንን በሁሉም ነገር ላይ ትክክል ነን ማለት አይደለም አንዳንዴም ወደ ኋላ የቀረንበት እና የምንቀርበት ነገር ይኖራል ይህንን ደግሞ የግል የጸሎት ጊዜ በመውሰድና ከጌታ ጋር በመሆን ማስተዋል አስፈላጊ ነው ያኔ በሌሎች ከመፍረድና የጌታንም ሥራ ወደኋላ ከማድረግ እንድናለን ጌታም ለእኛ እንደ ቃሉ የተሠወረብንን ነገር መግለጥ መተርጎምም ይችላል ጌታ የምናነበውን ቃል ይባርክልን አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ምሥጋና ይድረሰው አሜን
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:
Post a Comment