ቤተክርስቲያን
ክፍል አስራ ስድስት
የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች
እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር
እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ
ገላትያ 3 ፥ 29
የክርስቶስ መሆን ፣ በክርስቶስ መሆንና
ለክርስቶስ መሆን ትልቅ ጥቅም አለው እያንዳንዱን ሃሳብ በዝርዝር እንመለከተዋለን ለዛሬ ግን የክርስቶስ መሆን በሚለው ሃሳብ ላይ እናተኩራለን
ነገር ግን ገላትያ 3 ፥ 29ን መነሻ አድርጌ በመግቢያዬ ላይ በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደተስፋው ቃል ወራሾች ናችሁ የሚለው መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል
ሃሳብ የትምህርቱ መጀመርያ እና የማጠቃለያም ሃሳብ በመሆኑ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ በስፋት እመጣበታለሁ
ወገኖቼ እነዚህን በክርስቶስ የመሆንን ጥቅም የሚገልጹ እያንዳንዱ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎችን በዝርዝር እንመልከታቸው ብንል ሰፊ ጊዜ ይወስድብናል እንደገናም ጊዜ አይበቃንም ነገር ግን በክርስቶስ የሆነ ሰው እነዚህ ጥቅሶች በክርስቶስ የመሆንን ጥቅም በግልጽነት የሚያሳዩ በመሆናቸው ማብራርያ ሳያስፈልገው በቀላሉ ሊረዳቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ ስለዚህ
አሁን በቀጥታ ወዳዘጋጀሁት በክርስቶስ የመሆን ጥቅም አልፋለሁ በመጽሐፍቅዱሳችን ላይ የክርስቶስ የመሆንን ጥቅም የሚገልጹ ክፍሎች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል እነርሱም ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ መንፈስ አለን ስለዚህም የእርሱ ወገን ነን ሮሜ 8 ፥ 9 የክርስቶስ ስለሆንን ሁሉ የእናንተ ነው እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው ተባልን 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 23 የክርስቶስ ስለሆንን ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን ? ተብሎ ተነገረን ዕብራውያን 9 ፥ 14 የክርስቶስ ስለሆንን ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ ተባልን 2ኛ ቆሮንቶስ 4 ፥ 4 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና ተባልን 2ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 5 የክርስቶስ ስለሆንን በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና ተብሎም ተነገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 2 ፥ 15
የክርስቶስ ስለሆንን እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን አለን ገላትያ 1 ፥ 7 _ 10 የክርስቶስ ስለሆንን በስሙ ጽዋ ውሃ ያጠጣን ዋጋው እንደማይጠፋበት በእርግጠኛነትና በእውነት ተነገረን የማርቆስ ወንጌል 9 ፥ 11 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ፍቅር ቁርጠኛና ግድ የሚለን አደረገን 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 14 የክርስቶስ ስለሆንን ስለ እርሱ የታሰርንበትን የክርስቶስን ምስጢር እንድንነግር ጸለይን ጸልዩልንም አልን ቆላስያስ 4 ፥ 3 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሚመጣ ሰምተናል አሁንም የክርስቶስ ተቃዋሚ በብዛት እንዳለ ተረድተናል የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነም አውቀናል
1ኛ ዮሐንስ 2 ፥ 18 የክርስቶስ ስለሆንን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚታመን መንፈስ አለን 1ኛ ዮሐንስ 4 ፥ 3 የክርስቶስ ስለሆንን ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀልን ገላትያ 5 ፥ 24 የክርስቶስ
ስለሆንን የክርስቶስን ነገር ፈለግን ፊልጵስዩስ 2 ፥ 21 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ስም በተጠራበት ሥፍራ ብቻ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርን ሮሜ 15 ፥ 20
የክርስቶስ ስለሆንን በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ
የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል ተባልን ሮሜ 16 ፥ 16 የክርስቶስ ስለሆንን ይህንም እላለሁ እያንዳንዳችሁ
እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ ክርስቶስ ተከፍሎአልን ? ጳውሎስስ ስለእናንተ ተሰቀለን ? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን ? ተባልን 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 12 _ 16 የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ ልብ አላችሁ ተብሎ ተነገረን 1ኛ ቆሮንቶስ 2 ፥ 16 የክርስቶስ ስለሆንን እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ የሚል የሕያውነት ስያሜን አገኘን 1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 27 የክርስቶስ ስለሆንን እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው ተባልን 2ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 3
የክርስቶስ ስለሆንን ሥጋችን የክርስቶስ ብልቶች ናቸውና የክርስቶስን ብልቶች ወስደን የጋለሞታ ብልቶች ልናደርጋቸው እንደማይገባም ተነገረን 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 15 የክርስቶስ ስለሆንን ባሪያ ሆኖ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው የሚል ቃል ተጻፈልን 1ኛ ቆሮንቶስ 7 ፥ 22 የክርስቶስ ስለሆንን ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም የሚል መመርያም ተነገረን 1ኛ ቆሮንቶስ 9 ፥ 12 የክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ ሲል ሐዋርያው በስፋት ተናገረን 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 3
የክርስቶስ ስለሆንን ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናችሁ ሲል ሐዋርያው ተናገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 8 ፥ 23 የክርስቶስ ስለሆንን በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቁጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ ነን ሲል አሁንም ሐዋርያው አጽንቶ ተናገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 17
የክርስቶስ ስለሆንን የክርስቶስ እውነት በእኛ እንዳለ ይህ ትምክህት በእኛ ዘንድ በሌሎች ሀገሮችም አይከለከልም 2ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 10 የክርስቶስ ስለሆንን እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና
ተብሎም ተነገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 13 የክርስቶስ ስለሆንን ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ ሲል ከራሱ ታሪክ ጋር አያይዞ ሐዋርያው አስተማረን 2ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 9
የክርስቶስ ስለሆንን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን ? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን ? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም ሲል ሐዋርያው ነገረን ቲቶ 1 ፥ 10 የክርስቶስ ስለሆንን ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ ተባልን ገላትያ 6 ፥ 2 የክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህም አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ የክርስቶስ ኢየሱስ እስር የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር እንበረከካለሁ ሲል ነገረን ኤፌሶን 3 ፥ 1 የክርስቶስ ስለሆንን ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ አለን ኤፌሶን 3 ፥ 4 የክርስቶስ ስለሆንን ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ በማለት
የተሰጠውን ጸጋ ገለጸልን ኤፌሶን 3 ፥ 8 _ 9 የክርስቶስ የመሆን ጥቅሙ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ነገር ግን
በክፍል አስራ ሰባት ትምህርታችን ላይ ቀጣዩን ሃሳብ እንመለከታለን እስከዚያው ሁላችሁንም ጌታ ይባርካችሁ እያልኩ የምሰናበታችሁ
ቀሲስ አባ ዮናስ ነኝ
No comments:
Post a Comment