ምዕራፍ ሁለት
ሕጉንም የሚጠብቁ ሰዎችን
እንደ አደራ ገንዘብ ይጠብቃቸዋል
2ኛ መቃብያን 12 ፥ 7
እስመ ኢይጸድቅ ኩሉ ዘነፍስ በገቢረ ሕገገ ኦሪት
በቅድመ እግዚአብሔር እስመ እምኦሪት ተዐውቀት
ኃጢአት
ትርጉም፡- የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ
ፊት ስለማይጸድቅ ነው ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና
ሮሜ 3 ፥ 20
የአዋልድ መጻሕፍት የውስጥ ገበና ሲገለጥና በእግዚአብሔር ቃል ሲፈተሽ
የተወደዳችሁ እና የተከበራችሁ ይህንን ትምህርት የምትከታተሉ የእግዚአብሔር ወገኖች በሙሉ ባለፈው በምዕራፍ አንድ ትምህርታችን በመጽሐፈ መቃብያን 12 ፥ 3 _ 4 ላይ የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል የሚለውን ሃሳብ አንስተን ሐዋርያው ጳውሎስ ከተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ ጋር ስናስተያየው ፍጹም የተሳሳተና ልናገናኘውም የማንችል መሆኑን ተመልክተናል እግዚአብሔር የሚወዱትን ሳይሆን የወደደው ገና ለእርሱ ጠላቶች የነበርነውን ፣ ኃጢአተኞችን ፣ በአጠቃላይ ዓለሙን ሁሉ እንዲሁ ነው የወደደው እኛም ኃጢአተኞች ስለሆንን እግዚአብሔርን የሚወድ ማንነት እንደሌለንና እግዚአብሔርንም የወደድነው እርሱ በወደደን ፍቅር መሆኑን በዚሁ ምዕራፍ በሰፊው ተመልክተናል በምዕራፍ ሁለት ትምህርታችን ላይም የምንመለከተው አሁም የመቃብያኑ ጸሐፊ ያነሳውን ሃሳብ ተመርኩዘን ነው ይኸው የመቃብያን ጸሐፊ የሚወዱትን ሰዎች ይወዳቸዋል ብሎ አላበቃም ሕጉንም የሚጠብቁትን ሰዎችን እንደ አደራ ገንዘብ ይጠብቃቸዋል በማለት ተናገረ ይህን ማለቱ ጽድቅ ሁሉ ከእግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ከሰውና በሰው በኩል መሆኑን ሊያሳየን ፈልጎ ነው ሰው እግዚአብሔርን ወዶ በእግዚአብሔር የተወደደ ሕጉንም ጠብቆ በእግዚአብሔር በአምላኩ እንደ አደራ ገንዘብ የተጠበቀ መሆኑን ሊያስታውሰን ይፈልጋል መጽሐፍቅዱሳችን ግን እንዲህ አያስተምረንም ምክንያቱም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና ይለናል ስለዚህ ሕግ የእግዚአብሔርን ቁጣ በሰዎች ላይ የሚያመጣ ነው ነገር ግን ሕግ ከሌለ ሕግን የመተላለፍ በደል የለም ሲል ሐዋርያው ተናገረን ሮሜ 4 ፥ 15 በዚህ ቃል መሠረት እንግዲህ ሕጉ ተጠብቆ የዘላለምን ሕይወት ካላመጣና በፈንታውም የእግዚአብሔርን ቁጣ ከቀሰቀሰ ለምን ይሆን ? የመቃብያኑ ጸሐፊ ሕጉን የሚጠብቁትን ሰዎች እንደ አደራ ገንዘብ ይጠብቃቸዋል ማለቱ ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎች እተዋለሁ በመጽሐፍቅዱሳችን ቃል መሠረት ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና ሕግ ሰዎችን የሚያጸድቅ ሳይሆን በደለኛ እና ኃጢአተኛ አድርጎ የሚያጋልጥ ነው ነገር ግን ሕግ ከሌለ ግን ሕግን የመተላለፍ በደል አይኖርም ለዚህ ነው እንግዲህ ሐዋርያው ጳውሎስ የራሱን ሕይወት እንደ ምሳሌ አድርጎ በማቅረብ …………………በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ ያለነቀፋ ነበርኩ ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬዋለሁ ……………ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጉድፍ እቆጥራለሁ በማለት የተናገረን ፊልጵስዩስ 3 ፥ 3 _ 12 ስለዚህ ሕጉን ከመጠበቅ አኳያ እንግዲህ ከጳውሎስ በላይ ምሳሌ የምናደርገው ሰው የለንም ምክንያቱም ጳውሎስ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ ያለነቀፋ ነበርኩ ብሎናልና ነገር ግን ክርስቶስን በማመን ብቻ የሚገኘውን ጽድቅ ለማግኘት ሁሉን ረብ እንደሌለው እንደጉድፍ ቆጠረ ከዚህ የተነሳ መገረዙ ፣ ዕብራዊነቱ ፣ ፈሪሳዊነቱ ፣ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ያለነቀፋ መሆኑ ክርስቶስን በማመን ካገኘው ጽድቅ ጋር ሲመዛዘን ምንም ረብ የሌለው ፋይዳ ቢስ ነው በመሆኑም ጳውሎስን ያልጠቀመ መገረዝ ፣ ዕብራዊነት ፣ ፈሪሳዊነት ፣ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅነት ፣ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅም ያለነቀፋ ነኝ ብሎ መኩራራት ለእኛም አይጠቅመንምና ጳውሎስ እንደጉድፍ የቆጠረውን እነዚህን የዘረዘርናቸውን ነገሮች እኛም እንደ ጉድፍ ቆጥረን ክርስቶስን በማመን ወደሚገኘው ጽድቅ እንምጣ እግዚአብሔርም እንደ አደራ ገንዘብ የሚጠብቃቸው የመቃብያን ጸሐፊ እንደተናገረው ሕጉን የሚጠብቁትን ሳይሆን ክርስቶስን በማመን የሚገኘውን ጽድቅ አምነው የተቀበሉትን ነው ይህንን በተመለከተ እነዚህን ጥቅሶች ያንብቧቸው
ወዝንቱ ውእቱ ፈቃዱ ለአቡየ ከመ ኩሉ
ዘርእዮ ለወልድ ወአምነ ቦቱ ይረክብ
ሕይወተ ዘለዓለም ወአነ አነሥ በደኃሪት ዕለት
ትርጉም ፡-
ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ
የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ
ፈቃድ ይህ ነው እኔም በመጨረሻው ቀን
አስነሳዋለሁ
የዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 40
በጎቼ ድምፄ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ
ይከተሉኝማል እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ
ለዘላለምም አይጠፉም ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም
የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው
ማንም አይችልም እኔና አብ አንድ ነን
የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 27 _ 30
እግዚአብሔር እንግዲህ እንደ አደራ ገንዘብ የሚጠብቃቸው በልጁ በኢየሱስ አምነው የዘላለምን ሕይወት ያገኙትን ነው ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና እንደነዚህ ዓይነቶችን ሰዎች ማለት በልጁ በኢየሱስ ያመንን እኛን ከኢየሱስም ሆነ ከአብ እጅ የሚነጥቀን የለም
እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይገናኘን ደግሞም ይባርከን አሜን
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:
Post a Comment