Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ሃያ አንድ



ቤተክርስቲያን



ክፍል ሃያ አንድ



በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች



የተወደዳችሁ ወገኖች ይህንን ትምህርት በክፍል ሃያ አንድም ላይ አሁን እንቀጥለዋለን እንድትከታተሉት በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ የሚል ቃል ተጻፈልን ገላትያ 2 4 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል ገላትያ 2 16 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ ? አይደለም ተባልን ገላትያ 2 17 በክርስቶስ ስለሆንን በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና የሚል ቃል ተሰጠን ገላትያ 3 26 በክርስቶስ ስለሆንን አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና ተብሎ ታወጀልን ገላትያ 3 28 በክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ በሚል ቃል ወራሽነታችን ተረጋገጠልን ገላትያ 4 7 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና ተብለን በፍቅር የሚሥራ እምነትን ተለማመድን በመለማመድም ላይ እንገኛለን ገላትያ 5 6 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና በሚል ቃል አዲስ ፍጥረት መሆናችንን አምነን እንድንቀበል ተጻፈልን ገላትያ 6 15 በክርስቶስ ስለሆንን በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን ኤፌሶን 1 1 _ 3 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ ሲል ሐዋርያው አስታወቀን ኤፌሶን 1 9 _ 13 በክርስቶስ ስለሆንን ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሲል ሐዋርያው ነገረን ኤፌሶን 1 20 _ 21 በክርስቶስ ስለሆንን በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ኤፌሶን 2 6 _ 7 በክርስቶስ ስለሆንን እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ኤፌሶን 2 10 በክርስቶስ ስለሆንን አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል ተባልንን ኤፌሶን 2 13 በክርስቶስ ስለሆንን ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም ሲል ሐዋርያው ጻፈልን ኤፌሶን 3 5 _ 6 በክርስቶስ ስለሆንን ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘላለም አሳብ ነበረ ሲል ሐዋርያው ተናገረን የቱን እንደሆነ እናንተው ክፍሉን ገልጻችሁ በማንበብ መረዳት ትችላላችሁ ኤፌሶን 3 11 በክርስቶስ ስለሆንን እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው  ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ኤፌሶን 3 20 እና  21 በክርስቶስ ስለሆንን እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ የሚል መልዕክት ተሰጠን ኤፌሶን 4 32 በክርስቶስ ስለሆንን ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም ሲል ሐዋርያው ተናገረን ኤፌሶን 5 5 በክርስቶስ ስለሆንን ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ የሚል ቃል ተላለፈልን ኤፌሶን 5 21 በክርስቶስ ስለሆንን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ ካለ በኋላ አለፍ ብሎ ቁጥር 8 ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁን እንዴት እንድናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና ሲል ሐዋርያው የእግዚአብሔርን ምስክርነት ጠርቶ ናፍቆቱን ገለጠልን ፊልጵስዩስ 1 1 8 በክርስቶስ ስለሆንን ይህንንም ተረድቼ፥ በእናንተ ዘንድ እንደ ገና ስለ መሆኔ፥ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ አለን ፊልጵስዩስ 1 25 እና 26 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ  ሲል ገለጸልን ፊልጵስዩስ 2 1 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን አለን ፊልጵስዩስ 2 5 በክርስቶስ ስለሆንን በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ስለዚህም በከንቱ እንዳልሮጥሁ በከንቱም እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል ሲል ሐዋርያው ተናገረን ፊልጵስዩስ  2 16 በክርስቶስ ስለሆንን እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና ሲል ተናገረን ፊልጵስዩስ 3 3 በክርስቶስ ስለሆንን አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ ሲል ሐዋርያው በክርስቶስ የደረሰበትን መረዳት በግልጽ አስታወቀን ፊልጵስዩስ 3 8 እና 9 በክርስቶስ ስለሆንን አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ ወንድሞች ሆይ እኔ ገና እንዳልያዝኩት እቆጥራለሁ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ ሲል ለእድገት መዘርጋቱንና መፍጠኑንም ገለጸልን ፊልጵስዩስ 3 12 _ 14 በክርስቶስ ስለሆንን አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል አለን ፊልጵስዩስ 4 7 በክርስቶስ ስለሆንን ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ በማለት በክርስቶስ ሁሉን የመቻልን ሁኔታ ገለጸልን ፊልጵስዩስ 4 13 በክርስቶስ ስለሆንን አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል የሚል ቃል ተሰጠን ፊልጵስዩስ 4 19 በክርስቶስ ስለሆንን ለቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምታ አቅርቡ ከእኔ ጋር ያሉቱ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል በማለት የቅዱሳንን ሰላምታ አመጣልን ፊልጵስዩስ 4 21 ወገኖቼ በክርስቶስ የመሆንን ጥቅም  በዚህ የምናበቃ አንሆንም በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንቀጥለዋለን እስከዚያው ደህና ሁኑ


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment