Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ሃያ ስድስት



ቤተክርስቲያን


ክፍል ሃያ ስድስት


ለክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጥብቃ ታስተምራለች



እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሔርን
ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው

   ሮሜ 14 18

እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ የሚለውን ሃሳብ በእንግሊዘኛው እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገለግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው ይለናል ክርስቶስን የሚያገለግል ሰው ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው ነውር የሌለው ሕሊና ወይም ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው መትጋት አለበት በሐዋርያት ሥራ 24   16 ላይ ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ አለ በሐዋርያት ሥራ 23 1 ላይ ደግሞ ጳውሎስም ሸንጎውን ትኵር ብሎ ተመልክቶ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ አለ ነውር የሌለባት ሕሊና መልካም ሕሊና የሚሉት ሃሳቦች የሚያመለክቱት ንጹሕ ሕሊናን ነው በመሆኑም ጳውሎስ ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረኝ እተጋለሁ ማለቱ ነው  መልካም ሕሊና ወይም ንጹሕ ሕሊና ያለው ሰው በጌታም ሆነ በሰው ፊት መልካም የሆነውን የሚያስብ ነው በ2ኛ ቆሮንቶስ 8 21 ላይ በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና ይለናል ሕሊና አስተሳሰብን የሚመለከት ነገር ነው ሰው ማነው ? ስንል ሃሳቡ እንደሆነ መጽሐፍቅዱስ ይናገራል በመጽሐፈ ምሳሌ 23 7 ላይ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም ይለናል ስለዚህ ሰው ውጪያዊ ማንነቱ የቁመቱ ማጠርና መርዘም የመልኩ መጥቆርና መቅላት የመሣሠሉት ሳይሆን መጽሐፉ  በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና ብሎ ስለነገረን ሰው ማለት ውጪያዊ ማንነቱ ሳይሆን ሃሳቡ ነው ሃሳብ ደግሞ ከሰው አዕምሮ ውስጥ የሚፈልቅና የሚወጣ በመሆኑ የልብና የአዕምሮ እንዲሁም የፈቃድ ተሳትፎ ያለበት ነው ታድያ የሰው ፈቃድ ያለው በሰው አዕምሮ ውስጥ ነው ሰው ከመጀመርያ ሲፈጠር በነፃ ፈቃድ የተፈጠረ ፍጥረት ነው ማለት ማንኛውንም ነገር ሊያደርግ ነፃ ፈቃድ አለው እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ትዕዛዝ ነው የሰጠው እንጂ ነፃ ፈቃዱን አልተጫነውም ወይም  አልከለከለውም ስለዚህ ሰው ኃጢአት ሲሰራ በራሱ ወስኖና ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ነው ኃጢአት የሰራው በዘፍጥረት 1 26 ላይ እግዚአብሔር ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ሲል ሰው እግዚአብሔርን የሚመስልበት ማንነቱን አስተሳሰቡን ሊጠቁመን ፈልጎ ነው እግዚአብሔር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ሰውን እንፍጠር ሲል እንግዲህ የሰውን ጥሩ የሆነ ምግባርንና መልካም ጠባይን የሚያመለክት ነው እያልን ነው በእንግሊዘኛው እንዲህ ይለዋል The image God is talking about is His moral character , and we were created for the purpose of displaying his moral character.  ስለዚህ ሰው በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ በመፈጠሩ  እንደ እግዚአብሔር እንዲያስብ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መልካም ባሕርይ ወይም ሥነምግባር የእግዚአብሔርን ጠባይ እንዲያሳይ ሆኖ በዓላማ የተፈጠረ ነው ታድያ ሰይጣን መጥቶ ይህንን መልክ ነው ያበላሸው ሰው እግዚአብሔርን እንዲመስል ሆኖ የተፈጠረበትን መልክ ለማበላሸት ሰይጣን ከመጀመርያ ነፍሰ ገዳይና የሐሰት አባት ስለነበረ  በመጀመርያ በአዳም ላይ መንፈሳዊ ሞትን አመጣበት ማለት ከእግዚአብሔር ለየው እግዚአብሔርም እርሱን እንዲመስል የሰጠውን መልክና ምሳሌ አበላሸበት በመሆኑም ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበት ትልቁ ዓላማ ይህን ሰይጣን ያመጣብንን ሞት በሕይወት ሊለውጥልን እንደገናም እግዚአብሔር የሰጠንንም መልክ ሊመልስልን ነው ለዚህ ነው መጽሐፍቅዱሳችን በ1ኛ ዮሐንስ 5 11 _ 12 ላይ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም ሲል የጻፈልን መልክንም በተመለከተ በሮሜ 8 29 ላይ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና አለን ስለዚህ ኢየሱስን ልንመስል ዛሬ ወይንም በዓመታትና በዘመናት ውስጥ ሳይሆን አስቀድመን ተወስነናል  ሊመስል የተወሰነ ሰው ደግሞ እርሱ ሲገለጥ እርሱን እንዲመስል ያውቃል በ1ኛ ዮሐንስ 3 2 ላይ ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን ያለን ለዚህ ነው በመሆኑም ለክርስቶስ ለመሆን በንጹሕ ሕሊናም ክርስቶስን ለማገልገል የእግዚአብሔር እውቀት ያስፈልገናል ንጹሕ ሕሊና እኔ ንጹሕ ነኝ ክፉ ነገር እኮ አላስብም በማለት የሚመጣ ነገር አይደለም እኔ ንጹሕ ነኝ ክፉ ነገር አላስብም ብንልም እናስባለን ለምን ስንል አንዳንዶቻችን የሚለውጠውን ጌታ ገና አላገኘንምና ፍጥረታዊ ማንነት ያለን ፍጥረታዊ ሰው ነን ለፍጥረታዊ ሰው ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም ይለናል 1 ቆሮንቶስ 2 14 አንዳንዶቻችን ደግሞ ጌታን የተቀበልንና ጌታን ያገኘን ቢሆንም አዳማዊው ተፈጥሮና የአሮጌው ሰው ማንነት ውስጣችን ስላለ የሥጋን ሥራ ከኢየሱስ ጋር መስቀል በማንችልበትና በመንፈስ መመላለስም በሚያቅተን ጊዜ የሥጋን ምኞት እንፈጽማለን መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም ካለ በኋላ አያይዞም በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ እርስ በእርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ ይለናል ገላትያ 5 ፥ 16 _ 26 ጌታን ያልተቀበልን ሰዎች ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ከፍጥረታዊ ማንነት እንወጣለን ጌታን ተቀብለን በመንፈስ መመላለስ የሚያቅተን ሰዎች ደግሞ የሥጋንም ምኞት ከቶ እንዳንፈጽም የምንሆነው አንድ የእግዚአብሔር እውቀት ሲገባንና ለዚያም እውነት መኖር ስንጀምር ነው እርሱም ምንድነው በሮሜ 6 6 ላይ  ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቆአልና ይለናል ስለዚህ አሮጌው ማንነቱ ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ያወቀ ሰው ለአሮጌው ማንነቱ ቦታ አይሰጥም እንደውም አሮጌው ማንነቴ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎአል በማለት ይህንን የአሮጌው ሰው ማንነት መሞትን ዕለት ዕለት ያውጃል ሲያስፈልግም ደግሞ ይህ ሰው የኢየሱስ ነውና የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ ስለሚል ከኢየሱስ ጋር ሊሆን ሥጋውን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ይሰቅላል ገላትያ 5 24 ያኔ ነው እንግዲህ እንደ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ማለት የሚችለው ከክርስቶስ ጋር የተሰቀለና ለሥጋ መሻቱና ምኞቱ ሕያው ሆኖ የማይኖር ክርስቶስም በውስጡ የሚኖር ሰው እርሱ በመንፈስ የሚመላለስ ሰው ነው ታድያ ወደዚህ የእውነት ኃይል የምንመጣው ከላይ እንደገለጽኩት የእግዚአብሔር እውቀት ሲኖረን ነው በእግዚአብሔር እውቀት ከፍ ያለው የሰው ሃሳብ ይፈርሳል አዕምሮአችን ማለት ፈቃዳችንን የያዘው የውስጠኛው አስተሳሰባችን ለክርስቶስ ሊታዘዝ ለክርስቶስ ይማረካል 2 ቆሮንቶስ 10 5 ሃሳባችን ተስተካክሎና ተፈውሶ ንጹሕም ሆኖ ለክርስቶስ ብቻ ታጭተን ለክርስቶስ እንሆናለን 1 ቆሮንቶስ 11 2  እና  3  ክርስቶስም ቤተክርስቲያንን በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ እራሱን አሳልፎ ስለ ሰጠ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ ይለናል ኤፌሶን 5 27 ከዚህ የተነሳ ክርስቶስ የሚፈልጋት ቤተክርስቲያን የበጉን ሠርግ የምትጠብቅ ቤተክርስቲያን ናትና እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ በሁሉም ነገር ራሷን ያዘጋጀች መሆን ይጠበቅባታል ራዕይ 19 7 እና 8 የእግዚአብሔር ቃል እውነት የሚያስተምረን እንግዲህ ይህንን ነው ለዚህም ነው በፊልጵስዩስ 1 27 ላይ ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ የሚለን በፊልጵስዩስ 1 9 _ 11 ድረስ ደግሞ ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ ይለናል ለክርስቶስ ተዘጋጅቶ ለመድረስ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አስፈላጊዎች ናቸው እኛ ደግሞ ተዘጋጆች ብቻ ሳንሆን አዘጋጅ አገልጋዮችም ስለሆንን ክርስቶስን ስናገለግል በመልካም ሕሊና ወይም በንጹሕ ሕሊና በሚሆንበት ጊዜ እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ይሆናል ንጹሕ ሕሊና ቅንና አለነውር የሆነ ሕሊና ስለሆነ የሚሻለውን ፈትኖ ያወቀ በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን የሚያስብ ስለሆነ በፍቅር ይመላለሳል ስለዚህ በሚበላው ምግብ ወንድሙን አያሳዝንም ክርስቶስ የሞተለትን ወንድም በመብል አያጠፋውም ይጠነቀቅለታል  መልካም ሕሊና ከፍርድ ነፃ የሆነ ሰዎችን ሁሉ ለማገልገልና ለመጥቀም እግዚአብሔርንም ለማስደሰት የተነሳ በመሆኑ ሁልጊዜ የክርስቶስ አዕምሮ ያለው ነው በ1ኛ ቆሮንቶስ 2 16 ላይ እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው ? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን ይለናል የእንግሊዝኛው መጽሐፍቅዱስ የክርስቶስ አዕምሮ አለን ነው የሚለው የክርስቶስ አዕምሮ ያለው ደግሞ የክርስቶስ ሃሳብ ያለው ሰው ማለት ነው በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ ሃሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን የሚል ነው ፊልጵስዩስ 2 7 በክርስቶስ የነበረ ሃሳብ በእኛ ዘንድ ሲሆንና የክርስቶስ አዕምሮ ሲኖረን እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ ስለሚል ቃሉ ክርስቶስ እኛን በጠቀመበት መጥቀም እኛም እንደ ጳውሎስ ሌሎችን ስንጠቅም እንገኛለን 1 ቆሮንቶስ 9 12 _ 23 የተጻፈውን ክፍል እናንብብ ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ቃል ይባርከን አሜን


እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል
እያንዳንዳችን እንድናንጸው እርሱን ለመጥቀም ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ ክርስቶስ ራሱን ደስ
አላሰኘምና፤ ነገር ግን አንተን የነቀፉበት ነቀፋ ወደቀብኝ ተብሎ እንደ ተጻፈ ሆነበት

ሮሜ 15 1 _ 4


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment