ግጥም
ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ
ዓይኖችሕም መንገዴን ይውደዱ
ምሳሌ 23 ፥ 26
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ
የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና
ምሳሌ 4 ፥ 23
ትንቢተ ኢሳይያስ
61፥1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ዓይኖቻችን ሳሉ የምድር ከርታታ
ተስፋችን ተካቶ ሆኖ መንታ መንታ
ሕይወታችን ሲታይ በሰዎች እርዳታ
የተሟላ መስሎን ነገር በዚህ ዓለም
ስንኖር በተድላ ሁሉን በማጣጣም
ከምቾቶቻችን የሚነቀንቀን
ሳናስብ ይመጣል ጎትቶ ሊጥለን
ተስፋ ያደረግናቸው ከንቱ ይሆናሉ
ምኞት ናፍቆት ብቻ ሆነው ይቀራሉ
የተስፋ ጉም ዘግነን ጨብጠን በመቅረት
ትካዜና ሃዘን ሰቆቃና ምሬት
ኑሮአችንን ከበው ሲያመሰቃቅሉት
ሁሉም ነገር አሁን ግራ ይሆንና
የተስፋ ጭላንጭል ላይታይ ደመና
ሕይወት ተዳፍኖብን ከንቱ ሆኖ ይቀራል
ዕልባት መቋጫ መፍትሔውን ያጣል
ይህን ሁሉ ችግር ከወዲሁ የሚያውቅ
ሕያው እግዚአብሔር የነፍሳችን መልሕቅ
ስጡኝ አትከልክሉኝ ልባችሑን ይላል
የሕይወት መውጫችሑ በዚያ ተወስኖአል
እኛ ግን በአንጻሩ ለጌታ የምንሰጠው
ነገር ባበቃ ዕለት በዚያ በጨለማው
ተስፋችን ተሟጦ ጠፍቶ መደምደምያው
ተሰብሮና ዝሎ ልባችን ወድቆ ነው
ያም ቢሆን ለጌታ ምንም አይገደውም
የተሰበረን ልብ ጠግኖ ለማከም
ለአልቃሾች ደስታ ዘይትን ያፈሳል
አፋችንን በሳቅ በዕልልታ ይሞላል
ወይትባረክ እግዚአብሔር
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ
ዓይኖችሕም መንገዴን ይውደዱ
ምሳሌ 23 ፥ 26
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ
የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና
ምሳሌ 4 ፥ 23
ትንቢተ ኢሳይያስ
61፥1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ዓይኖቻችን ሳሉ የምድር ከርታታ
ተስፋችን ተካቶ ሆኖ መንታ መንታ
ሕይወታችን ሲታይ በሰዎች እርዳታ
የተሟላ መስሎን ነገር በዚህ ዓለም
ስንኖር በተድላ ሁሉን በማጣጣም
ከምቾቶቻችን የሚነቀንቀን
ሳናስብ ይመጣል ጎትቶ ሊጥለን
ተስፋ ያደረግናቸው ከንቱ ይሆናሉ
ምኞት ናፍቆት ብቻ ሆነው ይቀራሉ
የተስፋ ጉም ዘግነን ጨብጠን በመቅረት
ትካዜና ሃዘን ሰቆቃና ምሬት
ኑሮአችንን ከበው ሲያመሰቃቅሉት
ሁሉም ነገር አሁን ግራ ይሆንና
የተስፋ ጭላንጭል ላይታይ ደመና
ሕይወት ተዳፍኖብን ከንቱ ሆኖ ይቀራል
ዕልባት መቋጫ መፍትሔውን ያጣል
ይህን ሁሉ ችግር ከወዲሁ የሚያውቅ
ሕያው እግዚአብሔር የነፍሳችን መልሕቅ
ስጡኝ አትከልክሉኝ ልባችሑን ይላል
የሕይወት መውጫችሑ በዚያ ተወስኖአል
እኛ ግን በአንጻሩ ለጌታ የምንሰጠው
ነገር ባበቃ ዕለት በዚያ በጨለማው
ተስፋችን ተሟጦ ጠፍቶ መደምደምያው
ተሰብሮና ዝሎ ልባችን ወድቆ ነው
ያም ቢሆን ለጌታ ምንም አይገደውም
የተሰበረን ልብ ጠግኖ ለማከም
ለአልቃሾች ደስታ ዘይትን ያፈሳል
አፋችንን በሳቅ በዕልልታ ይሞላል
ወይትባረክ እግዚአብሔር
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment