Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል አስራ ዘጠኝ



ቤተክርስቲያን


ክፍል አስራ ዘጠኝ


እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር
እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ

ገላትያ 3 29


አሁንም በዚህ በክፍል አስራ ዘጠኝ ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው የክርስቶስ መሆንን ነው የክርስቶስ ብቻ እንጂ የማንም ስላልሆንን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን በዚህ በገላትያ 3 29 ላይ እናንተስ የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ በማለት  የክርስቶስ ልንሆን የተነሳንበትን መነሻ ሃሳቦች በዝርዝር ያቀርባል መጽሐፉ አብርሃምን የአብርሃምን ዘር እና የተስፋውን ቃል ያነሳል ዛሬ የምንመለከተው ይኸው የገላትያ የመጽሐፍ ያነሳቸውን አብርሃምን የአብርሃምን ዘር እና የተስፋውን ቃል ይሆናል እነዚህ ሦስት ዋና ዋና ሃሳቦች ለክፍሉ ተያያዥና ቁልፍ የሆኑ ሃሳቦች ስለሆኑ በእነዚህ ሃሳቦች ላይ ትምህርታችንን እናጠነጥናለን በመጀመርያ የምንመለከተው አብርሃምን ነው መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃምን የአባቶች አለቃ በግዕዙ ቃል ርእሰ አበው ይለዋል በእንግሊዘኛው Abraham the Patriarch  የሚለውን ቃል ይዟል ዕብራውያን 7 4 አብርሃም ለጥንታውያን እስራኤል የመጀመርያውና ትልቅ አባት ታማኝ ለሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የመጀመርያ ተምሳሊታቸው ነው አብርሃም ብዜት ያላቸው የብዙሃን አባት ነው እንደገናም በምሳሌነት የምናነሳው ባለማዕረግ አባት ነው በኒው ኢሉስትሬትድ ባይብል ዲክሺነሪ ላይ በሚገባ ይገልጸዋል ABRAHAM father of a multitude originally Abram (exalted father ) – the first great PATRIARCH of ancient Israel and a primary model of faithfulness for Christianity. The accounts about Abraham are found in Genesis 11 : 26_________ 25 : 11, with the bibilical writer focusing on four important aspects of his life ( New Alustrated Bible Dictionary ) አብርሃም ዕብራዊ ተብሎ በመጠራት በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ የመጀመርያው ሰው በመሆኑ  በዘፍጥረት 14 13 ላይ አንድ የሸሸ ሰው መጣ ለዕብራዊው ለአብርሃምም ነገረው እያለ ይቀጥል እና ይኸው ዲክሺነሪ Summary ሲያደርገው እንዲህ ይለዋል Abraham was the father of the Hebrews and the prime example of a righteous man ይለዋል  ስለዚህ በይስሐቅና በያዕቆብ በኩል ያሉት የልጅ ልጆቹ  ደግሞ ዕብራውያን መሆናቸውን ያውቃሉ ይኸውም በዘፍጥረት 39 ፥ 17 ላይ  ይህንንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው ያገባህልን እብራዊ ባርያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ እኔም ድምጼን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ በማለት የጶጢፋራ ሚስት መናገሯን እንመለከታለን በዘፍጥረት 40 14 እና 15 ላይ የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ስንመለከት ደግሞ ሕልሙን ለፈታለት ሰው ዮሴፍ የተናገረውን እናያለን ነገር ግን በጎ በተደረገልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርኦን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ እኔን ከዕብራውያን ሀገር ሰርቀው አምጥተውኛልና ከዚህም ደግሞ በግዞት ቤት ያኖሩኝ ዘንድ ምንም አላደረግሁም በማለት ይናገራል በዘፍጥረት 43 32 እና 33 ላይ  ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፥ ለእነርሱም ለብቻቸው፥ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና በፊቱም በኵሩ እንደ ታላቅነቱ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ ተቀመጡ ሰዎቹም እርስ በርሳቸው ተደነቁ ይለናል  እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው የመጀመርያው ቃልኪዳን ወደ ይስሐቅና ወደ ልጅ ልጁ ወደ ያዕቆብ ተላልፎአል ዘፍጥረት 26 3 ዘፍጥረት 28 13 ዘፍጥረት 35 11 _ 12  ቆይቶም የመጽሐፍቅዱስ ሪፈረንስ አዘውትሮ እንደሚገልጽልን የእስራኤል እግዚአብሔር የአብርሃም እግዚአብሔር መሆኑን ነው በእንግሊዝኛው ዲክሺነሪ አሁንም እንዲህ ይላል In later biblical references the God of Israel is frequently identified as the God of Abraham and Israel is often called the people « of the God of Abraham » በዘፍጥረት 26 ፥ 24  ላይ ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ  በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ በማለት ለይስሐቅ እግዚአብሔር ተስፋ ሲሰጠው እንመለከታለን እስራኤልም ሁልጊዜ የሚጠሩት የአብርሃም እግዚአብሔር ሕዝቦች ተብለው ነው በመዝሙር 47 9 ላይ የምድር ኃይለኞች ለእግዚአብሔር ናቸውና የአሕዛብ አለቆች ወደ አብርሃም አምላክ ተሰበሰቡ እርሱንም ከፍ ከፍ አደረጉት ይለናል እንደገናም በመዝሙር 105 6 ላይ ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ በማለት ይናገራል  የእግዚአብሔር ሕዝቦች ችግርና ሁከት ውስጥ በነበሩ ጊዜ በእግዚአብሔር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ አብርሃም ጠቃሚ የሆነ ቅርጽንና መልክን የሚሰጥ ሰው ነበር እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባውን ቃልኪዳን እንዲያስታውስ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ይግባኝ ይሉ ነበር ሕዝቅኤል 32 13 ዘዳግም 9 27 መዝሙር 105 9 እነዚህ ጥቅሶች የሚያስታውሱን ይህንኑ እውነት ነውና የክፍሉን ጥቅሶች ከመጽሐፍቅዱሳችሁ እያወጣችሁ አንብቧቸው ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ከላይ በጅማሬ መግቢያ ላይ ባብራራነው ሃሳብ መሠረት አብርሃም የመጀመርያውና ትልቁም አባት የተባለው ለጥንታውያኑ እስራኤል ብቻ ሳይሆን ታማኝ ሆነው የእርሱን እምነት ለጠየቁና አምነውም ለተከተሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ትልቅ የእምነት አባትና ምሳሌ ነው ለዚህም ነው መጽሐፍቅዱሳችን በሮሜ 4 11 ላይ ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው ይለዋል ለተገረዙት ሲል አይሁድን ያመለክታል ላልተገረዙት ሲል አሕዛብን ያመለክታል ስለዚህ አብርሃም ጻድቅ የተባለው ከተገረዘ በኋላ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው ከመገረዙ አስራ አራት ዓመት አስቀድሞ ጻድቅ ተባለ ዘፍጥረት 17 እንመልከት ለዚህም ነው በዘፍጥረት 15 6 ላይ አብራምም በእግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት የሚለን በገላትያ 3 16 ላይ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ  ስለ ብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ ካለን በኋላ ይህንም እላለሁ፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ታድያ ይህ በእምነት በኩል የክርስቶስ የምንሆንበት እንደ ተስፋው ቃልም ወራሽ ሆነን የምንቀርበት የተስፋ ቃል አብርሃምና ዘሮቹ ጋር አልቀረም ዛሬ ላይ እኛን የክርስቶስ አማኞችን ብቻ ሳይሆን የሰውን ፍጥረት ሁሉ ጎሳ ነገድ ዘር ባርያ ጨዋ ሃብታም ደሃ ሴት ወንድ ሳይል ሁሉን የክርስቶስ ሊያደርግ  ይኸው በዘመናችንም ይነገራል እንደገናም ይህ የተስፋ ቃል ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በፊት የተሰጠ በመሆኑ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠው  ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም  ማለት በክርስቶስ በሆነው እምነት ብቻ ሊያጸድቅ ደግሞም ሊያወርስ የተረጋገጠ ስለሆነ የተረጋገጠልን በማመን ብቻ የሆነውን ጽድቅ ስላገኘን ክብርን ለእግዚአብሔር እናመጣለን በመሆኑም  ይህንን የተረጋገጠውን እግዚአብሔርም አምኖበት ያረጋገጠውን ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በፊት የመጣው ሕጉ የሚሽረው አይሆንምና  ለሰው ልጆች ሁሉ የሚያዋጣው  ትልቁ ነገር እግዚአብሔር አምኖ ባረጋገጠው ከእምነት በሆነ ጽድቅ አምኖ መዳን ወይንም መጽደቅ ብቻ ነው በመሆኑም እስራኤል አብርሃም አምኖ በዳነበት ጽድቅ አምነው መዳን ሲችሉ አብርሃም አባት አለን ብለው በመመካትና ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በፊት በተሰጠው ሕግን የመጠበቅ ሕይወት ቀሩ ስለዚህ በገላትያ መጽሐፍ ምዕራፍ 3 6 _ 9 ላይ እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ ካለን በኋላ ስለ ሕጉ ሲናገር ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው የሚል ቃል ተጽፎልን እናገኛለን እንደገናም በገላትያ 3 23 _ 29 ላይ እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ ይለናል በክርስቶስ ሆኖ የመጣልን እምነት ከሕግ በታች ተዘግተን እንጠበቅ ከነበረው ሕይወት አውጥቶናል ስለዚህ ሕግ በአሁኑ ሰዓት ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን እንጂ አውራሻችንና አጽዳቂያችን አይደለም እንግዲህ ይህን የእግዚአብሔርን የቃሉን እውነት በዚህ መልኩ ካወቅን ሞግዚት ከሆነን ሕግ ወጥተን ሊያጽድቀን ወደሚችለው አዳኛችን ወደሆነው ወደ ክርስቶስ እንምጣ መጽሐፍ አሁንም በገላትያ 3 10 _ 12 ላይ ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ በማለት ተናገረ የሕግ ሥራ ከእርግማን በታች አደረገን እንጂ የሚያጸድቀን አልሆነም ኢየሱስ ግን በእንጨት ተሰቅሎ ከሕግ እርግማን ዋጀን እንደገናም ሕግ ኃጢአትን የሚገልጥ በመሆኑ ቁጣን አስከትሏል ሮሜ 7 7 _ 11  በመሆኑም እንዲሁ በከንቱ አብርሃም የጸደቀበትን እምነት ሳይዙ አብርሃም አባት አለን ማለት እንደገናም የኃጢአት ባርያ ሆኖ በሕግ ባርነት እና ቁጣ ውስጥም ተቀምጦ እኛ የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ባርያዎች አልሆንም ማለት ከእውነት የራቀ ሐሰት ነው ለዚህም ነው መጽሐፉ ሳይደብቀን እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ  የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ  ሲል የተናገረው የማቴዎስ ወንጌል 3 8 ዮሐንስ ወንጌል 8   31 _ 38  የአብርሃም ዘር በመሆን አብርሃምም አባት አለን በማለት አርነት አይገኝም አርነት የሚሰጥ ከኃጢአት ባርነትም የሚፈታ ልጁ ኢየሱስ ብቻ ነው ለዚህም ነው ጌታችን ኢየሱስ በወንጌሉ ላይ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ በማለት የተናገረው ለአይሁድም ሲመልስላቸው እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም አብርሃም አባት አለን ማለትን አትጀምሩ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንዲችል እላችኋለሁና ሲል የተናገራቸው የሉቃስ ወንጌል 3 8 አያይዞም አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል አላቸው ሕዝቡም እንግዲህ ምን እናድርግ ?  ብለው ይጠይቁት ነበር ይለናል የሉቃስ ወንጌል 3 9 እና 10 እንመልከት ወገኖቼ እንግዲህ ለእኛም ዛሬ የሚጠቅመን አብርሃም አባት አለኝ የአብርሃም ዘር ነኝ ለአንድም ስንኳ ባርያ አልሆንኩም ማለት ሳይሆን በተናጠልም ይሁን በኅብረት እንግዲህ ምን እናድርግ ወይም ምን ላድርግ ሲሉ ጌታን መጠየቁ አማራጭ የሌለው ነገር ነው ጌታም ለዚህ ሙሉ የሆነ መልስን ሰጥቷል አርነት የወጣ በእርግጥም የክርስቶስ ይሆናልና እንደገናም የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋው ቃል ወራሽ ወደ መሆን ይመጣልና ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ አለ ወገኖቼ ሙሉ የሆነ አርነትን ሊሰጠን የታመነው ጌታ ኢየሱስ ያድናል የሚሰማ ሁሉ አዎንና አሜን ይበል ኢየሱስ ትላንትናን አድኗል ዛሬም ለዘላለም እስከ መጨረሻው ያድናል

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ጌታ ይባርካችሁ

No comments:

Post a Comment