Friday, 5 December 2014

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምዕራፍ ሁለት ክፍል ስምንት የሕዝቡ እውነተኛን ነገር መጥላት



የቤተክርስቲያን ተልዕኮ


ምዕራፍ ሁለት



ክፍል ስምንት


የሕዝቡ እውነተኛን ነገር መጥላት



የእግዚአብሔር ሕዝብ እውነተኛን ነገር በሚጠላበት ጊዜ ለሐሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎች የተጋለጠ ይሆናል በትንቢተ ኢሳይያስ 30 10 ላይ በተለይ አዲሱ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም ግልጽ አድርጎ ያብራራዋልና አዲሱን ትርጉም ሄደን እንመልከት አሁንም ሂድ በሰሌዳ ላይ ጻፍላቸው በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ክተብላቸው ለሚመጡትም ዘመናት ለዘላለም ምስክር ይሆናል እነዚህም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው ባለ ራዕዮችን ከእንግዲህ ራዕይን አትዩ ይላሉ እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን ደስ የሚያሰኘውን ንገሩን የሚያማልለውን ተንብዩልን ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ ከጎዳናውም ራቁ ከእስራኤል ቅዱስ ጋር ፊት ለፊት አታጋጥሙን የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ሄደን ስንመለከት እግዚአብሔር ሁልጊዜ እውነተኛ ነው ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገረውን እውነተኛም የሆነውን ነገር ይናገራል ለዚህም ነው ለኤርምያስ አሁንም ሂድ በሰሌዳ ላይ ጻፍላቸው በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ክተብላቸው ለሚመጡትም ዘመናት ለዘላለም ምስክር ይሆናል ያለው በመዝሙር 33 11 እንደገናም በመዝሙር 100 5 የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና እንደገናም በመዝሙር 89 34 ላይ ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም ሲል ተናግሯል ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ሰው የሃሳብ መለዋወጥ አያደርግም ማለት ሃሳቡን አይቀይርም  ያለውን ይፈጽማል እንደተናገረም እንዲሁ ያደርጋል ትንቢተ ኢሳይያስ 46 8 _ 11 ትንቢተ ዳንኤል 4 34 _ 36 የተጻፈውን ክፍል እንመልከት ከዚህ የተነሳ  በሮሜ 3 4 ላይ እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን ይለናል እኛም የእግዚአብሔር ባሮች ልንናገር የሚገባን እንደ እግዚአብሔር ቃል ነው የእግዚአብሔርንም ቃል እየተጠነቀቅን ማድረግ እንደሚገባን ቃሉ ይነግረናል ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን ይለናል 1 ጴጥሮስ 4 11 እንደገናም በ2ኛ ጴጥሮስ 1 19 ደግሞ ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ እያለ ይነግረናል አንዳንዱ ሰው ግን የእግዚአብሔርን እውነት ከመጥላት የተነሳ አፉን አውጥቶ የሚቃወምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል አልቀበል ብሎ ይቃወም እንጂ የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለምና እግዚአብሔር ቃሉን አይሽርም የዮሐንስ ወንጌል 10 35 በመጽሐፍቅዱሳችን ላይ ሰዎች ለሕይወታቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሲፈልጉ ወደ ባለራዕይ እንደሚሄዱ ቃሉ ይናገራል በ1ኛ ሳሙኤል 9 9 ላይ ዛሬ ነቢይ የሚባለው ቀድሞ ባለ ራእይ ይባል ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ ኑ፥ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር ይለናል በመሆኑም እነ ሳኦል ወደ ወደ ሳሙኤል ከመምጣታቸው በፊት የሳኦልን ነገር ለሳሙኤል እግዚአብሔር ገልጦለት ነበር ገናም ሳኦል ሳይመጣ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ ብሎ ገልጦለት ነበር ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እሰዽልሃለሁ ልቅሶአቸው ወደ እኔ የደረስ ሕዝቤን ተመልክቻለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል ሳሙኤልም ሳኦልን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር፦ የነገርሁህ ሰው እነሆ እርሱም በሕዝቤ ላይ ይሠለጥናል አለው ይለናል ታድያ ሳሙኤል የሳኦልን ነገር እግዚአብሔር ገልጦልኛልና ሲል በቀጥታ  ወደ መርፈቅያው ወስዶ እግዚአብሔር ንጉስ ነህ ብሎሃል ብሎ ሲቀባው አናይም ያደረገው ነገር  ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ ካዘጋጀለት በኋላ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ ተነሣና ላሰናብትሕ አለው ሳኦልም ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ እነርሱም በከተማይቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፦ ብላቴናውን ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው አንተ ግን የእግዚአብሔርን ቃል አሰማህ ዘንድ በዚህ ቁም አለው ብላቴናውም አለፈ ይለናል 1 ሳሙኤል 9 16 _ 27 እውነተኛ ባለ ራዕይና ነቢይ በምንሆንበት ጊዜ ለሰማነው ድምጽ ወይም መገለጥ የእግዚአብሔርን ቃል በማረጋገጫነት እንናገራለን የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው መገለጥ ባዶ የሆነ ወይም ከሥጋ አለበለዚያም ከሰይጣን የሆነ መገለጥ ነውና ዋጋ የለውም መገለጣችንም ሆነ ለሰዎች የምናስተላልፈው ፈውስ  የእግዚአብሔርን ቃል ምስክር ያደረገ በእግዚአብሔርም ቃል የተረጋገጠ ሊሆን ይገባል የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው መገለጥ ግን ሰዎች ቢወዱትና ሊሰሙትም ጓጉተው ዕልልታና ውዳሴ ሳይቀር ቢሰጡትም እግዚአብሔር ወደሚፈልገው ፍጻሜ ላይ አይደርሱበትም ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት የሚያጋጥማቸውና ሊስተካከሉም ከሆነ የሚያስተካክላቸው ሊባረኩም ከሆነ ወደ በረከቱ ሙላት የሚያስገባቸው ፍላጎታቸውን ብቻ ሊያሟላላቸው የመጣ የሰዎች መገለጥ ሳይሆን ከእውነተኛው መገለጥ መልስ እውነተኛውን መገለጥ የሚያረጋግጥላቸው የእግዚአብሔር ቃል ነው ምክንያቱም የምንሆነው የእግዚአብሔር ቃል ትሆናላችሁ ያለንን ነው ሰዎች  በመገለጥ  የሚያገለግሉ ስለሆኑ ወይም መገለጥ ስላላቸው ትሆናላችሁ ያሉንን አይደለም ንጉስ ሳኦልም የእግዚአብሔር ቃል ያለውን ነው የሆነው በመጨረሻም የእግዚአብሔርን ቃል ስለናቀ እግዚአብሔርም ንጉስ እንዳይሆን ናቀው ታድያ የእግዚአብሔር ቃል ያለንን እንድንሆን እግዚአብሔር በቃሉ የሚለንን እንስማ ማገልገል ማሰማትም  የምንፈልግ ሰዎች ካለን እግዚአብሔር በቃሉ ሊል የፈለገውን ሳንጨምር ሳንቀንስ እንደ ሳሙኤል መስማት ለሚገባቸው ሰዎች ሁሉ እናሰማ ሰዎችን ሳያደናግር በትክክለኛ መንገድ ላይ ሄደው እግዚአብሔር ወደላው ቦታ በትክክል የሚያደርሳቸው የእኛ መገለጥ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ የምናሰማው የእግዚአብሔር ቃል ነው ከዚህም የተነሳ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 4 1 _ 4 ላይ ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ ይለናል እውነተኛው ቃል ጆሮን የሚያሳክክ ቢሆንም ሕይወት የሚገኝበት ትምህርት ነው ጌታ እግዚአብሔር ይህንን የሕይወት ትምህርት ሰምተን እንድንፈወስ እውነት መስለው ከሚያታልሉን ማለቅያ ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክና ተረት ከሚመልሱን አጓጉል ከሆኑ የሰዎች ሃሳብና ፈቃድ ካለበት እግዚአብሔር ይመልሰን ትምህርቱ ይቀጥላል ጌታ ይባርካችሁ


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment