Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ሃያ ሁለት



ቤተክርስቲያን


ክፍል ሃያ ሁለት



በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን አጽንታ ታስተምራለች



በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙ ብዙና ሰፊ ሃሳብ ያለው በመሆኑ መጽሐፍቅዱሳችንን ይበልጥ እንድናገላብጥ እንድናጠናም ያደርገናልና ሳንታክት እንከታተል በክርስቶስ ስለሆንን በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን በማለት ሐዋርያው ጻፈልን ቆላስያስ 1 2 በክርስቶስ ስለሆንን ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ በሰማይ ከተዘጋጀላችሁ ተስፋ የተነሣ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ እምነታችሁ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ስለዚህም ተስፋ በወንጌል እውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ ስለተባልን ክርስቶስ ኢየሱስ የሰማይ ተስፋችን በመሆኑ ይህንን የወንጌል እውነት እኛም አስቀድመን ሰማን ቆላስያስ 1 3 _ 5 በክርስቶስ ስለሆንን አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፥ ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጐደለውን እፈጽማለሁ ሲል ሐዋርያው ነገረን ቆላስያስ 1 24 በክርስቶስ ስለሆንን ጳውሎስ ብቻ ሳይሆን እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው ቆላስያስ 1 28 በክርስቶስ ስለሆንን በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል ሲል ሐዋርያው ተናገረን ቆላስያስ 2 5 በክርስቶስ ስለሆንን የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ ተባልን ቆላስያስ 2 11 በክርስቶስ ስለሆንን እናንተ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና 1 ተሰሎንቄ 2 14 በክርስቶስ ስለሆንን ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው አለን 1 ተሰሎንቄ 3 2 በክርስቶስ ስለሆንን ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ 1 ተሰሎንቄ 4 16 በክርስቶስ ስለሆንን ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና የሚል የተስፋ ቃል ተሰጠን 1 ተሰሎንቄ 5 17 _ 18  በክርስቶስ ስለሆንን የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ 1 ጢሞቴዎስ 1 14 በክርስቶስ ስለሆንን በዲቁና ሥራ በመልካም ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ማዕርግና በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ብዙ ድፍረት ያገኛሉ የሚል የተስፋ ቃል አገኘን 1 ጢሞቴዎስ 3 13  በክርስቶስ ስለሆንን ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና በሚል የማስጠንቀቅያ ቃል ተነገረን  1 ጢሞቴዎስ 5 11  በክርስቶስ ስለሆንን ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ ሲል ሐዋርያው ጻፈልን  1 ጢሞቴዎስ 6 13 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ሐዋርያው ስለራሱ ተናገረን 2 ጢሞቴዎስ 1 1 በክርስቶስ ስለሆንን ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን 2 ጢሞቴዎስ 1 9 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ ሲል ሐዋርያው ለእኛም መከረን 2 ጢሞቴዎስ 1 13 በክርስቶስ ስለሆንን እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ ሲል ሐዋርያው ዳግመኛ እኛንም አበረታታን 2 ጢሞቴዎስ 2 1 በክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ ሲል ደግሞ ጻፈልን 2 ጢሞቴዎስ 2 10 በክርስቶስ ስለሆንን በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ ተብሎ ተጻፈልን 2 ጢሞቴዎስ 3 12 በክርስቶስ ስለሆንን ስለዚህ የሚገባውን አዥ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ ይልቁንም እንደዚህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው አሁንም ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስር የሆንሁ ስለፍቅር እለምናለሁ ሲል የፍቅር ልመናውን አቀረበልን ፊልሞና 1 8 እና 9 በክርስቶስ ስለሆንን አዎን፥ ወንድሜ ሆይ፥ በጌታ እኔ እንድጠቀምብህ ይሁን፤ በክርስቶስ ልቤን አሳርፍልኝ ሲል ጻፈልን ፊልሞና 1 20  በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ከእኔ ጋር የታሰረ ኤጳፍራ በማለት የታሰረውን ኤፍራታን ጠቆመን ፊልሞና 1 23 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ ሲል ሐዋርያው ጴጥሮስ በአስደናቂው ምክሩ መከረን 1 ጴጥሮስ 3 16 በክርስቶስ ስለሆንን ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁም አለን 1 ጴጥሮስ 4   13 በክርስቶስ ስለሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል በማለት የማጽናኛ ቃል ጻፈልን 1 ጴጥሮስ 5 10 በክርስቶስ ስለሆንን በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን አሜን ሲል ሐዋርያው የሰላሙን ስምምነት አሜን በማለት ገለጸልን 1 ጴጥሮስ 5 14 በክርስቶስ ስለሆንን ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት ሲል ጻፈልን 2 ዮሐንስ መልዕክት 1 9 ወገኖች ሆይ መጽሐፍቅዱሳችሁን ይበልጥ ገልጣችሁ እንድታነቡ በክርስቶስ የመሆን ጥቅሙን በስፋት ከመጽሐፍቅዱሳችን ውስጥ በመጥቀስ ለማየት ሞክርናል የሚቀጥለው ትምህርቴ ግን በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ ለሰጠኋችሁ ጥቅሶች ማብራርያና መደምደምያ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦችን በጥቂቱ ላቀርብላችሁ እወዳለሁ እስከዚያው የጌታ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን የምላችሁ

ቀሲስ አባ ዮናስ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም

No comments:

Post a Comment