Sunday, 7 December 2014

የግጥሙ ርዕስ አንተ ሠረገላ

የግጥሙ ርዕስ

 



አንተ ሠረገላ 

 


አንተ ሠረገላ የእሳት ሠረገላ 
ከአርያም የመጣህ ገሥግሰህ በተድላ 
ፍጻሜው የታየ የእግዚአብሔር ሰው 
ሊወሰድ ሊነጠቅ ተራ የደረሰው 
ኤልያስ የሚባል በሀገር የታወቀው 
ሰማይን ሲከፍት ሲቆልፍ የታየው 
ካንተ ሳልወሰድ የምትፈልገውን 
ጠይቀኝ በቶሎ ፍጹም በመታመን 
ብሎ ተናገረ ለደቀመዝሙሩ 
ኤልሳዕ ለተባለው ታማኝ በምስጢሩ 
ኤልሳዕም ቸኮለ ለጥያቄው ፈጥኖ 
እጥፍ ድርብ ቅባት ፈልጎና ታምኖ 
ምንም እንኳ ኤልሳዕ አስቸጋሪ ነገር 
ቢለምን ቢጠይቅ በፍጹም ሳያፍር 
ይኸው ተቀበለ የቅባቱን ጉልበት 
ዮርዳኖስም ሆነ የተከፈለለት
ኤልሳዕን ሊያሻግር ፈቅዶና ታዞለት
አንተ ሠረገላ ጉደኛ ነህ በጣም 
ሁለቱን ወዳጆች ልትለያቸው ፍጹም 
መሐላቸው ገባህ ኤልያስን ልትወስደው 
አባት ብሎ ጮኸ ዳግመኛ ላያየው 
ደቀመዝሙር ኤልሳዕ ታማኝ ሆኖ የቆየው 
ሲወሰድ ሲነጠቅ በእሳት ሠረገላው 
የእግዚአብሔር ወዳጅ ኤልያስ ቴስቢያዊው

አንተ ሠረገላ የእሳት ሠረገላ
ከአርያም የመጣህ ገሥግሰህ በተድላ

« አንተ ሠረገላ የእሳት ሠረገላ ..……

No comments:

Post a Comment