Thursday, 4 December 2014

ቤተክርስቲያን ክፍል ስድስት



ቤተክርስቲያን

ክፍል ስድስት

የክፍል ስድስት ትምህርታችን ከክፍል አምስት የቀጠለ ተከታታይ ሃሳብ ነውና ቅዱሳን ወገኖች በማስተዋል ተከታተሉ ያነሳነው ሃሳብ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት በቅድሚያ እራስ መሠራት የሚል ነው የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩ ሰዎች በቅድሚያ እነርሱ የተሠሩ ናቸው ለዚህ ነው በጴጥሮስ መጽሐፍ ላይ በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ የሚለን 1 ጴጥሮስ 2 4 _ 6 ከዚህ የምንባብ ክፍል የምንረዳው መንፈሳዊ መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የተሠራ ነው ያልተሠራ ካህን መንፈሳዊ ቤት መሆን አይችልም እንደገናም መንፈሳዊ መስዋዕት ማቅረብም አይገባውም እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ቅድሚያ መሠራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው የምንሠራው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ ቀርበን ሕያዋን ድንጋዮች በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ  ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መስዋዕት ለማቅረብ ነው ስለዚህ ዛሬ ችግራችን ያለው መሥዋዕታችን ላይ ሳይሆን ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ ቀርበን እንደሚገባ ያልተሠራን በመሆናችን ያልተሠራው እኛነታችን  ነው ሰዎች ዛሬ ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ የሚቀርቡት ለመሠራት ብለው ሳይሆን የጎደለ ነገራቸው እንዲሞላ ከመፈለግ የተነሳ ነው ስለዚህ ብዙው ነገራችን የተሠራ አይደለም  ለዚህ ነው ጌታ የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል ? ሲል የተናገረው ትንቢተ ኢሳይያስ 1 11 _ 16 የእግዚአብሔር ጉዳይ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ መስዋዕት ሳይሆን የተሠራ ማንነት ነው በመሆኑም የእግዚአብሔር ጉዳይ የእኛም ይሁን በማለት ወንድማዊ ምክሬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ ሠሪያችን ጌታ ስለሆነ ኢሳይያስ 64 8 ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ ተባልን መሠራት ከብሉይ ኪዳን ዘመ ጀምሮ ያለና በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ በመሆኑ አዲስ ነገር የሚሆንብን አይደለም መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር 100 3 _ 5 ላይ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና አለን ስለዚህ ሰዎችን የሚሠራ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰዎች አይደሉም ሰው እንኳን ሌላውን ሊሠራ እራሱንም እንኳ መሥራት ማስተካከል አይችልም እንደገናም ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና የሚገባውና የሚያመሠግነው የተሠራ ሰው ነው   በኤርምያስ  መጽሐፍ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው፦ ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፥ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር በማለት ይቀጥልና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁ ይለናል ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 18 በሙሉ እናንብብ በመሆኑም እንግዲህ ወደድንም ጠላንም ሁላችንም ለመሠራት በእግዚአብሔር እጅ ነን ነገር ግን በሐዲስ ኪዳን የተሰጠን ምርጫ ፈቃደኛ ሆነን ወደ እርሱ በመቅረብ ለሚሠራን ለእርሱ እራሳችንን መስጠት ነው ይህ ካልሆነ ግን መሠራታችን የማይቀር በመሆኑ እግዚአብሔር በጊዜና በሁኔታዎች ውስጥ ይሠራናል አንዳንዶች ከሞኝነት ይሁን ካለማወቅ መድረክ ስለያዙ በሃላፊነት ቦታ ስለተቀመጡ ስለሚያስተዳድሩ ስለሚመሩ የተሠሩና ተሠርተውም ያለቁ ይመስላቸዋል ስለዚህ እራሳቸውን ለማየት ብሎም ለመሠራትና ለመስተካከል ፈቃደኞች አይደሉም ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን ጠንካራ መልዕክት ሲለቀቅ ቶሎ ብለው በተቃውሞ በመነሳት መልዕክቱንም ሆነ የመልዕክቱን አቅራቢ ሊያገሉ ሊጠሉና ሊያሳድዱ ይነሳሉ በራዕይ መጽሐፍ ላይ ለሰባቱም አብያተክርስቲያናት ልዩ ልዩ ዓይነት የማስጠንቀቅያ መልዕክት ተላልፎአል ራዕይ ምዕራፍ እና መመልከት እንችላለን በመሆኑም መልዕክቱን ያቀረበው ሳያፈገፍግ በግልጽነት ነው የተናገረው ስለዚህ ዛሬም ላይ ላለችው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል መልእክት በግልጽነት ሊነገር ይገባል በተለይ የንስሐ መልዕክት በአደባባይ በጀማ በክሩሴድ ጭምር የሚነገር እንጂ በጓዳ በግል ብቻ የሚነገር አይደለም ታድያ አንዳንዶች ይህን ከመጥላት ይመስላል በአደባባይ የሚነገሩ የንስሐ መልእክቶችን ሲጠሉ ተናጋሪውንም ሲያንቋሽሹና ሲያጥላሉ ይስተዋላሉ በዚህ ጉዳይ እንግዲህ እግዚአብሔር ይቅር ይበለን ከምል በቀር የምለው የለኝም ንስሐ የለውጥ የመመለስና የመታደስ ምልክት ነው ስለዚህ ንስሐ ብንገባ በብዙ እናተርፋለን እንጂ የምንጎዳው ነገር የለም ንስሐን መጥላት ግን ምን እንደሆነ ለእናንተው ለአንባቢዎች ብተወው እመርጣለሁ በኤፌሶን 2 21 እና  22  ላይ በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ ይለናል ስለዚህ እድገትና መሠራ ሁላችንንም የሚመለከት ጉዳይ ነው በቤቱ ውስጥ ሆነን እየተጋጠምን ያለን ሁላችን የእግዚአብሔር ሕንጻዎች የሆንን ቅዱሳን እንሠራለን በዚያው ልክ ደግሞ እናድጋለን በዚህ ቤት ውስጥ አንዱ አዳጊ ሌላው አሳዳጊ አይሆንም አንዱ ሠሪ ሌላው ተሠሪ አይሆንም በእርሱ ሁሉም እየተጋጠመ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን የሚያድግና ለእግዚአብሔርም መኖርያ ሊሆን የሚሠራ ነው ስለዚህ በአንዳንድ አስፈላጊና ተገቢ በሆኑ መጽሐፍቅዱሳዊ መልዕክቶች መቆጣት አልሠራም አላድግም አልለወጥም ማለትን ያመለክትብናልና ብንታመምም የግድ እስክንፈወስ ድረስ ታግሠን መጠበቅ የእኛ ይሆናል ምናልባትም በመልእክቱ የታመምነው እግዚአብሔር እየሠራንና እያሳደገን ስለሆነ ከመቃወም የእግዚአብሔርንም መልዕክተኞች ከማሳደድና ስም ከማጥፋት ይልቅ የመጣው መልዕክት እኔን ለመለወጥ ስለሆነ ለበጎ ነው ልንል ይገባል


የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ለሕይወት ያድርግልን


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment