ካህን የቱንም ያህል የራሱን ሕይወት በሥርዓት የሚመራ ቢኾንም እንኳን፥ ለአንተ (ድኅነት) የማይጨነቅ ከኾነ፣ አዎ፥ ለአንተ ብቻ ሳይ!ኾን በእርሱ ዙሪያ ላሉት ሰዎች ኹሉ የማይጠነቀቅ ከኾነ፥ ዕጣ ፈንታው ጽዋ ተርታው ከክፉዎች ጋር በእሳተ ገሃነም ነው፡፡ እርሱ ራሱ በሠራው ኃጢአት ተጠያቂ ባይኾንም እንኳን ማድረግ የሚገባውን ባያደርግ በአንተ መጥፋት ምክንያት እርሱም ይጠፋል፡፡
ስለዚህ ይህ ታላቅ ጉዳት ሊያገኘው እንደሚችል ዐውቀህ ተረድተህ፥ ለካህናት ከፍ ያለ በጎ ፈቃድህን ስጣቸው (ታዘዛቸው)፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ” ብቻ ሳይኾን “ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡ እንደ መኾናቸው” ያለው ይህን ሲያመለክት ነውና (ዕብ.13፡17)፡፡
ስለዚህ ካህናት ከእናንተ ከምእመናን ከፍ ያለ ክብርን [እንደዚሁም ማግኘት ያለባቸውን ኹሉ] ሊቀበሉ ይገባቸዋል፡፡ እነርሱን በመናቅ በማዋረድ ከሌሎች ጋር የምትተባበሩ ከኾነ ግን፥ የእናንተ የገዛ ራሳችሁ ድኅነትም ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ አንድ የመርከብ አለቃ በበጎ ሕሊና ውስጥ ሲኾን፥ የተጓዡ ደኅንነተም እንደዚሁ የተጠበቀ ይኾናል፡፡ በተጓዦቹ ንቀትና መዋረድ የተሰላቸ ከኾነ ግን በአግባቡ ሊጠነቀቅላቸው አይችልም፤ ወይም መርከቢቱን በአግባቡ መምራት አይቻለውም፡፡ ከዚህ የተነሣም ራሱን ጨምሮ ተጓዦቹን ኹሉ እልፍ መከራ ውስጥ ይከትታቸዋል፤ የመርከብ አደጋ እንዲገጥማቸው ያደርጋል፡፡
ልክ እንደዚሁ ካህኑም ከእናንተ ክብርን የሚቀበል ከኾነ፥ የራሱን ብቻ ሳይኾን የእናንተንም ጉዳዮች በአግባቡ መምራት ይቻለዋል፡፡ ካህናቱን ተስፋ ወደ መቁረጥ ስሜት ወደ ኀዘን የምታስገቡዋቸው ከኾናችሁ ግን እጆቻቸው እንዲዝሉ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ይህን የምታደርጉ ከኾነም የቱንም ያህል ቢተጉ እንኳን እነርሱን ብቻ ሳይኾን ራሳችሁንም እጅግ ከፍ ወዳለ መዋግድ (ወደ ብዙ ማዕበል) ታስገባላችሁ፡፡
በልብ መታሰቡ በሕሊናም መዘከሩ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን ክርስቶስ አይሁድን በተመለከተ ምን እንዳለ አድምጡ፡- “ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡ ስለዚህ ያዘዙአችሁን ኹሉ አድርጉ ጠብቁትም” (ማቴ.23፡2-3)፡፡ አሁን “ካህናተ ሐዲስ በሙሴ ወንበር ተጠቀምጠዋል” ልንል አይገባንም፤ “በክርስቶስ ወንበር” ተቀምጠዋል ልንል ይገባናል እንጂ፡፡ እንደሚገባ ትምህርቱን ተቀብለዋልና፡፡ እንዲህም በመኾኑ ቅዱስ ጳውሎስ ጨምሮ፡- “እግዚአብሔር በእኛ [እናንተን] እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል (2ኛ ቆሮ.5፡20)፡፡
[ስለዚህ ስለ ነፍሳችሁ የሚተጉትን፣ ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡትን ካህናተ ሐዲስን እጅግ ልታከብሯቸው፣ ልትታዘዟቸውም ይገባል፡፡]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የዮሐንስ ወንጌልን ሲተረጉም ከድርሳን 86 የተወሰደ