"ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነውና በጊዜህ ሁሉ ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት አይምሰልህ። ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።"
#ብላቴን_ጌታ_ኅሩይ_ወልደ_ሥላሴ
#ብላቴን_ጌታ_ኅሩይ_ወልደ_ሥላሴ
ውድ ወንድሜ ሰውን በስብከት ለማገልገል የግድ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መድረክ ላይ በመቆም ብቻ አይደለም፣ ትልቁና ዋነኛው ሰውን በራስ ህይወት መለወጥ ነው፡፡ ስለዚህ በህይወትህ ለብዙዎች አብነት እንድትሆን እንጂ የግድ ስብከት አዘጋጅተህ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይጠበቅብህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከሆንክ ሰዎች ፊትህን ባዩት ጊዜ የዋህነትን፣ ሩህሩህነትን ይማራሉ፣ ንግግርህንም በሰሙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራነት፣ ታማኝነት፣ ፍፁምነትና ፍቅርን ያገኛሉ፡፡
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ - ከመንፈስ ነፃነት የተወሰደ)
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ - ከመንፈስ ነፃነት የተወሰደ)