"ማንነትህን ማወቅ"
ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።
ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እንደጻፉት)

የኦሮሚያ ቤተክህነት መስራቾች የነ ቄስ በላይ ጉድ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ማን ያርዳ የቀበረ ፣ ማን ያዉራ የነበረ እንደሚባለው የኦሮሞ ባሌ ተወላጅ መላከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ በ Ltv ወቅታዊ ከጋዜጠኛ ተመስገን መንግስቴ ጋር ቀርበው የእነዚህን ጉደኞች ጉድ ይበልጥ አፍረጥርጠዉታል ።
አባ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል
.......>ይህንን የሚያደርገው ሰው በ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ በተደረገው ምርጫ መጭበርበር ምክንያት የኦሮሞ ልጆች ሲጨፈጨፉ የልጆቹን መጨፍጨፍ ትክክል ነው ብሎ ለመንግሥት መልስ የሰጠና ህዝብን ያስጨፈጨፈ ሰው ነው ።
አሁን የኦሮሚያ ቤተክህነት እንመስርት ብለው የተሰለፉ ሰዎች ለኦሮሞ ህዝብ በቋንቋ መጠቀም አዝነው ከሆነ ከ10 ዓመት በፊት የቤተክርስቲያን ሶስተኛ ባለስልጣን ነበር ፣ የቤተክርስቲያን ምክትል ስራ አስኪያጅ ነበር ለምን በዛ ሰዓት ይህንን አላደረገም ?
በ2001 ዓ.ም እኔ ስለቤተክርስቲያን እና ስለ ኦሮሞ ህዝብ በቋንቋው መጠቀም ስላለበት ፣ ቤተክርስቲያን ላይ ስላለው ችግር ሳነሳ እነዚህ ሰዎች ባለስልጣን ነበሩግን ጥያቄውን ማንሳት ይቅርና ቀና ብለው የማያዩ ሰዎች ነበሩእንደዉም እኔን ከስራ አስባረዉ ለ3 ወር ደሞዜን ተነጥቄ ነበር ከስራ ተባርሬም ነበር ፣ ጥያቄውንም አፍነዉት ነበር ለምን ካላችሁ የመንግሥት ተላላኪዎች ነበሩ ።
እነዚህ ሰዎች ከቤተክርስቲያኒቱ ወጥተው ፓለቲካዉን ማቡካት ከጀመረ አመታትን አስቆጥረዋል ።
ከእነዚህ ሰዎች በስተጀርባ ያለው ትናንት የኦሮሞ ክርስቲያኖችን በሜንጫ አንገቱን በሜንጫ መቅላት ነበር ስለን የነበረው አክራሪ ብሔርተኛ ሰው ነው ።
በአጭሩ እነዚህ ሰዎች ጭንቅላታቸው ለኦሮሞ ህዝበ ክርስቲያንና ክርስቲያን ማሰብ ሳይሆን የዘር ፓለቲካን ማራመድ ነው አላማቸው የኦሮሞ ወጣቶችም ይህን ማወቅ አለባቸው ነገ እነዚህ ሰዎች በኦሮሞ ክርስቲያኖች ላይ እንደሚነሱ ማወቅ አለባቸው ቤተክርስቲያንም አንድ ስለሆነች በአባቶቻችን መስዋዕትነት ነገም አንድ ሆና ትቀጥላለች
ያሳለፈውም እና ያለፈውም ታሪክ ይህንን ያስረዳል ።
እና ሌሎችንም አባታችን ብዙ ብለዋል በLtv ወቅታዊ ላይ ማየት ትችላላችሁ