…እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ አኖራለሁ ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለ አይፀፀትም ጻድቅ እረሱ (ዳዊት) ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈፀመ ከዚህ በኋላ "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ብሎ ጮኸ ይህችውም አማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወለድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት።… ቅድስት ሆይ ለምኝልን።…
በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ። እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ።
(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)
(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ
ትርጉም፦ ዓለም ሳይፈጠር ለነበረና ዓለምን አሳልፎ ለዘለዓለም ለሚኖር ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድረጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው።"
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

…በዚህ አለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን ስለሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው ፣ አዳምን ከስህተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና የምንወለድበትን መንፈስ ረቂቁን (ረቂቁን ልደት ) ሰጠኸን ፣ ከመላእክት ጋርም አመሰገንህ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 22ኛው ድርሳኑ ላይ ይህኑን ኃይለ ቃል ደግሞ ተርጉሞት እናገኛለን ፡፡ እርሱ ለወይን መጥመቂያዎቹ ጋኖች አይሁድ የማንጻት ሥርዐትን ፈጸሙ ብሎ ወንጌላዊው መጻፉ ለምን ዓላማ እንደሆነ እንዲህ በማለት ይገልጽልናል፡-
“በዚያን ዘመን አይሁድ የወይን ጠጃቸውን የሚጠምቁት
በድንጋይ ጋኖች ነበር፡፡ ስለዚህም ወንጌላዊው “አይሁድም
እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡ ኢየሱስም ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው” ብሎ ጻፈልን፡፡ ወንጌላዊው እንዲህ ማለቱ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የወይን ጠጁ ካለቀ በኋላ የሚቀረው አተላ በውኃ ቢጠበጥ ደካማ ወይን ጠጅ ስለሚሆን (በእኛ ቅራሪ እንደምንለው ዓይነት ነው) ኢአማንያን አተላውን በውኃው በጥብጦ ተአምር አደረኩ ይለናል ብለው እርሱን ከመማን እንዳይመለሱ፤ የድንጋይ ጋኖቹ በአይሁድ የማንጻት ልማድ በውስጣቸው ያለው አተላ(Lee) ተደፍቶ ንጹሑ መሆናቸውን ለማስረዳት ሲል ወንጌላዊው እንዲህ አለ፡፡
አሁን ደግሞ ቀደም ብለን ወደ ተመለከትነው ወደ መጀመሪያ
ድርሳኑ እንመለስ፡፡ በዚህ ድርሳን ላይ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ብሎ ጽፎልን እናገኛለን፡-
“… ጌታችን በሌላ ቦታ አንዲት ሴት “የተሸከመችህ ማኅፀንና
የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው”(ሉቃ.11፡27) ያለችውን
እንደገሠጻት እናቱን በዚህ ቦታ የገሠጻት አይደለም፡፡ ያቺ ሴት
ከእርሱ በአጸፌታው ብፅዕት መባልን ሽታ ስለነበርና ስለዚህ
ጌታችን “አዎን ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው
የሚጠብቁት ናቸው” ብሎ መለሰላት፡፡ እንዲህም ሲል በሥጋ የወለደችውን እናቱን ክብር ማቃለሉ ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከእርሱዋ መወለዱ ንጽሕናዋንና እምነቱዋን ተመልክቶ እንደሆነ ለማስረዳት እንዲህ አለ፡፡ ይህም የቅድስት እናታችንን ንጽሕናና ቅድስና በእጅጉ የሚያጎላ ነው፡፡
ቅድስት እናታችንን ለእናትነት ያበቃት ራሱዋን በቅድስና ጠበቃ በመገኘቱዋ ነው እንጂ በሥጋ ከዳዊት ወገን በመሆኑዋ ብቻ አልነበረም፡፡ ይህ ለእኛ ልዩ ትምህርትን ይሰጠናል፡፡ እኛ በጥምቀት የእርሱ ወገኖች የተባልን ክርስቲያኖች በመልካም ሥነ-ምግባራችን ካልተመላለስን በቀር በስም ብቻ የክርስቶስ ቤተሰቦች መሰኘታችን የሚያመጣልን አንዳች ፋይዳ እንደሌለ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእናትነት የመመረጡዋ ምክንያት ይጠቁመናል፡፡ ዳዊት በሥጋ ዘመዶቻቸው ስለሚታመኑ ሲናገር “ወንድም ወንድሙን አያድንም” (መዝ.48፡7) ብሎአል፡፡ እኛም ከቅዱሳን ጋር በሥጋ ስለተዛመድን ብቻ አንድንም፡፡ ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ያገኘነውን ጸጋ ተጠቅመን ራሳችንን በቅድስና ያመላለስን እንደሆነ ብቻ ልንድን እንችላለን፡፡ እንዲህ አድርገን ስንገኝ ነው ከቅዱስናው ተካፋዮች ለመሆን የምንበቃው፡፡
አይሁድ በሥጋ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ወገናቸው ስለሆነ አልዳኑም፡፡ የጌታ ወንድሞች ከተባሉት ውስጥ (ከያዕቆብና ከይሁዳ በቀር) የዳነ የለም፡፡ የእርሱ ወንድሞች መባላቸው ከዓለም ጋር ከመጥፋት አልታደጋቸውም፡፡ እርሱ ያስተማረባት ኢየሩሳሌም (በጥጦስ) ከመጥፋት አልዳነችም፡፡ በሥጋ ከጌታ ጋር የሚዛመዱ አይሁድ ክርስቶስን ባለመቀበላቸው በአሕዛብ ነገሥታት ተጨፈፍጭፈው አልቀዋል፡፡
ምክንያቱም የክርስቶስን አምላክነት በመቀበል የጽድቅ ጥሩርን ለብሰው ባለመገኘታቸው ነበር፡፡ ሐዋርያት ግን ከአይሁድ ተለይተው ከሌሎች ይልቅ ልቀውና ከብረው ተገኙ፡፡ ምክንያቱም የሚያድናቸውንና የሚጠቅማቸውን የጽድቅ ጎዳና ተከትለው ነበረና፡፡ ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ተጠቃሚዎች ለመሆን ልክ እንደ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእምነታችን መጽናትና በመልካም ሥነ ምግባር በመመላለስ ለዓለም ብርሃን ሆነን መገኘት ይኖርብናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ብቻ ነው ልንድን የምንችለው፡፡ እነ እገሌ እና እነ እገሌ የክርስቶስ የሥጋ ዘመዶች ነበሩ የተባለላቸው ሰዎች ነበሩ፤ አሁን ግን ከነስም አጠራራቸው ጠፍተዋል፡፡ እርሱን በእምነት የተከተሉት ሐዋርያት ግን ሥራቸውና ስማቸው በዓለም ዙሪያ ሲታወስና ሲወሳ እስካሁን አለ፡፡
የብዙ ሺህ ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች የሥጋ ወገኖች በመሆናችን አንመካ፤ ነገር ግን በእነርሱ የጽድቅ ሥራ ብቻ ከፍርድ እንደማናመልጥ ተረድተን እነርሱን በምግባር እንምሰላቸው፡፡ ቅዱሳን ከሆኑ ወገኖች በመወለዳችን በእኛ ላይ የባሰን ፍርድ ከማምጣት በቀር ሌላ በሥጋ በመዛመዳችን አንዳች ብቻ የምናገኘው ጥቅም የለም፡፡ ይልቁኑ ምሳሌ የሚሆኑን በሥጋ የተዛመድናቸው ቅዱሳን ከአጠገባችን እያሉ እነርሱን በምግባር መስለን አለመገኘታችን የባሰ ፍርድን ያመጣብናል፡፡ እኛ አይደለም እነርሱን ልንመስል የመምህራኖቻችንን የሕይወት ፈለግ ልንከተል አልፈቀድንም፡፡
እኔ እንዲህ ማለቴ ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰብከን ወደ
ክርስትና እምነት ካመጣናቸው በኋላ እነርሱ በእኛ ላይ ያላቸውን ትምክህት በመስማቴ ነው፡፡ እነርሱ ወደ ክርስትና እምነት ከተመለሱ በኋላ ዘመዶቻቸውንና የሥጋ ወገኖቻቸውን እንዲሁም ቤታቸውን በመተው “የእኛ ዘመዶች፣ ወዳጆችና፣ ባልንጀሮች በክርስትና እምነት ውስጥ ያሉት ክርስቲያኖች ናቸው” ብለው በድፍረት በእኛ እንደሚመኩ ይናገራሉ፡፡ ይህ ለእኛ ታላቅ ውርደት ነው፡፡ ምክንያቱም ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የተመለሱ ወገኖች በእኛ እየተመኩ እኛ ግን ከጽድቅ ሕይወት ርቀን በኃጢአት ሕይወት ውስጥ እየዳከረን መገኘታችን ነው፡፡
ሌላው የሚያስደንቀው ነገር ለክርስቲያናዊ ሥነምግባር ቦታ
ሳትሰጥ ስለክርስቲያናዊ ሥነምግባራችን በተጠየቅን ጊዜ
እራሳችንን ለመከላከል ስትል “የኔ አባት፣ አያቴ፣ ቅም ቅም
አያቶቼ፣ እንዴት ያሉ ቅዱሳን ነበሩ” ብለን መመለሳችን ነው፡፡
እንዲህ በማለታችን ግን በራሳችን ላይ ፍርድ ይበረታብናል እንጂ አንዳች ጥቅምን አናገኝም፡፡ ምክንያቱም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የቅድስና ሰንሰለት በእኛ ክፉ ምግባር በመበጠሳችን ነው፡፡
ለአይሁድ ነቢያት ምን እንደሚሉዋቸው ስሙ“…እስራኤል
ስለሚስት አገለገለ፡፡ ስለ ሚስትም ጠባቂ ነበር፡፡”(ሆሴ.12፡
13) እንዲሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
“አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ አየም ደስም አለው” ብሎ መሰከረለት፡፡(ዮሐ.8፡56) በሁሉ ስፍራ ነቢያት ለእስራኤላውያን ሲያስተምሩዋቸው የአባቶቻቸውን የጽድቅ ሥራ በማስቀደም ነበር፡፡ እኚህ ነቢያት ቅዱሳን አባቶችን እያመሰገኑአቸው ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አይሁድ እነርሱን አብነት አድርገው በጽድቅ ሕይወት ባለመመላለሳቸው ምክንያት የባሰ ፍርድ እንደሚከተላቸው ሲያስጠነቁቋቸውም ጭምር ነበር፡፡
እንግዲህ ይህን ልብ በሉ ራሳችሁን ታድኑ ዘንድ በጽድቅ ሥራ ትጉ፤ በሌሎች መልካም ሥራ ተደግፋችሁ የምትድኑ
መስሎአችሁ ራሳችሁን አታታሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አመለካከት
ለእኛ ምንም ዓይነት ትርፍን አያመጣልንም፡፡ ነቢዩ ዳዊት
“በሞት የሚያስብህ የለም” ካለ በኋላ “በሲኦልም
የሚያመሰግንህ ማን ነው? አለ፡፡(መዝ.6፡5) ስለዚህ
በእግዚአብሔር መንግሥት ከማይመጠነው በረከት ተካፋይ ለመሆን እንድንበቃ ነፍሳችን ከሥጋችን ሳትለይ በዚህች ዓለም ሳለን ንስሐ እንግባ፡፡
በአፍቃሪያችን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር አብና ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡