"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።"
ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ
ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ
"የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ ‘ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ’ አለው” (ማቴ.2፡13)፡፡
እዚህ ላይ ሰብአ ሰገልንና ብላቴናውን የተመለከተ ልንጠይቀው የሚገባን ጥያቄ አለ፡፡ ሰብአ ሰገል ያልተደናገጡ ይልቁንም ኹሉንም ነገር የተቀበሉት በእምነት ከነበረ፥ እኛ ደግሞ ለምን እነርሱ ወደ ፋርስ፣ ጌታችንም ከእናቱ ጋር ወደ ግብፅ ሳይሸሹና በቤተ ልሔም በመቆየት ከሄሮድስ መከራ እንዳልተረፉ ልንጠይቅ ይገባናል፡፡ ስለዚህ ለምን? ጌታችን ወደ ግብፅ ሳይሸሽ በሄሮድስ እጅ ቢያዝ ሄሮድስ ምንም ምን እንዳያደርግበት ማድረግ አይችልም ነበርን? አይደለም ! ጌታችን ገና በዚህ ዕድሜው እንደዚህ አድርጎ ቢኾን ኖሮ ፍጹም ሰው መኾኑ (ትስብእቱ) ባልታመነ ነበር፤ [ምትሐት ነው በተባለ ነበር፡፡] ሰው ኾኖ ሰውን ያዳነበት የኪነ ጥበቡ ታላቅነት ዕፁብነትም ሰው ባልተቀበለው ነበር፡፡
እነዚህና ሌሎች ሰዎች ሊገባቸው በሚችል መልኩ የተከናወኑ ብዙ ምሥጢራትና መንፈሳውያን ተግባራት እየተከናወኑ እያለ እንኳን አንዳንድ ሰዎች “እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ አልተዋሐደም፤ [ሎቱ ስብሐትና] ተረት ተረት ነው” ብለው ለመናገር ከደፈሩ፥ ኹሉንም ነገሮች እንደ ሰውነቱ ሳይኾን እንደ አምላክነቱና እንደ ኃይሉ መጠን ቢያደርገው ኖሮ’ማ ምን የማይሉት ጽርፈት ነበር? ምንስ የማይደፍሩት ድፈረት ነበር?
በመኾኑም በአንድ መልኩ ሰብአ ሰገልን ለፋርስ ሀገር ሰዎች መምህራን አድርጎ ሾሞ ላካቸው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ንጉሡ የማይቻለውን ነገር ለማድረግ እየሞከረ እንደ ነበረ እንዲያውቅ፣ ማንንም ሳይኾን የገዛ ራሱን የሚጎዳውን ቊጣውን እንዲያርቅ፣ ከንቱ ድካሙንም እንዲያቆም እያደረገው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶቹን በግልፅ ድል መንሣት ብቻ ሳይኾን [“አሸናፊ እግዚአብሔር” እንዲል] ሕሊናቸውን በቀላሉ መርታትም ኃይሉ ነውና፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ግብፃውያንን በሕሊናቸው ደረጃ ረትቶአቸዋል፡፡ ወርቅና ብራቸውን በኃይል አስገድዶ ሳይኾን ሕሊናቸውን በመርታት ለአይሁድ በግልፅ እየቈጠሩ እንዲሰጡ አድርጓቸዋል፡፡ በሕሊናቸው ሲረታቸው ከአፍአ ያየው አንድስ እንኳ አልነበረም፡፡ ይህም በእውነት ያለ ሐሰት ከሌሎቹ ተአምራት ምንም ምን ያልተነናነሰ [እና ዐሥራ ኹለተኛው] ተአምር ነው፡፡ ይህ መርታቱም [እንደ ሌሎቹ ተአምራት] በጠላቶቹ ዘንድ እንዲፈራ ያደርገዋል፡፡ የአስቀሎናና ሌሎች ሰዎች ታቦተ ጽዮንን ማርከው ከወሰዱአት በኋላም የእግዚአብሔር እደ መዓቱ በሀገራቸው ሰዎች ላይ ጸናች፡፡ [ብልታቸውን አሳብጦ አጠፋቸው፡፡ የአይጥ ወራሪ አመጣባቸው፡፡] የአስቀሎና ሰዎች ይህን ካዩ በኋላ ግን ሟርተኞችን ጠርተው አይሁድን እንውረራቸው እንውጋቸው አላሉም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ እንዲነሣሡ አላደረጉአቸውም፡፡ ሌላው ተአምራት ያስፈራቸውን ያህል ሕሊናቸውም ተረትቶ እንዲህ ነበር ያሉት፡- “እስራኤልን አንሰድም ብለው ፈርዖን ግብፃውያን ልባቸውን እንደ አጸኑ ታቦተ ጽዮንን አንሰድም በማለት ልቡናችሁን ለምን ታጸናላችሁ?” (1ኛ ሳሙ.6፡6)፡፡ ይህንን ያሉት በግልፅ ከተደረጉት ተአምራት የማይተናነስ ሌላ ተአምር በልባቸው ስለ ተከናወነ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ኃይሉና ታላቅነቱን በግልፅ የሚያስረዳ ነው፡፡ እዚህም ላይ የኾነው ልክ እንደዚህ፥ ጨካኙን ንጉሥ ዕፁብ ድንቅ ለማስባል በቂ የኾነ ነገር ነበር፡፡ ሰብአ ሰገል እንዳታለሉትና እንደ ተሳለቁበት ባወቀ ጊዜ ሄሮድስ ምን ተሰምቶት ሊኾን እንደሚችል፣ ትንፋሹ እንዴት ቀጥ ብሎ ሊኾን እንደሚችል አስብ፡፡ ወደ ልቡናው ተመልሶ ደግ ካልኾነ ታዲያ ምን ይኹን? ይህ እንዲኾን ስሕተቱ ጌታችን እነዚህን ኹሉ ነገሮች በኪነ ጥበቡ እንዲያ እንዲኾኑ ስላደረገ ሳይኾን ሄሮድስ ራሱ መጠን አለፍ ከኾነ ዕብደቱ የተነሣ ነው፡፡ በበደል ላይ በደል እየጨመረ በፍዳ ላይ ፍዳ በራሱ ላይ ከመረ እንጂ ልቡናውን ወደ በጎ አልመለሰምና፤ ደንግጦ ከክፋት አልተከለከለምና፡፡
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፥ ድር.8፥2