"የብሉይ ኪዳን ካህናት ሰውነትን ከለምጽ የማንጻት ሥልጣን ነበራቸው፡፡ እንዲያውም የማንጻት ሥልጣን ሳይኾን የነጹ መኾን አለመኾናቸውን መመርመርና የጻውን ነጽቶአል ብሎ ማወጅ ብቻ ነበር፡፡ እንዲህም ኾኖ ግን ካህናት ምን ያህል ይከበሩ እንደ ነበር ከመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ይቻላል፡፡ የዘመነ ሐዲስ ካህናት ግን ሥልጣን የተቀበሉት በሥጋ ለምጽ ላይ ሳይኾን በነፍስ ለምጽ ላይ ነው፡፡ ከተመለከቱ በኋላ ንጹህ መኾን አለመኾኑን ለመመርመር ሳይኾን በርግጥና በፍጹም ለማንጻት ነው፡፡ ስለኾነም የዘመነ ሐዲስ ካህናትን ከሚነቅፉት፥ ከዳታንና ከማኅበሩ የበለጠ እጅግ የተረገሙ ናቸው፤ ከእነርሱ የባሰ ቅጣትም የሚገባቸው ናቸው፡፡"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ክህነት፣ ፫፥፮
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ክህነት፣ ፫፥፮
"ቀና ያይደለ ጠማማ የሆነ አገር ከዚህ ያለን አይደለም ነቢያትና ሐዋርያት አስቀድመው የደረሱበት በልዕልና ያለ ነው እንጂ። ለእኛ ከዚሕ በአሸዋ የተሠራ ነፋሳት የሚነፍሱበት ፈሳሾች የሚገፉት ቤት ያለን አይደለም።በላይ ያለች ነጻ የምታወጣ ኢየሩሳሌም ናት እንጂ። አስቀድመው የጳጳሳት አለቆች፣ ጳጳሳት ፣ኤጴስ ቆጶሳት፣ቀሳውስትና ዲያቆናትም የገቡባት ናት እንጂ። እኚህ እንደኛ ሥጋን የለበሱ ሲሆኑ ባነዋወራቸው መላእክትን መሰሉ። ሰውነታቸውን አነጹ
ልብሳቸውንም ነጭ አደረጉ። የሥጋቸውንም አዳራሽነት አላሳደፉም ስማቸው በበጉ ደም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተጻፈ፡፡"
/ቅዳሴ አትናቴዎስ/
ልብሳቸውንም ነጭ አደረጉ። የሥጋቸውንም አዳራሽነት አላሳደፉም ስማቸው በበጉ ደም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተጻፈ፡፡"
/ቅዳሴ አትናቴዎስ/
"ሰዎች ኹሉ የሚያብዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ እናም እነርሱ እንዳበዱት ያላበደ ሰውን ካዩ 'አንተ እብድ ነህ፤ እንደኛ አይደለህም' እያሉ ያጠቁታል" ታላቁ ቅዱስ እንጦንስ
ከብልህ ሰው ፫ ነገሮች ፩ ለሰው ሁሉ ቸር አዛኝ መሆን ፪ በዛም አነሰም በሰጡት አመስጋኝ መሆን ፫ በሰው ነገር ጥልቅ ብሎ አለመግባት ናቸው። ✝፫ ቱን ነገሮች የያዘ ሰው ፍፁም ነው✝ ፩ ማስተዋል ፪ማወቅ ፫ሃይማኖት ናቸው። እነዚህ ሦሥቱ በዓለም ለመኖር ክብር ሲሆን ልቦና (ማስተዋል) ለስጋ ገዢዋ ነው። አእምሮ(ማወቅ)መሪዋ ነው። ሃይማኖትም ብርሃን ነው። 💠💠ላታደርጉት የማይገቡ ፫ ነገሮች💠💠 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ፩እግዚአብሔር በቀባው ንጉስ ላይ መሳቅ መሳለቅ (መክ 10:20) ፪ በአዋቂና በጀግና ሰው መዘበት (1ጢሞ5:1-2) ፫ በሚመክርና በሚያስተምር ልባም ሰው ላይ መቀለድ (ሮሜ 12፥8)💠💠 ፍኖተ ዜማ ወስብሀት ለእግዚአብሔ
"የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ"
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ