"የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ፤ መከራን ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፤ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በነገሩም ሐሰት አልተገኘበትም፡፡ከመስቀሉ ወደ ሲኦል በመውረዱ አዳነን፤ በአባታቸው በአዳም በደል በሲኦል ተግዘው የነበሩ ጻድቃንን ፈታ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣ በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን፤ የንስሐንም በር ከፈተልን፡፡በአባታችን በአዳም በደል የተዘጋ የገነት ደጅን የከፈተልን፤ ዕፀ ሕይወትን የሚጠብቅ ኪሩብንም ያስወገደ፤ የእሳት ጦርን ከእጁ ያራቀ፤ ወደ ዕፀ ሕይወት ያደረሰን እርሱ ነው፤ ፍሬውንም (ሥጋውን ደሙን) ተቀበልን፡፡"
ሃይማኖት አበው ዘጎርጎርዮስ 36፣26፣27፣30፣38
ሃይማኖት አበው ዘጎርጎርዮስ 36፣26፣27፣30፣38
December 30, 2018