"እምነት ያለ ሥራ (ምግባር) የሞተ ነው፤ ሥራም ያለ እምነት እንደዚሁ የሞተ ነው፡፡ በእምነታችን ሕፀፅ የሌለብን ብንኾንም እንኳን ምግባር ግን ከሌለን እምነታችን ብቻውን ምንም አይጠቅመንም፡፡ ልክ እንደዚሁ በጎ ምግባራትን ለመሥራት ብዙ መከራዎችን ብንቀበልም እምነት ግን ከሌለን ምንም አይረባንም፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኦሪት ዘፍጥረት፣ ድርሳን ፪፥፲፬
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኦሪት ዘፍጥረት፣ ድርሳን ፪፥፲፬
+ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ +
‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)
‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተርእዮ ማርያም አበው‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)
‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"የብሉይ ኪዳን ካህናት ሰውነትን ከለምጽ የማንጻት ሥልጣን ነበራቸው፡፡ እንዲያውም የማንጻት ሥልጣን ሳይኾን የነጹ መኾን አለመኾናቸውን መመርመርና የጻውን ነጽቶአል ብሎ ማወጅ ብቻ ነበር፡፡ እንዲህም ኾኖ ግን ካህናት ምን ያህል ይከበሩ እንደ ነበር ከመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ይቻላል፡፡ የዘመነ ሐዲስ ካህናት ግን ሥልጣን የተቀበሉት በሥጋ ለምጽ ላይ ሳይኾን በነፍስ ለምጽ ላይ ነው፡፡ ከተመለከቱ በኋላ ንጹህ መኾን አለመኾኑን ለመመርመር ሳይኾን በርግጥና በፍጹም ለማንጻት ነው፡፡ ስለኾነም የዘመነ ሐዲስ ካህናትን ከሚነቅፉት፥ ከዳታንና ከማኅበሩ የበለጠ እጅግ የተረገሙ ናቸው፤ ከእነርሱ የባሰ ቅጣትም የሚገባቸው ናቸው፡፡"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ክህነት፣ ፫፥፮
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ክህነት፣ ፫፥፮