🕯🕯🕯
ቤተ ክርስቲያን መሄድ ጥቅም የለውምን ?
የግብጻዊው መነኩሴን ምክር ላካፍላችሁ
ብዙ ጊዜ በእግረ ስጋው ወደ ቤ/ክ ይመላለስ የነበረ አንድ አማኝ ወደ አንድ አባት ሄዶ ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን መመላለሱ ስሜት አልባ እና ትርጉም የሌለው ነገር እንደሆነበት እየተማረረ እንዲህ አላቸው “ለ 30 አመታት ያህል ቤተ ክርስቲያን ተመላልሻለሁ፣ በእነዚህ አመታት ብዙ ጉባኤያትን ተካፍያለሁ፣ ቅዳሴ አስቀድሻለሁ፣ ንስሀ ገብቻለሁ. . . . . . ግን ትርጉም ያለው ነገር የለኝም፣ ካሳለፍኳቸው አገልግሎቶች ውስጥ ትዝ የሚሉኝ ብዙም የሉም፣ እንደ ትዝታ የሚታወሰኝም የለኝም፣ እንደ ብክነት አየዋለሁ . . . .ካህናቱና ሰባክያኑም ያለ ምንም ትርፍ ጊዜያቸውን እያባከኑ ያለ ይመስለኛል. . . . .”
ካህኑ በጥንቃቄ አዳመጡት፡፡ የብዙ አማኝ ችግርም እንደሆነ አስረዱት፣ ሰይጣን ሆነ ብሎ የቀየሰው ወጥመድ እንደሆነ አስታወሱትና ያለፈውን የህይወት ተሞክሯቸውን እያነሱለት እሱ እንደ ብክነት መስሎት የተመለከተው ነገር ጥቅሙ እንደነበር ነግረውት የእሱ ችግር ሰይጣን ቤተ ክርስቲያን ባሳለፋቸው 30 አመታት የተጠቀመውን እንዳይመለከት አይኑን ዘግቶት ጉድለቱን ብቻ እያሳየው ተስፋ እያስቆረጠው እንደሆነ ነግረውት የራሳቸውን ተሞክሮ በዘይቤ እንዲህ አሉት ፡-
“ትዳር የያዝኩት የዛሬ 30 አመት ነው፣ ካገባሁ 30 አመት ሞልቶኛል፡፡ በእነዚህ 30 አመታት ውስጥ ባለቤቴ ከ 32,000 በላይ የምግብ አይነት ሰርታ መግባኛለች፡፡ ሆኖም ግን አንድም ቀን እነዚህን የምግብ ዝርዝሮች ለአንድ ጊዜም ቢሆን አስታውሻቸው አላውቅም፣ የማውቀው ነገር ቢኖር ግን ይህንን ነው፡- እነዚህ ምግቦች ተንከባክበውኛል፣ በሽታ እንዳያጠቃኝ ተከላክለውልኛል፣ ስራዬን በአግባቡ እንድሰራ ጥንካሬ ሰጥተውኛል፣ የነቃ አእምሮ እንዲኖረኝ አንቅተውኛል፡፡ ባለቤቴ ዛሬ በዚህ ጤንነት እንድቆም ያደረገኝን ምግብ ባትመግበኝ ኖሮ በህይወት ባልኖርኩና በሞትኩ ነበር ፣ አይነታቸው ትዝ ስላላለኝ ጥቅም የላቸውም ልል ይገባኛልን? ለዛሬ መኖሬ ምክንያት ባለፈው 30 አመታት የተመገብኳቸው ግን አሁን ትዝ የማይሉኝ ምግቦች ናቸው፣ ምግብ ሁሌም አዲስ ነው፣ የምንመገበውም እንደ አዲስ ነውና፡፡ ባልሞት እንኳን ንቁ ሆኜ ሰው የሚጠቀምበትን አገልግሎት ባላገለገልኩ እንደ አንተ አይነት ያሉትን ባልመከርኩ ነበር”
ልክ እንዲሁ ላለፉት ብዙ ጊዜያት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄጄ ባይሆን ኖሮ በመንፈሴ ሞቼ በኖርኩ ነበር፡፡ ዛሬ ቤተ ክርስቲያንን ተጠግቼ ህይወቴን እንድመለከት ባልሆንኩ ነበር፤ ሌላው ቢቀር እንኳን “ያሳለፍኩት አመታት ብክነት ይሆኑ እንዴ” ያስባለኝ ቤተ ክርስቲያን መመላለሴ ነው፡፡ የሰማኋቸው፣ ያነበብኳቸው የቃል ምግቦቹ በዝተው ዛሬ እንድቆም አድርገውኛል፡፡ ጥቅሜን ማየት ተስኖኝ እንጂ ለካ ዛሬ በመንፈሴ ጤናማ ሆኜ የቆምኩት ባለፉት 30 አመታት የተመገብኳቸው አገልግሎቶች ናቸው? የዛሬ 20 እና 25 ዓመታት የተማርናቸውን ትምህርቶች ላናስታውሳቸው እንችል ይሆናል፡፡ ዛሬ መልካም አእምሮ እንዲኖረን ያደረጉት፣ ኃጥያት ስንሰራ የሚገስፅ አእምሮ እንዲኖረን ያደረጉት እዚህ በመመላለሳችን ያገኘናቸው ሀብቶች ናቸው።
ለምንም ወደታች ስትወርድ እግዚአብሔር ለአንድ ነገር ወደ ላይ ያወጣሃል፡፡ የወረድክ ቢመስልህም አትመን ጌታ ወደ ላይ ለጥቅም ያወጣሃልና፡፡ በቤቱ ያለ ትርፍ እየተመላለስክ ያለህ አይምሰልህ ሽልማት ላይ ደርሰሃልና፡፡ እምነት የማይታየውን ያያል፣ የማይታመነውን ያምናል፣ የማይቻለውን ይቀበላል፡፡ ሴጣን ከቤ/ክ እንድንቀር፣ ፀሎት እርግፍ አድርገን እንድንተው ሲፈልግ ነው ያንን ማድረጋችን ምንም ጥቅም እንደሌለው ደጋግሞ ያሳስበናል። በቤቱ መመላለሳችን ግን ጥቅም አለው በረከት አለው። ማንም የአንድ ባለፀጋ ቤት ተጋብዞ ሄዶ ሳይበላ ሳይጠጣ ሚመጣ የለም፣ እኛም ከሁሉ የሚበልጠው ባለፀጋው የመድህን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤት(ቤተክርስቲያን) ኑ ብሎ ጠርቶን ሄደን ባዶአችንን ፍፅም አንመለስም። ለእኛ አሁን ጥቅሙ ባይታየንም የመንፈስ ቅዱስ በረከት ግን እያደረብን ይሄዳል።
በቤቱ ፀንተን ለዘለዓለም እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን!