መልካሙ አምላካችን እግዚአብሔር የሰዎችን መልካም ሥራ ሁሉ አይዘነጋም ጥቂት ብትሆንም እንኳ።
እርሱ በመልካም ምድር ላይ ከወደቀች በኋላ ሠለሳ ስድሳና መቶ እጥፍ ፍሬ ስለምታፈራው መልካም ፍሬ አስተምሯል። አምላካችን እዚህ ላይ ሠላሳ ፍሬ ያፈራችውን ዘር ከመልካም ዘር ነው የቆጠራት። እርሱ ሠርክ አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መጥተው የተቀጠሩትን ሠራተኞች ተቀብሏል። (ማቴ 20፥9) ከእርሱ በስተቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ የተቀበለው በሕይወቱ የመጨረሻ ሰዓት ውስጥ ነበር። (ሉቃ 23፥43) እርሱ ታናናሾች ለተባሉት ሰዎች በደቀ መዝሙሩ ስም ቀዝቃዛ ውኃ ወይም ጽዋ ያጠጣ ዋጋውን እንደማያጣ እውነት እላችኋለሁ ብሎ በማሳሰብ ተናግሯል። (ማቴ 10፥42) የእርሱ መልካምነት ሦስት ዓመት ተመላልሶ ምንም ፍሬ ላላገኘባትን በለስ ሊያስቆርጣት ባዘዘ ጊዜ ጠባቂዋ በመካከል በአስታራቂነት ገብቶ "......ጌታ ሆይ ዙሪያዋን እስክኮተኩትላት ፋንድያ ስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት ወደ ፊትም ብታፈራ ደኀና ነው ያለዚያ ግን ትቆርጣታለህ። (ሉቃ 13፥8-9) በማለት እንዲናገር ፈቅዶለታል።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ!

August 31, 2019
አቤቱ ተወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን ፡ የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ፡ ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን፡ እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
ጌታችን ሆይ ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ፡ ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን ፤
ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን ፡ የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ ፡ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ)