…የነብያት ሀገራቸው ቤተልሄም ሆይ ደስ ይበልሽ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ባንቺ ዘንድ ተወልዷልና። የቀድሞውን ሰው አዳምን ከምድር (ከሲዖል) ወደገነት ይመልሰው ዘንድ አዳም ሆይ መሬት ነበርክና ወደመሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ፣ ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚአብሔር ፀጋ ትበዛለች። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።
“እርሱ ሰው የሆነው እኛን አማልክት ዘበጸጋ ያደርገን ዘንድ ነው፤ ከሴት፣ ከድንግል የተወለደው በስህተት ላይ የነበረውን ትውልዳችንን ያስቀርልንና ከዚያ ወዲህ የተቀደስን ዘሮች እና የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ነው፡፡” ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ