August 30, 2019
ነሐሴ 24
አቡነ ተክለሃይማኖት
ድካም በማብዛት እንደ ነቢያት፣ ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት፣ በመገረፍ እንደ ሰማዕታት፣ አጥንቱ ከስጋው ጋር እስኪጣበቅ ከሰውነቱ ማለቅ ብዛትና የሚያቃጥለውን ላብ እንደ ደም ዥረርታ በማፍሰስ፥ ከስግደቱ የተነሳ የሰውነቱ መለያ እስኪቆጠር ድረስ ተባህትዎን በመያዝ እንደ መነኮሳት ሆኖ መንፈሳዊ መገዛቱን ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ። አይን እያለው እንደማያይ፣ ጆሮ እያለው እንደማይሰማ፣ ክረምትና በጋን ሳያያቸው 8 ጦር ዙሪያው ተክሎ የእግሩ አገዳ እስኪቆረጥ ድረስ ያለ ምግብ ያለ ውሃ ቅጠል እንኩአን ሳይቀምስ በፅኑ ተጋድሎ እንባውን እያፈሰሰ በብዙ የደከመ። ብጹዕ አባታችን በህመም በተያዘ ጊዜ በመንፈስ ልጆቹ የሆኑ ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም ተሰብስበው ብዙ አለቀሱለት፡፡ አባታችንም ‹‹ልጆቼ አታልቅሱ ነገር ግን የሽማግሌውን ቃል ስሙ ከሁሉ አስቀድሞ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ ልጆቼ ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንግዲህ ወዲ ግን ተሰናበትኳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅሩ የክብሩም ባለቤትነት የረዳትነቱም ሀብት ዘወትር ከእኔና ከሁላችሁም ጋር ለዘላዓለሙ በእውነት ይኑር፡፡›› በማለት እንደዚህች ባለች እለት በምግባር ፍጹም የሆነ ተጋድሎው የበዛ ትሩፋቱ ያማረ፣ ሌሊትና ቀን በመቆም እግሩ የተሰበረ፣ በክረምትና በበጋ ውርጭ መልኩ የጠቆረ፣ በጌታችን ስም ደም ተቀብቶ ሰማዕት የሆነ፣ የዓለም ፀሐይ የትምህርት ብርሃን ብጹዕ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት በተወለዱ በ 99 ዓመት ዐረፉ፡፡
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
ነሐሴ 24 እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እረፍቷ ነው። እርሷ በሁሉ ጎዳና ፍጹምነትን ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት። ገና ከልጅነት የነበራት የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው::
ከተባረከ ትዳሯ 12 ልጆችን አፍርታ ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ አድርጋ ኑራለች። በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት ደርሳለች። አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇ ዳግማዊ ቂርቆስን አዝላ ምናኔ ወጥታልች።
በደብረ ሊባኖስ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን የፈጸመችው ግን ጣና ሐይቅ ውስጥ ነው። በተለይ ለ22 ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ ዓሣ በሰውነቷ ውስጥ እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች። በቀኝና በግራ 12 ጦሮችን ተክላም ጸልያለች።
ብዙ ኃጥአንን አማልዳ 12 ክንፎችን አብቅላ ከፍ ከፍ ብላለች። ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኳ ለማስታረቅ ሞክራለች። ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ ፈቅዶላታል። ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት ሲሆን አጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም (ጣና ዳር) ይገኛል።