Friday 14 February 2020

Image result for የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የታቦት ቀኖና


የሐገራችን ታቦት የጥንቆላና የአስማት መስሪያ እንደሆነ አውደ ነገስት ወፍካሬ ከዋክብት የተባለው መፅሐፍ ሲያጋልጠው

ጸሎት በእንተ መፍትሔ ሥራይ ዘይትነበብ በዕለተ እሑድ።

ኪን ወእደ ሰብእ ጠቢብ ወነሐቢ ብእሲ አው ብእሲት ሐበረደጁን ምርታዶ ምርታዶ አክሎግ አክሎክ ኤፍዛዜዎን ኤፍዛዜዎን ሐረጅ ሐረጅ ዶር አላዶር ሔጅረጅ ሔጅረጅ በስመ ሐበረዶን አንተ ውእቱ ሥራይ ተፈታሕ ሥራየ ፍቍራን ወደብተራ ሥራየ ብእሲ ወብእሲት ሥራየ አረሚ { ወክርስቲያን }ዘተገብረ በመብልዕ ወበመስቴ ወዘይገብሩ ሥራያተ እኩያን መሠርያን ሰማየ ነጺሮሙ ወምድረ ጐድጕዶሙ {→ ታቦተ ገሢሶሙ} ወዕጣነ ወጊሮሙ ስብሐ አጢሶሙ ወአንቆቅሖ ደጊሞሙ ሰርዶ ወአሥዋር መሊሖሙ ወከርካዐ መቲሮሙ ዘንተ ኵሎ ዘይገብሩ ፍታሕ ሥራያቲሆሙ ወሰዓር ድጋማቲሆሙ ከመ ኢይቅረቡ ኀበ መንገለ ሥጋሃ ወነፍሳ ለዓመትከ......... ለዓለመ ዓለም አሜን።

( አውደ ነገስት ወፍካሬ ከዋክብት ገፅ 170)

በመብልና በመጠጥ የተደረገን የወዳጅ የደብተራ አስማት ፣የወንድና የሴት አስማት ፣የአሕዛብና የክርስቲያን አስማት ፍታ ፣ ዋርካ ቆርጠው ሰርዶና ቅጠል ምሰው ፣ ስብ አጢሰው ፣እጣን አሳርገው ፣
{{ ታቦት ዳስሰው}} ፣መሬት ቆፍረው ሰማይ አይተው ክፉ አስማተኞች ያደረጉትን ሁሉ ይህን አስማታቸውን ፍታ ድግምታቸውን ሻር ወደ እከሊት ስጋና ነፍስ እንዳይቀርቡ ለአመትከ እገ ___ ከዓለም እስከ ዓለም አሜን

አምላክ ባላዘዘው መልኩ በተለያዩ ፃድቃንና መላዕክት ስም ተሰይሞ በየ ቤተ መቅደሱ ተቀምጦ ለዚሁ ለድግምት አገልግሎት የሚውለው ይህ ታቦት በእርግጥ ክጥንቆላና ከአስማት ስራ ውጭ ፍይዳ የለውም የታቦት ዋነኛ ጥቅሙ ጥንቆላና አስማት መስሪያ ብቻ ነው ወገኖቻችን ልትነቁ ይገባል ።

No comments:

Post a Comment