Monday 17 February 2020

ተአምረ ኢየሱስ 15ኛው ተአምር "" ከለታት በአንደኛው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከልጆች ጋር ሲጫወት : ከልጆቹ መካከል አንዱ ወድቆ ሞተ :: ሌሎቹ ልጆች የልጁን መሞት አይተው ሲሸሹ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶ ግን በዚያው ቦታ ላይ ብቻውን ከሙዋቹ ልጅ ጋር ቀረ :: የሞተው ሰው ቤተሰቦች መጥተው ሲመለከቱ ልጃቸው ሞቷል : ኢየሱስም አጠገቡ ነበር :: በዚህን ጊዜ ልጃችንን የገደልከው አንተነህ አሉት :: ኢየሱስም እኔ አልገደልኩትም አላቸው :: ሰዎቹም አማላካችን ኢየሱስን ብዙ በዘበዘቡት ምርመራም ባበዙበት ጊዜ ኢየሱስም ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ ዜኑ ዜኑ (የልጁ ስም ነው ዜኑ) እኔ ገድዬካለሁ ብሎ ከሞት ተነስቶ እንዲመሰክር በታላቅ ቃል ጠራው :: የሞተውም ልጅ ተነስቶ ጌታዬ ሆይ አንተ እኔን አልገደልከኝም ብሎ መሰከረ :: የልጁም ቤተ ሰቦች ፈጸመው አደነቁ :: እርሱ ብቻውን ታላቅ ተአምራትን ያደረገ : ከልኡላን ይልቅ ልኡል ነው በማለት እግዚአብሔርን አመሰገኑ :: ይቅርታውና ቸርነቱ ለሁላችን ይደረግልን ይላል :: አሜን ይደረግልን :: የእኛ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህንን ነው የሚናገሩት :: አሁንም በቀጥል የተለይ ነገር አታዩም :: ከቅድሙ የቀጠለ እስቲ አንድ ነገር ልጨምርላቹ ( ከላይ የቀጥለ ነው ) :

No comments:

Post a Comment