Tuesday 11 February 2020

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሐፍ አስመረቀች

‹መጽሐፈ ቅዳሴ -ክታበ ቅዳሴ- Kitaaba Qiddaasee
                                               ‹መጽሐፈ ቅዳሴ -ክታበ ቅዳሴ- Kitaaba Qiddaasee
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሐፍን መጋቢት 10 ቀን 2008  ዓ.ም  በእሊሌ ሆቴል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፤ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት  ፤የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስና  የተለያዩ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎችና   በተገኙበት   በደመቀ  ሁኔታ  አስመረቀች።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
መጽሐፈ ቅዳሴው የቋንቋው ተናጋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በቀላሉ እንዲረዱትና እንዲያስቀድሱ  በሦስት  ኮለን የተዘጋጀ ነው።ባለ ሦስት ዓምዱ (ኮለም) መጽሐፈ ቅዳሴ፡- የመጀመርያው ረድፍ በግእዝ ቋንቋ፣ ሁለተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በሳባ (ግእዝ) ፊደል፣ ሦስተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በቁቤ ፊደል ተጽፏል፡፡ ይህ ሁሉ ነገር እንዲሰራ  ኃይሉን ለሰጠ  ፈጣሪ  እንደ ቅዱስ ዳዊት “ ምንተኑ አዐሥዮ ለእግዚአብሔር  በእንተ ኵሉ  ዘገብረ ሊተ”  መዝ115÷3 በማለት ማመስን ይኖርብናል ፡፡
 10 ዓመታት ያህል በፈጀው በዚህ የትርጉም ሥራ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን  እንድሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተሳትፈውበታል።
መጽሐፈ ቅዳሴው  516 ገጾች ያሉት 14ቱን   ቅዳሴ  ያካተተ መሆኑም በምረቃው ዕለት  ተነግሯል። “ አዝልፍኬ አንብቦተ   መጻሕፍት  እስመ እማንቱ  ይመርሃሁ  ለልብከ  ኀበ አንክሮተ   እግዚአብሔር ፤ መጻሕፍትን አዘውትረህ   አንብብ     መጻሕፍት  እግዚአብሔርን  ወደ ማድነቅ   ልብህን  ይመሩታልና”  ማር ይስሐቅ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በምረቃ ሥነ -ሥርዓቱ ላይ “  ቤተ ክርስቲያን   ልጆቻቸን  በቋንቋቸው   አምለካቸውን  ማመስገን ይችሉ ዘንድ  ማስተማርና  ለእግዚአብሔር  መንግሥት  ማዘጋጀት  ተቀዳሚ  የቤተ ክርስቲን ተግባር  ነው ”  በማለት  ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ዐቀፍ ሆና በእኩልነት የምታገለግል መሆኑን  ጭምር ገልጸው፥ በቀጣይ በሌሎች ቋንቋዎች እንዲህ ዐይነቱ   ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
‹መጽሐፈ ቅዳሴ -ክታበ ቅዳሴ- Kitaaba Qiddaasee
‹መጽሐፈ ቅዳሴ -ክታበ ቅዳሴ- Kitaaba Qiddaasee

ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ  (የጠቅላይ ቤተክህነት  ዋና ሥራ አስኪያጅ  የወላይታ  ኮንታናየዳውሮ  አህገረ ሰብከት ሊቀጳጳስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን    ሊቃውንት  ባቖዩትና  ባዘጋጁት  የትርጉም ስልት  መጻሕፍትን መተርጎሙ  በየጊዜው ከሚበረዘውና  ከሚከለሰው የተርጉምና የአስተሳሰብ ስህተት ይጠብቃል” ብለዋል ፡፡
 ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ
ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ
አባ ኃ/ማርያም  መለሰ(ዶ/ር)  “ በኦሮሞኛ   ቋንቋ  የተተረጎመው  የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሐፍ  ለዘመኑ  ትውልድ  መልስ የሚሰጥ  አስፈላጊ ወቅታዊ ነው ” ብለውታል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን   ሥርዓተ ቅዳሴ መጽሐፍን   በ1918 ዓ.ም   ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲሆን   በ1956 ዓ.ም በዐረበኛ  በ1946 ዓ.ም በእንግሊዘኛ ፤ በ2008 ዓ.ም  በአፋን ኦሮሞ  ተተርጉሞ  ለአገልግሎት እንዲውል አድርጋለች  ፡፡
በ1998 ዓ.ም   በጥቅምት ወር በተደረገው  የቅዱስ  ሲኖዶስ  ምልዓተ ጉባኤ ላይ የምዕራብ ወለጋ  ሀገረ ስብከት  ሊቀጳጳስ   ብጹዕ አቡነ ሔኖክ  ባቀረቡት ጹሐፍ “ እኛ የተሾምንበት  ዋና ዓላማ  ልጆቻችን  በሚሰሙት ቋንቋ   አስተምረን  ከእግዚአብሔር መንጋ ለመቀላቀል ና ልጆቻችን  ለመጠበቅ  ነው ፡፡  እኔ በተሾምኩበት ሀገረ ስብከት ያሉት ቤተ ክርስቲያን  ልጆቻቸን   የቀደሙት አባቶቻቸው   ሃይማኖቱን  ቢያቆዩላቸወም  በአሁኑ ወቅት ግን  ወጣቱና ተተኪው ትውልድ   የአስኳላውን ትምህርት  በአፍ -መፍቻ ቋንቋቸው  በአፉን ኦሮሞ  ስለሚማሩ  የሚፈጸመውን የአምልኮ ሥርዓት  ሊሰሙ ባለመቻላቸው  እያጣናቸው  በመሆኑ  የሥርዓት አምልኮ  መጻሕፍት  በአፋን   አሮሞ   መተርጎም   እንዳለበት  ቅዱስ ሲኖዶስ  በጉዳዩ ላይ  በጥልቀት ተወያይቶበት  ሊወስን ይገባል ”  በማለት አሳስበው  ነበር
ብጹዕ አቡነ ሔኖክ
ብጹዕ አቡነ ሔኖ                                                                                                    ነብዩ ቅዱስ ዳዊት   በመዝ.118÷126 “ ጊዜ ገቢር  ለእግዚአብሔር  ያለውን   ኃይለ ቃል  ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡  በተጨማሪም  በማኀበረ ቅዱሳን ኀትመትና ኤሌክትሮኒክስ   ሚዲያ ዋና ክፍል   በኦሮሞኛ  ቋንቋ ዳንጋልቡ(DhangaaLUbuu) ወይም” የነፍስ ስንቅ” የሚል ስያሜ የተሰጣት  መጽሔትም  እየተዘጋጀች  ለምእመናን  በመሰራጨጥት ላይ ትገኛለች፡፡
DhangaaLUbuu
DhangaaLUbuu
                                            ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ ወለሊቃውንቲከ   ይዜንዉከ
                     ምንጭ መክስተ ልሳን ዘአፋን ኦሮሞ መጽሔት (Ifa Hiikka  Mullata Afaan Oromoo)

No comments:

Post a Comment