Sunday 23 February 2020

✥ይቅር ማለት አሸናፊነት ነው ይቅርታ መጠየቅ ብልህነት ነው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አስተማሪ ጽሁፍ እንሆኛ ያንብቡ ።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥የደብብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ በነፃነት ትግል ወቅት ታስረው ነበር ጊዜ በኋላ ትግሉ ውጤታማ ሆኖ ማንዴላ የደብብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ከሆኑ ከጊዜ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።

✥አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።

✥ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማንዴላ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ።

✥እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማንዴላ "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ።

✥ የግል ምልከታ የሰው ልጅ ሁል ጊዜ ልክ አይሁንም ሁሌም አይሳሳትም ይቅር የማይል ሰው እርሱ ጊዜ ደርሶ ሁኔታዎች ገጥመው መሳሳቱ አይቀርም እና ይቅር ባላለ ልቡ ይቅርታን አይጠይቅም ቢጠይቅም ፍጹም ሰላም አይሰማውም። ይቅርታ ማድረግ የሕሊና እረፍት ነው ይቅር አለማለት የክፋት እስር ቤት ነው ። ይቅር የምንል ከሆነ ብናጠፉም ይቅር ለመባል ለወደፊቱ ተስፉ አለን ከሰው በናገኝው እንኳን ፍጹም ማህሪ ከሆነው አምላክ ምህረት ይገኛል ። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና ይቅር ማለት አሸናፊነት ነው በፈጣሪ ዘንድ ምህረት ምናገኝባት ።

✥ይቅርታ መጠይቅ ውርደት ሳይሆነ ብልህነት ነው። በጥፋታችን ያጣነውን ጉደኘ ፣ ተአማኝነት፣ የበጠስነውን የሕይወት ገመድ ዳግም ለማሰር የምንጓዝበት መንገድ ነው።

ሰዎች ሁላችን ይቅርታ ባንጠይቅ የተጠየቅንም ይቅር ባንል የሰው ልጆች ሁላችን በአንድ ላይ መኖር አንችልም ምክያቱም አውቆንም ይሁን ሳናውቅ እንበድላለን እንሳሳታለን ታዲያ በዚህ መሃል ይቅርታ የማንጠይቅ ስንጠየቅም ይቅር የማንል ከሆነ እንዴት መኖር እንችላለን ። እስራኤላውያን በመሴ ክፉ አስበው በድንጋይ ለሚግሩት ቢነሱ እርሱ በኃጢአታቸው እንዳይጠፉ ይቅር ብሎ ምህረት ይለምናል ።
ጌታችን ላይም አይሁዶች በክፉት እሮማዊያን ጨክነው በስቅሉት ጊዜ እርሱ ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ በደላቸውን ሳይቆጥር ይቅር ብሎ እኛ ይቅር እንድል ምሳሌ አርያ ሆኖ አሳይቶናል የፈለገ ብንበደል ፣ በንገፋ፣ በንሰደብ ፣በንመታ በጌታችን ላይ ከደረሰው የበለጠ መከራ አልደረሰብንም እና እርሱን አረያ አብነት አድርገን ይቅር እንበል ይቅር እንድንባል ማቴ 6:14-15።

ሀገር ትዳር ጓደኝነት የሚቀጥሉት ይቅር በማለት እና ይቅርታ በመጠየቅ ነው።

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

በቴሌ ግራም መዝገበ ሃይማኖት ወይም @mezgebehaymanot ይቀላቀላሉ 🤳

beletekebede03@gmail.com

ጥቅምት 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment