​ስንክሳር ዘውርኀ መጋቢት አምስት 
ገፅ17—25
562 አመት ሳይመገብ የቆው የኢትዮጵያን ህዝብ ሃጢያት ያስማረና ስላሶችን ያዘለው  የአባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእረፍት ቀን መታሰቢያ 
ብዙወቻችን ይህን ሰው በፎቶ እናውቀዋለን
 ታሪኩ ረጅም ስለሆነ አጠር አድርጌ ነው ያቀረብኩት 
 በተወለደበት ቀን ከናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣኸኝ እያለ ለስላሴ ሰገደ ስላሴም የአንድነቱና የሶስትነቱን ሚስጥር እንደሚያሳዩት ቃል ገቡለት 
 ሶስት አመት ሲሞላው ገብርኤል ከእናቱ እቅፍ ተቀብሎ ብዙ ባሕታዊያን በሚኖሩበት ገዳም አስገባው 
ከዚያም ተምሮ ዲቁና ተቀበለ 
ከዚያም በበርኀ ብዙ ተጋድሎ አደረገ አንድ ቀን እየሱስ መጥቶ የብርሃን ሰረገላ ሰጠው ወደ ኢትዮጵያ ምድር እንዲሄድ አዘዘው ከዚያም በስልሳ አንበሳና በስልሳ ነበር ታጅቦ ኢትዮጵያ ገባ ዝቋላ እንደደረሰ በአራቱም አቅጣጫ ሲያይ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰሩትን ኃጢያታቸውን በዐይናቸው ፊት የተገለጠ ሁኖ አየ 
ከዚያም በራሱ ተዘቅዝቆ ተወርውሮ (ዳይቭ) ወደ ባህሩ ገባ በእጅህ የፈጠርካቸውን እነዚህን ህዝቦች ካልማርካቸው ከዚህ ባህር አልወጣም ብሎ አርባ ቀን አርባ ለሊት ቆየ ስምህን የጠራ መታሰቢያህ ያደረገውን እምርልሃለው የሚል መልዕክት መላዕክ መጥቶ ነገረው አባታችንም መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ካልማርክልኝ አልወጣም ብሎ ለመልአኩ ነገረው አባታችንም በዚያ ባህር 100 አመት ስጋው አልቆ በአጥንቱ ብቻ በባህሩ ውስጥ ኖረ ሰባት መቶ ሽህ ሶስ መቶ ሚሆኑ አጋንንት በቀስትና በድንጋይ ወጉአቸው 
ከዚያም እየሱስ ባህሩ ዳር ቆሞ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ምሬልሃለው ውጣ አለው አባታችንም አጥንቶቹ እንደ ወንፊት ተቀዳዶ ወጣ
ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሐይ በላይ ከሰማይ በታች ሰባት አመት ኖረ ዳግመኛም ወደ ምድር ወርዶ እንደ አምድ ተተክሎ ሰባት አመት ተተክሎ ኖረ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ መጥቶ ሁለት አይኑን አንቁሮ አሳወረው እስከ ሁለት ሳምንትም ምንም ሳይንቀሳቀስ ቆሞ ፀለየ 
ገብርኤልና ሚካኤል መጥተው አይኑ ላይ እፍ ሲሉበት አይኑ እንደቀድሞ ብርሃን ሆነ ወደ ዝቋላ ሲሄድ ሶስት ሽማግሌዎችን አገኘ አዝለህ ውሰደን ብለው ለመኑት ሲጠጋቸውም ሁለመናቸው የደከመ በሽበት የተከበቡ ሁነው አገኛቸው 
አባታችንም እናተ አረጋዊያን ከወዴት ናችሁ ብሎ ጠያቃቸው እነሱም ተነስተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሃም እንዳየ አያቸው ተንቀጥቅጦ መሬት ላይ ወደቀ 
አንድ ጣኦት አምላኪ ንጉስ ጋር ተገናኝቶ ጣኦቱ አቡየን ሲያይ ተሰበረ የንጉሱ ሰራዊትም አደነቁት ንጉሱ ይህን አይቶ ስለተቆጣ ያደነቁትን ገድሎ እሳቸውን ሊገድል ከቀረው ሰራዊት ጋር ሲመጣ በታላቅ መብረቅ ተመቶ ከነ ሰራዊቱ ጠፍ ከንጉሱ ጋር አራት ሽህ ሰዎች ሞቱ አየሱስ መጥቶ እነዚህ የኔም ያንተም ጠላቶች ናቸው መላዕክት ወደ ሲኦል እንዲዎስዷቸው አዘዘ አባታችንም እነዚህን ማርልኝ ሲለው እየሱስ ከሱ ተሰወረ 
አባታችንም እግሮቹን በገመድ አስሮ በገደል ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ ሰይጣን መጥቶ ገመዱን ቆረጠው ወደ ታች ተወርውሮ ወረደ ሚካኤል መጣቶ ያዘውና በራሳህ ላቁምህ ወይስ በግር ሲለው በራሴ አቁመኝ አለው አባታችን በጥርሱ ዲንጋ ነክሶ እስከ ሰላሳ አመት ኖረ ከሰላሳ አመት በኃላ እየሱሰ መጥቶ አባታችን ጠራው እነሆ እነዛን ከሃዲዎች ምሬልሃለው አለው በሽተኛን እንዲፈውስ ሙታንን እንዲያስነሳ ስልጣን ሰጠው 
በእድሜው መጨረሻ እየሱስ ተገልጦ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እስከ አስራ አምስት ትውልድ ምሬልሃለው አለው የእድሜው ዘመን አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን አረፈ 
እግዚአብሔር ከጥፍት ውሃ በኃላ የሰው ልጅ እድሜ ስንት ይሁን ነበር ያለው የሰውልጅ መንግስተ ሰማያት ሚገባውስ በምንድን ነው ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር አስታርቁልን !!