Monday 31 December 2018

የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን ክፍል አንድ ትምህርት የትምህርት ርዕስ ፦ የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖችና የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ ተባረኩ እንደሰማችሁትና እንደተከታተላችሁት ጌታ አጃቢዎች እንድንሆን ሳይሆን ትክክለኛ የራሱ ደቀመዛሙርት እንድንሆን ስለፈለገ ይህንን መሠረታዊ ትምህርት በትምህርቱ የመነሻ ክፍለጊዜያችን ላይ ሰጥቶናል :: ዓለምን እንደኖህ በጽድቅ የምንኮንን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንድንሆን ራሳችንን ለጸጋው ባለቤት ለእግዚአብሔር በማስገዛት ጸጋውን ተቀብለን ወደዚህ ሕይወት ልንመጣ እንደምንችል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካኝነት በጽኑ ተናግሮናል :: ያገለገለንን የእግዚአብሔር ሰው መምህር ጌታቸው ምትኩን ጌታ እግዚአብሔር ይባርከው ለማለት እፈልጋለሁ ትምህርቱ እንግዲህ ሰኞ ሰኞ ሁልጊዜ በዚሁ ሰዓት ይቀጥላል :: ይህንንም ትምህርት ለሰዎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ :: ሰዎችን መጋበዝ አትርሱ :: ጌታ እግዚአብሔር የሳምንት ሰው ይበለን ቸር እንሰንብት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከተሃድሶ አገልግሎት

Thursday 27 December 2018

የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ከዚህ በመቀጠል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ምክንያት በማድረግ አሁንም በድጋሜ መልዕክትን ወደ እናንተ ይዤ ቀርቤያለሁና ተከታተሉ የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና የዕለቱ የምንባብ ክፍል ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ( የማቴዎስ ወንጌል 2: 1 - 2 ) 1ኛ ) እነዚህ ሰዎች ሊሰግዱ መጥተው የቀሩ አልሆኑም ፣ ንጉሥ ሄሮድስም አላስቀራቸውም ፣ ኢየሱስ ጋር መጥተው ሰገዱለት ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት ( የማቴዎስ ወንጌል 2 : 11 ) 2ኛ ) ኢየሱስ ከተወለደ ጀምሮ ንጉሥ ነው ደግሞም የሚሰገድለት ነው :: ከሞት ተነስቶና ሞትን አሸንፎ ብቻ አይደለም የተሰገደለት በታንኳይቱም የነበሩት፦ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 14 : 33 ) እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 9 ) እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ( የሉቃስ ወንጌል 24 : 52 ) በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ ( ራዕይ 5 : 11 - 14 ) 3ኛ ) ኢየሱስን አንጠራጠረው ፣ ንጉሣችንና አዳኛችንም ነውና አንካደው ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 17 ) ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት ( የማርቆስ ወንጌል 15 : 19 ) ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል 2ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 12 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 20 December 2018

በመምህር ጌታቸው የተዘጋጀ ትምህርት ነበረ በኮኔክሽን ምክንያት ቢቁዋረጥም ጌታ በመንፈሱ ያካፈለን መልዕክት ነበረ ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን መምህር ጌታቸው ምትኩ የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት ለመስጠት በሰዓቱ ተገኝቶ ነበር ነገር ግን በኮኔክሽን ችግር ምክንያት በዕለቱ ሊያስተላልፍልን ይዞት የመጣውን ትምህርት ማስተላለፍ አልቻለም በሚቀጥለው ጊዜ ጌታ ረድቶን በሚኖረን ፕሮግራም ያለምንም ችግር ለተከታታይ ሳምንታት ሳይቋረጥ እናስተላልፋለን ብለን እናምናለን ወንድማችን እንደምታውቁት ለማስተማር ከኢትዮጵያ ነውና የሚገባው የሃገራችንን የኔት ወርክ ሁኔታ ደግሞ ታውቁታላችሁና በጣም አስቸጋሪ ነው ለወደፊቱም ያለምንም ችግር የተዘጋጁበትን ትምርቶች እንደሚገባ እንዲያስተላልፉ ከኢትዮጵያ ለሚገቡ አገልጋዮችም ሆነ እዚሁ ላለነው ለእኛም ጭምር አብዝታችሁ ጸልዩልን ለማለት እወዳለሁ ይሁን እንጂ ጌታ መልዕክት ስለነበረው በሚደንቅ ሁኔታ ቃሉን በመንፈስቅዱስ አማካኝነት አስተላልፎልናል መልዕክቱ የሚጠቅማችሁ ስለሆነ ደጋግማች በማስተዋል ስሙት ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 19 December 2018

Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...ይህቺ ናት ርትዕቷና ቀጥተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ተብላ የሚፎከርላት እንግዲህ :: መጨረሻዋ ይሄ ሆነ :: ጉድ አይሰማም አይባልምና አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የማይከበሩባት ፣ ጉሮሮአቸው ታንቆ የሚደበደቡባት ፣ መንፈሳዊ መሪዎች የማይከበሩባት እና የማይደመጡባት ፣ ሊያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አረጋዊ አባትና የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የተደበደቡባት ቤት ሆነች :: ወገኖቼ የእስራኤል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ፣ አናቂ ቁጥር 1 ሽፍቶች መነኮሳትን እስር ቤት ባይወስድ ፣ በቤተመቅደሱ ውስጥም የነበረውን ድብድብ ባያስቆም ፣ ጉሮሮአቸው የታነቀው ምስኪኑ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ለሕልፈተ ሕይወት በተዳረጉ ነበር :: ወገኖቼ እስቲ አንድ ጊዜ ይህንን ሁኔታ ቆም ብላችሁ አስቡት የራስ ሀገር ባልሆነ በኢየሩሳሌም ከአንድ ትልቅ ገዳምና የኃይማኖት ተቋም ይሄ ድርጊት ሊፈጸም ይገባልን ? የሦስት ሺህ ዓመት ክርስትና አለኝ የምትለዋ ይህቺ ቤተክርስቲያንስ በዚህ አሳፋሪ ጉዳይ ስሟ በዓለም ዙርያ ሊናኝና ሊነሳስ ይገባ ነበር ? ታድያ ለዚህ እኮ ነው እኛም አፋችንን ሞልተን አሁን ላይ ላለችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ ያስፈልጋታል የምንለው :: በሆሴዕ 4 ፥ 6 - 8 በተጻፈው ቃል መሠረት ከምዕመኖችዋ በፊት ያሉት ካህናትዎችዋ በደሙ የተገኘውን የኃጢአት ሥርየት ለማግኘት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በነፍስ ወከፍ የግል አዳኛቸው አድርገው ዛሬ ነገ ሳይሉ እና ሳይሞቱ በምድር ላይ አሁኑኑ ድህነትን ተቀብለው ቢገኙ ፣ የዳነ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላኩም መንፈስ የታጠበ ፣ የተቀደሰና የጸደቀ ስለሆነ ዓመጸኛ ተሳዳቢ ሴሰኛ ነጣቂ ተደባዳቢ ገዳይና የመሣሠሉትን አይሆኑም በ2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 9 - 11 የተጻፈውን ቃል በማስተዋል እናንብበው :: ቀራጩ ዘኬዎስ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ በቀረጥ ሰብሳቢነቱ አሁን ከዘረዘርኳቸው ተርታዎች የተመደበ ሰው ነበር :: ነገር ግን ኢየሱስን ይዞ ወደ ቤቱ በመግባት ዘኬዎስ ግን ቆሞ ይለናል ቃሉ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆነ አራት እጥፍ እመልሳለሁ ሲል ልባዊ ኑዛዜውን እንዳቀረበና ኢየሱስም አሁን ለቤቱ መዳን እንደሆነለት አውጆ የአብርሃም ልጅ ነህ እንዳለው እንመለከታለን የሉቃስ ወንጌል 19 ፥ 1 - 10 :: ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል እንደሚል ቃሉ ሮሜ 4 ፥ 5 የሚያስደንቀው እውነት ኢየሱስ ስለበደላችን የሞተ እኛንም ስለማጽደቅ የተነሣ ነውና በእርሱ በማመናችን ምክንያት ብቻ እምነታችንን ጽድቅ አድርጎ ይቆጥረዋል ሮሜ 4 ፥ 22 - 25 :: ለዚህም ነው ዘኬዎስን እውነተኛ ንስሐ በመግባቱ ብቻ ተቀብሎ መዳንን የሰጠው :: ወገኖቼ ሆይ ጽድቃችን ወይም ሥራችንማ ይኸው አረጋዊ ጳጳስ ሳይቀር እስከ መደብደብ ደርሶ በእግዚአብሔር ፊት አላቆመንም :: ይኸው ታየ ኦኮ በቃ ! ስለዚህ ትምክህታችን ጽድቃችን ቅድስናችንና ቤዛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 30 እና 31 ን እንመልከት :: መልዕክቴን ስጠቀልለው አሁን ላይ ያለሽው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚበጅሽ አንድና አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ነውና ወደ እግዚአብሔር ቃል ፊትሽን መልሺ ስል በወንድማዊና አባታዊ ምክሬን ልሰጥሽም ሆነ ላስገነዝብሽ እወዳለሁ:: በኢሳይያስ መጽሐፍ እንደተጻፈው በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ በማለት ይናገራል ትንቢተ ኢሳይያስ 2 ፥ 2 - 5 ይመልከቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ከወንድሞቼ ጋር በመነጋገር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መሪነትን አገልግሎትንና ክህነትን ሌሎችንም ጉዳዮች መሠረት ያደረገ ሰፋ ያለ ትምህርት ይዘን በቪዲዮ ልንቀርብ እንችላለን :: እስከዚያው ግን ይህቺን መልዕክት በማንበብ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ለወገኖቼ ትቻለሁ :: ሌላው መናገር የምፈልገው ወንድምህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ ነውና ይሄ ውሽንፍር ወደ ወንጌላውያኑም ቤተክርስቲያን ከሞላ ጎደል ጎራ ያለ በመሆኑ ይፋ ሆኖ ባይገለጥም በአንዳንድ ደካማና ያልበሰሉ ፓስተሮችም ሆነ ነቢያት እየታየ ያለ ክስተት ሆኗል ስለዚህ በአጠቃላይ የክርስቶስ ስም በእኛ ምክንያት እንዳይሰደብ ሁላችንም ልናስብበት ይገባል የሚለውን ምክር ልሰጥ እፈልጋለሁ :: ጌታ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...

December 18, 2018 በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 12 ) አለማፈርስ ያለው ማንን በማመን ነው ? ማርያምን ወይስ ኢየሱስን ? ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርም የሚለውንና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤቴ ሆይ ከአንቺ ዘንድ ሽቶ የወደደውን ሁሉ ያላገኘ ማነው? በአንቺ አምኖ ያፈረ ማነው ? አንቺን ለምኖ ወደ ገሃነም ያወረድሽው ማነው ? ወደ ሠርግ ቤት ማለት ወደ መንግሥተ ሰማይ አገባሽው እንጂ የሚለውን በ2007 እትም ተአምር 41 : 25 እና በተአምር 43 : 23 - 25 ማግኘትም እንችላለን :: የተአምረ ማርያም መጽሐፍ በተለያየ ዓመተ ምሕረት የተጻፈ በመሆኑ እንደየ ዓመተ ምሕረቶቹ ምዕራፎቹና ቁጥሮቹ ይለያያሉ ተባረኩ በባለፈው ትምህርታችን ላይ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ ርኢክሙኑ ኦ አኃው "እስመ ኩሉ ዘረሰየ ትውክልቶ ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ ወላዲቱ ኢይትኀፈር " ወደ አማርኛው ሲተረጐም :--- ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ብሎን ነበር ( ተአምር 31 : 25 ) እምነታችን የመጣው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ስለሆነ የማናፍረው እምነታችንን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ አድርገን ሳይሆን በትንቢተ ኢሳይያስ  28 ፥ 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም ይላልና የማዕዘኑን ድንጋይ የሆነውን ኢየሱስን አምነን ነው ዛሬ ደግሞ በተአምር 33 ፥ 23 - 25 ላይ ኦ እግዝእትየ ቅድስት ድንግል በ፪ ማርያም መኑ ዘኀሠሠ እምኔኪ ወኢረከበ ኮሎ ዘፈቀደ ወመኑ ዘተወከለ ኪያኪ ወተኀፍረ ወመኑ ዘጸውአ ኀቤኪ ወሰደድኪዮ አፍኣ ዘእንበለ ዘአባእኪዮ ውስተ ቤተ መርዓ ይለናል ወደ አማርኛው ስተረጉመው በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤቴ ሆይ ከአንቺ ዘንድ ሽቶ የወደደውን ሁሉ ያላገኘ ማነው? በአንቺ አምኖ ያፈረ ማነው ? አንቺን ለምኖ ወደ ገሃነም ያወረድሽው ማነው ? ወደ ሠርግ ቤት ማለት ወደ መንግሥተ ሰማይ አገባሽው እንጂ በማለት ይህንን ቃለ ተናገረ ይህ ማለት ታድያ ሰዎች ከማርያም እንዳይሄዱና እንዲታዘዙላት ፣ እንዲያመልኩዋት ፣ እንዲሰግዱላትና እንዲገዙላት ስለ ራሷም ታላቅነት ጭምር እንዲናገሩ ነው ይህ የስሕተት መጽሐፍ የሚያስተምረው በዚህም ምክንያት እንግዲህ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ ደፍሮ ማርያም ማለት መንግስተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው አለን ( የዘወትር መቅ፡ቁጥር፡ 5 ) እመቤታችንን የቤተክርስቲያን ልጆች አክብሩዋት ለእናንተ ለኃጥአን መድኃኒት ስለሆነች ሳትጠራጠሩ በፍጹም ልባችሁ እመኑባት እርስዋ መድኃኒታችሁ ናትና አለን ( የዘወትር መቅ፡ቁ፡ 34 ) የካቲት 16ቀን አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበት የጻድቃን ማረፊያቸው ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ሰማይ አሳረጉዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያው ድረስ ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ሁሉ ተቀበሉዋት ከአጽማችን አንችን አጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግ/ር ምስጋና ይግባው እያሉም ሰገዱላት ባንቺ ደህንነትን አገኘን የአምላካችን ልጅ ካንቺ ተወለደ ከጥፋት የሕይወት ወደብ የሆንሽን እያሉም ሰገዱላት አለን (12ኛ ተአምር ቁ፡12 - 13) እመቤታችንን የዓለም ሁሉ መድኃኒት አድርጎ እንደፈጠራት ልብ አድርጋችሁ እነሆ እወቁ አለን (12ኛ ተአምር ቁ፡ 62) ልመናንና አምልኮንም በተመለከተ ደግሞ አንቺ ከሰማያውያን መላእክት ልዕልት እንደሆንሽ ከመሬታውያን ጻድቃንም የከበርሽ እንደሆንሽ ያውቁ ዘንድ ይደረግልኛል ብሎ አምኖ አንቺን በእኔ ስም የለመነ ሰው ቢኖር ከሰማዕታት አንዱም ቢሆን ከቅዱሳንም ወገን ቢሆን የፈለገው ይደረግለታል (18ኛ ተአምር ቁ፡30_31) እንደኔ ያላችሁ ወንድሞቼ ሆይ ከእንግዲህ ወዲህ 16ቱን ሕግጋት ለመፈጸም የእግ/ር ባሮች ለመሆን አንሻ እሱ በቀትር ግዜ በመስቀል ላይ እመቤታችሁ እናታችሁ እነሆ እያለ የቃል ኪዳን እመቤት እሷን ሰጥቶናል ስለዚህ የእናታችን የድንግል ማርያም ባሮች ለመሆን ፈጽመን እንሽቀዳደም ብዬ እነግራችሁዋለሁ። (12ኛ ተአምር ቁ፡ 52_53) ከነዚህ ሃሳቦቹ የተነሳ ይሄ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ እግዚአብሔር የለም ኢየሱስም ለእኛ አልሞተልንም እያለን ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚነግረን ግን 1ኛ ) አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ( 1ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 5 ) 2ኛ ) ወደ እግዚአብሔር የቀረብነው ፣ ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ ? ያልነው በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ግልጽ አድርጎ ነግሮናል ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም ( 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት  3 : 18 - 20 ) ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ ? የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው ፤ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ( 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች  15 : 55 - 57 ) 3ኛ ) በዚህም ምክንያት የምንንበረከከውም ሆነ የምንገዛው ለእግዚአብሔር አብ ክብር እየሰጠን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በመንበርከክ ብቻ ነው በመዝሙር 95 : 6 ላይ ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ ይለናል በመዝሙር 100 : 4 ላይ ደግሞ ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ በማለት ይነግረናል እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ይለናልና ( ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች  2 : 6 - 11 ) ታድያ ከዚህ ከተባረከው የእግዚአብሔር እውነት አንጻር የተአምረ ማርያምን መጽሐፍም ሆነ ጸሐፊውን ፦—————————— በማቴዎስ ወንጌል 4 : 10 በተጻፈው ቃል መሠረት ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና በማለት ገስጾ አባሮታልና እኛም እንዲሁ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ስንል እናባርረዋለን ደግሞም እናስወግደዋለን 4ኛ ) መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው ስለዚህ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ( የሐዋርያት ሥራ  4 : 12 ) እንደገናም ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎናል ( የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 ) በዕብራውያን 7 ፥ 24 ላይ ደግሞ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ይለናል 5ኛ ) ትዕዛዛትንም በተመለከተ እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ የማቴዎስ ወንጌል 5 : 18 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል የማቴዎስ ወንጌል 5 : 19 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም የዮሐንስ ወንጌል 14 : 24 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 13 December 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 11 ) ማንን ነው ማመን ያለብን ? በማን ስንታመንና ማንንስ ስናምን ነው የማናፍረው ? ጉደኛውና ተረተኛው የተምረ ማርያም መጽሐፍ ርኢክሙኑ ኦ አኃው "እስመ ኩሉ ዘረሰየ ትውክልቶ ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ ወላዲቱ ኢይትኀፈር " ወደ አማርኛው ሲተረጐም :--- ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ይለናል ( ተአምር 31 : 25 ) 1ኛ ) ማንን ነው ማመን ያለብን ? ለሚለው ጥያቄ ሀ ) መጽሐፍቅዱሳችን በእግዚአብሔር እመኑ ነው የሚለን ማልደውም ተነሡ፥ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፦ ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 : 20 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል የማርቆስ ወንጌል  11 : 22 - 23 ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ የዮሐንስ ወንጌል  14 : 1 - 3 ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ግን አላለንም ይህንን ያለን የተአምረ ማርያም መጽሐፍ ነው ለ ) እምነታችን የመጣው ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ስለሆነ እንዲሁ ዝም ብለን እንደ ደራሽ ውሃ ያመነው ወይም የምናምነው እምነት የለም ስለዚህ ፦———————— እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ይለናል ሮሜ 10 : 17 ሐ ) የአብርሃም እምነት በእግዚአብሔር ቃል የሆነ እምነት ነበር እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ኦሪት ዘፍጥረት  15 : 4 - 6 ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው ሮሜ   4 : 22 - 25 2ኛ )በማን ስንታመንና ማንንስ ስናምን ነው የማናፍረው ? ከዚህ ከተቆጠረልን ከእምነት የሆነ ጽድቅ የተነሳ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ነው የተባልነው :: ያም ያመነው ፣ ያላመንበት ብንኖር ደግሞ በእርሱ ብናምን የማናፍርበት ፣ የተመረጠና የከበረ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ነው ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም ትንቢተ ኢሳይያስ  28 :16 በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት  2 : 6 - 8 እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ ሮሜ 9 : 30 - 33 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና ሮሜ 10 : 8 - 11 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Thursday 6 December 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 10 ) ለሁሉም ሰው ለማርያምም ጭምር የኢየሱስ ሞት አስደናቂ ነው ይሁን እንጂ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ይገኝበታል በተባለው መጽሐፈ ዚቅ ፦ « ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል » የሚል ሃሳብ ተጽፎ ብናገኝም 1ኛ ) የማርያም ሞት ግን አይደለም ለእኛ ፣ ለራስዋ ለማርያም እንኩዋ ያስፈራት እንጂ ያስደነቃት አልነበረም ለምን ስንል ፦ የሞት ጣር ያዘኝ፤ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ ( መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22 : 5 - 6 ) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ ( መዝሙረ ዳዊት 18 : 4 - 5 ) ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ ( መዝሙረ ዳዊት 55 : 4 ) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ ( መዝሙረ ዳዊት 116 : 3 ) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ የሞት ጥላ በዓይኖቼ ቆብ ላይ አለ ( መጽሐፈ ኢዮብ 16 : 16 ) የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው የሞትን ጥላ ድንጋጤ ያውቃሉና (መጽሐፈ ኢዮብ 24 : 17 ) 2ኛ ) በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ራሱ በሥጋው ወራት ፦ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት ይለናል ዕብራውያን 5 : 7 ከዚያ በፊት ግን ፦———————————— ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም፦ አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 41 - 42 ) ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 43 - 44 ) ከጸሎትም ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣና ከኀዘን የተነሣ ተኝተው ሲያገኛቸው ስለ ምን ትተኛላችሁ ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 45 - 46 ) 3ኛ ) ኢየሱስ በሥጋና በደም እንዲሁ በመካፈሉ የመጣ ለውጥ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ይለናል ( ዕብራውያን 2 : 14 - 15 ) 4ኛ ) ይህ እንዲሆን ታድያ ኢየሱስ የተናገረው ፣ አባቱም እግዚአብሔር ያደረገው ወይም የሠራው ሥራ ነበረ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል ( የማቴዎስ ወንጌል 20 : 18 ) እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፥ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል ( የማርቆስ ወንጌል 10 : 33 ) እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና ( የሐዋርያት ሥራ 2 : 24 ) ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ ( የዮሐንስ ራእይ 1 : 18 ) 5ኛ )ለሁሉም ሰው ለማርያምም ጭምር የኢየሱስ ሞት አስደናቂ መሆኑ በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ ( የማቴዎስ ወንጌል 4 : 14 - 16 ) ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል ( የሉቃስ ወንጌል 1 : 79 ) እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ ( ቆላስይስ 1 21 -22 ) የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ( 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 15 : 56 ) ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን ( ሮሜ 6 : 7 -8 ) በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና ( ሮሜ 8 : 2 ) ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን ( 2ኛ ጢሞቴዎስ2 : 11 ) አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል ( 2ኛ ቆሮንቶስ 1 : 9 -10 ) ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው ? ( 2ኛ ቆሮንቶስ 2 : 16 ) ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም ? የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና ( 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 3 : 7 ) እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል ( 1ኛ ዮሐንስ መልእክት 3 : 14 ) ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 10 ) ለሁሉም ሰው ለማርያምም ጭምር የኢየሱስ ሞት አስደናቂ ነው ይሁን እንጂ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ይገኝበታል በተባለው መጽሐፈ ዚቅ ፦ « ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል » የሚል ሃሳብ ተጽፎ ብናገኝም 1ኛ ) የማርያም ሞት ግን አይደለም ለእኛ ፣ ለራስዋ ለማርያም እንኩዋ ያስፈራት እንጂ ያስደነቃት አልነበረም ለምን ስንል ፦ የሞት ጣር ያዘኝ፤ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ ( መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22 : 5 - 6 ) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ ( መዝሙረ ዳዊት 18 : 4 - 5 ) ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ ( መዝሙረ ዳዊት 55 : 4 ) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ ( መዝሙረ ዳዊት 116 : 3 ) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ የሞት ጥላ በዓይኖቼ ቆብ ላይ አለ ( መጽሐፈ ኢዮብ 16 : 16 ) የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው የሞትን ጥላ ድንጋጤ ያውቃሉና (መጽሐፈ ኢዮብ 24 : 17 ) 2ኛ ) በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ራሱ በሥጋው ወራት ፦ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት ይለናል ዕብራውያን 5 : 7 ከዚያ በፊት ግን ፦———————————— ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም፦ አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 41 - 42 ) ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 43 - 44 ) ከጸሎትም ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣና ከኀዘን የተነሣ ተኝተው ሲያገኛቸው ስለ ምን ትተኛላችሁ ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው ( የሉቃስ ወንጌል 22 : 45 - 46 ) 3ኛ ) ኢየሱስ በሥጋና በደም እንዲሁ በመካፈሉ የመጣ ለውጥ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ይለናል ( ዕብራውያን 2 : 14 - 15 ) 4ኛ ) ይህ እንዲሆን ታድያ ኢየሱስ የተናገረው ፣ አባቱም እግዚአብሔር ያደረገው ወይም የሠራው ሥራ ነበረ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል ( የማቴዎስ ወንጌል 20 : 18 ) እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፥ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል ( የማርቆስ ወንጌል 10 : 33 ) እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና ( የሐዋርያት ሥራ 2 : 24 ) ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ ( የዮሐንስ ራእይ 1 : 18 ) 5ኛ )ለሁሉም ሰው ለማርያምም ጭምር የኢየሱስ ሞት አስደናቂ መሆኑ በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ ( የማቴዎስ ወንጌል 4 : 14 - 16 ) ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል ( የሉቃስ ወንጌል 1 : 79 ) እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ ( ቆላስይስ 1 21 -22 ) የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ( 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 15 : 56 ) ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን ( ሮሜ 6 : 7 -8 ) በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና ( ሮሜ 8 : 2 ) ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን ( 2ኛ ጢሞቴዎስ2 : 11 ) አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል ( 2ኛ ቆሮንቶስ 1 : 9 -10 ) ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው ? ( 2ኛ ቆሮንቶስ 2 : 16 ) ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም ? የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና ( 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 3 : 7 ) እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል ( 1ኛ ዮሐንስ መልእክት 3 : 14 ) ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Monday 26 November 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 8 ) እውነተኛዋ የኢየሱስ እናት ማርያምና ሐሰተኛ የተአምረ ማርያምዋ ማርያም ልዩነታቸው 1ኛ ) እውነተኛዋ የኢየሱስ እናት ማርያም ሀ ) ወሣህሉኒ ለትውልደ ትውልድ ለዕለ ይፈርህዎ የሉቃስ ወንጌል 1 : 50 ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል የሉቃስ ወንጌል 1 : 50 ብላለች ለ ) እስመ ገብረ ሊተ ኀይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ የሉቃስ ወንጌል 1 : 49 ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው የሉቃስ ወንጌል 1 : 49 ብላለች ሐ ) ወትቤሎ ማርያም ለመልአክ ነየ አመተ እግዚአብሔር ይኲነኒ በከመ ትቤለኒ ወእምዝ ሖረ ወኀለፈ እምኀቤሃ መልአክ የሉቃስ ወንጌል 1 : 38 ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ የሉቃስ ወንጌል 1 : 38 ብላለች 2ኛ ) ሐሰተኛ የተአምረ ማርያምዋ ማርያም ( የጠረፍዋ ንግሥት ) ሀ ) በተአምር  4  ላይ  ማርያምን  ለመገነዝ  ሲሄዱ  ታውፋንያ  የተባለ  አይሁድ አልጋዋን  ስለያዘ  እጁ  በመልአክ  ተቆርጦ  አልጋው  ላይ  ቀረ።  ይህ  ሰው ሐዋርያትን  ይቅርታ  ጠየቀ፤  ክርስቶስንም  ይቅር  እንዲለው  ለመነ። ሐዋርያት  ግን  ወደ  እመቤታችን  ለምን  አሉት።  ማርያም  ቀድሞውኑ ከሞት  ተነሥታ  ነበርና  ለመናት።  ማርያምም  ጴጥሮስን  እንዲቀጥልለት ነገረችው። ጴጥሮስም በክርስቶስ ስምና በማርያም ስም እጁን መለሰለት ብላ ትናገራለች:: ለ ) እንደገናም በተአምር 33 ፥ 23 - 25 ላይ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤቴ ሆይ ከአንቺ ዘንድ ሽቶ የወደደውን ሁሉ ያላገኘ ማነው? በአንቺ አምኖ ያፈረ ማነው ? አንቺን ለምኖ ወደ ገሃነም ያወረድሽው ማነው ? ወደ ሠርግ ቤት ማለት ወደ መንግሥተ ሰማይ አገባሽው እንጂ ብላ ሰዎች ከእርስዋ እንዳይሄዱና እንዲያመልኩዋት ፣ እንዲሰግዱላትና እንዲገዙላትም ስለ ራሷ ታላቅነት ተናገረች :: 3ኛ ) በእነዚህ ጉዳዮች መጽሐፍቅዱስ የሚሰጠው ዳኝነት በተራ ቁጥር ሀ በተጠቀሰው ሃሳብ መሠረት ይህ  ጴጥሮስ  ትክክለኛውና እውነተኛው ሐዋርያው ጴጥሮስ ቢሆን ኖሮ ይደንቀን ነበር :: ነገር ግን በማርያም በኩል የታውፋንያን እጅ እንዲቀጥልለት የተነገረው ጴጥሮስ ፣ እንደገናም በክርስቶስ ስምና በማርያም ስም እጁን መለሰለት የተባለው ጴጥሮስ በመጽሐፍቅዱሳችን የምናውቀው እውነተኛውና ሐዋርያም የሆነው ጴጥሮስ አይደለም :: እውነተኛውና የመጽሐፍቅዱሱ ጴጥሮስማ በሐዋ 3 ፥ 6  ብርና  ወርቅ  የለኝም፤  ይህን  ያለኝን  ግን  እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ በማለት ነው በኢየሱስና በኢየሱስ ስም ብቻ በሽተኞችን የፈወሰው :: ይህ ብቻ አይደለም በሐዋ 4 ፥ 12 መዳንም በሌላ  በማንም  የለም፤  እንድንበት  ዘንድ  የሚገባን  ለሰዎች  የተሰጠ  ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና  ነው ያለው :: ከማርያም ትእዛዝ ተቀብሎ በማርያም ስም ፈወሰ ተብሎ የተጻፈበት ሥፍራ በመጽሐፍቅዱሳችን አንድም ቦታ ላይ የለም :: በማርያም ስም መፈወስም ሆነ አጋንንትን ማስወጣት የጌታም ሆነ የሐዋርያቱ ትምህርት አይደለም:: መጽሐፍቅዱሳችንም አይደግፈውም :: የተአምረ ማርያም ትምህርት ነው :: ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆነ የተአምረ ማርያም ትምህርት ደግሞ የእግዚአብሔር ሳይሆን የአጋንንት ትምህርት ነውና አንቀበለውም :: የመጽሐፍቅዱሱ ጴጥሮስም ሆነ እንደ ጴጥሮስ ያለ የእግዚአብሔር ቃል እምነት ያለን እኛ ሁላችን በሽተኞችን እንድንፈውስ አጋንንትንም እንድናወጣ የታዘዝነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጂ በማርያም ስም አይደለም የማርቆስ ወንጌል 16 ፥ 15 - 18 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 10 ፥ 5 - 15 :: የኢየሱስ እናት ማርያምም ከሞት አልተነሳችም ደግሞም አላረገችም 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፥ 50 :: ከሞት ተነስቶ ያረገውና ተመልሶም የሚመጣው ኢየሱስ ብቻ ነው ዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 13 ፤ የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 11::እንደገናም የኢየሱስ እናት ማርያም ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ያለንን የጌታ አማኞችን የሚላችሁን አድርጉ አለችን እንጂ የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 5 ከሞት የተነሳች ሆናና በእግዚአብሔርም ቦታ ራስዋን ተክታ የሰዎችን ጸሎት አልሰማችም :: ደግሞም ፍጡር እንጂ አምላክ አይደለችምና የተቆረጡ እጆችን በስሜ በመለመን ቀጥልላቸው ስትል የነገረችውም ሆነ ትዕዛዝ የሰጠችው ሐዋርያ የለም :: በእግዚአብሔር ቦታ ራሷን ተክታም እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ አትሠጥም ፣ ልትሠጥም አትችልም :: ከዚህ የተነሳ እኛ የቃሉ አማኞች ፍጡር የሆነችዋን የኢየሱስን እናት ማርያም ከፈጣሪ ለይተን የምናውቅና ማርያምም የተፈጠረች እንጂ ፈጣሪ አለመሆንዋን የተረዳን ስለሆንን ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ፣ ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ስንል በዓል አዘጋጅተንና አጽዋማትን ቀምረን የምንጠራት ማርያም የለችንም :: ከዚህም ሌላ ሐዋርያቱም ወደ ማርያም ለምኑ አላሉንም :: ትምህርታቸው አይደለችምና እነርሱ ክርስቶስን ነው የሰበኩልን:: በስሙም ብናምን የኃጢአታችንን ሥርየት እንደምናገኝ ነው የነገሩን 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 23 ፤ የሐዋርያት ሥራ 10 ፥ 42 እና 43 የምናነበውን ቃል አስተውለን እንድንታዘዘውና በዚህም በሰማነው ቃል ወደ እውነቱ እንድንመጣ ቸሩ መድኃኔዓለም ያግዘን ይርዳን:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Thursday 8 November 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 5 ) አስፈሪው የእግዚአብሔር ቁጣ በልዝብ ምላስም ሆነ በስጦታችን ልናበርደው የማንችለው ነው ( ምሳሌ 15 ፥ 1 ፣ ምሳሌ 21 ፥ 14 ) በፊንሐስ አማካኝነት፦ዘኊልቁ 25 ፥ 7 _ 13 ሀ ) መቅሰፍት ከእስራኤል የተከለከለበት ለ ) የእግዚአብሔር ቁጣ ከእስራኤል የተመለሰበት ሐ ) ለእስራኤል ልጆች ማስተስረይ የመጣበት ነው አስፈሪውና ጽኑዕ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሕዝቡ እንዲከለከል እግዚአብሔርም ቁጣውን ከሕዝቡ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ቅንዓት በመካከል የሚቀና ፊንሐስ ያስፈልጋል ዘኊልቁ 25 ፥ 11 ሀ ) እንደ ዔሊ እርሱ እግዚአብሔር ነው ደስ ያሰኘውን ያድርግ የማይል ( መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 3 ፥ 18 ) ለ ) ንቂ ቁሚ የሚል ኢሳይያስ 51 ፥ 17 ፤ መሣፍንት 5 ፥ 12 ፣ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥40 - 42 ስለዚህ፦ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5 : 14 ) ሐ ) ደግመሽ አትጠቺው የሚል ኢሳይያስ 51 ፥ 22 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 8 : 1 - 11 መ ) ጠጉርሽን ቁረጪ ጣይውም የሚል ኤርምያስ 7 ፥ 29 ፣ ራዕይ 3 : 1 - 6 ፣ 15 - 22 ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ ይለናል 1ኛ ነገሥት 13 ፥ 18 ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5 : 6 ፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4 :2 ፤ ሮሜ ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3 : 16 - 18 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Monday 5 November 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 4 ) ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን የሚወድ ማንነት የለንም ኤፌሶን 2 : 3 የእግዚአብሔር ቁጣና የሰው ቁጣ ልዩነታቸው ሀ ) የእግዚአብሔር ቁጣ ፦ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ ሰው ቁጣ ቶሎ የሚነሣና የሚበርድ አይደለም እንደገናም እግዚአብሔር በባሕርዩ ቁጣ የለበትም ነገር ግን ቅዱስና ጻድቅ ስለሆነ በኃጢአት ምክንያት ይቆጣል ቁጣውም በፍርዱ ይታያል ትንቢተ ኢሳይያስ 59 : 1- 4 ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 53 በሙሉ ዘኁልቁ 25 : 7 - 13 ፤ ትንቢተ ዘካርያስ 8 : 14 - 16 የዮሐንስ ወንጌል 3 : 36 ፤ ሮሜ 1: 18 ፤ ሮሜ 2 :5 ፤ ኤፌሶን 5 : 6 ለ ) የሰው ቁጣ ከፍርሃትና ከኩራት ከስንፍናም የሚመጣ በመሆኑ ቶሎ የሚነሣና የሚበርድም ነው ከዚህም ባሻገር በቃሉ እና በመንፈሱ እውነት ካልታረመና ካልተገታ የሥጋ ሥራ ስለሆነ አሳዛኝ ውጤትን ያመጣል ዘፍጥረት 27 : 41 - 45 ፤ ዘፍጥረት 30 : 1- 3 ፤ ዘፍጥረት 49 :6 እና 7 ፤ ምሣሌ 27 : 4 ሐ ) ልዝብ መልስ ወይም ስጦታ የሰውን ቁጣ ሊያበርድ ይችላል ምሣሌ 15 : 1 ፤ ምሣሌ 21 : 14 መ ) የእግዚአብሔር ቁጣ ግን የሰው ቁጣ ስላልሆነ በልዝብ መልስም ሆነ ስጦታ ልናበርደው አንችልም 1ኛ ሳሙኤል 15 : 13 - 16 ፤ትንቢተ ኤርምያስ : 12 : 2 የማቴዎስ ወንጌል 15 : 8 ፤ የማርቆስ ወንጌል 7 : 6 ፤ ቲቶ 1 : 16 ትንቢተ ኢሳይያስ 1 : 11 - 16 ፤ ሆሴዕ 6 : 6 ሠ ) ለእግዚአብሔር የሚገኝ እውነተኝነት መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 19 : 18 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 4 ) ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን የሚወድ ማንነት የለንም ኤፌሶን 2 : 3 የእግዚአብሔር ቁጣና የሰው ቁጣ ልዩነታቸው ሀ ) የእግዚአብሔር ቁጣ ፦ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ ሰው ቁጣ ቶሎ የሚነሣና የሚበርድ አይደለም እንደገናም እግዚአብሔር በባሕርዩ ቁጣ የለበትም ነገር ግን ቅዱስና ጻድቅ ስለሆነ በኃጢአት ምክንያት ይቆጣል ቁጣውም በፍርዱ ይታያል ትንቢተ ኢሳይያስ 59 : 1- 4 ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 53 በሙሉ ዘኁልቁ 25 : 7 - 13 ፤ ትንቢተ ዘካርያስ 8 : 14 - 16 የዮሐንስ ወንጌል 3 : 36 ፤ ሮሜ 1: 18 ፤ ሮሜ 2 :5 ፤ ኤፌሶን 5 : 6 ለ ) የሰው ቁጣ ከፍርሃትና ከኩራት ከስንፍናም የሚመጣ በመሆኑ ቶሎ የሚነሣና የሚበርድም ነው ከዚህም ባሻገር በቃሉ እና በመንፈሱ እውነት ካልታረመና ካልተገታ የሥጋ ሥራ ስለሆነ አሳዛኝ ውጤትን ያመጣል ዘፍጥረት 27 : 41 - 45 ፤ ዘፍጥረት 30 : 1- 3 ፤ ዘፍጥረት 49 :6 እና 7 ፤ ምሣሌ 27 : 4 ሐ ) ልዝብ መልስ ወይም ስጦታ የሰውን ቁጣ ሊያበርድ ይችላል ምሣሌ 15 : 1 ፤ ምሣሌ 21 : 14 መ ) የእግዚአብሔር ቁጣ ግን የሰው ቁጣ ስላልሆነ በልዝብ መልስም ሆነ ስጦታ ልናበርደው አንችልም 1ኛ ሳሙኤል 15 : 13 - 16 ፤ትንቢተ ኤርምያስ : 12 : 2 የማቴዎስ ወንጌል 15 : 8 ፤ የማርቆስ ወንጌል 7 : 6 ፤ ቲቶ 1 : 16 ትንቢተ ኢሳይያስ 1 : 11 - 16 ፤ ሆሴዕ 6 : 6 ሠ ) ለእግዚአብሔር የሚገኝ እውነተኝነት መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 19 : 18 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Thursday 1 November 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ... በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 3 ) የተወደደ ሰው ከእግዚአብሔር የሚሆንለት ነገር የተወደደ ሰው ፦ ————————————————— 1ኛ ) እግዚአብሔር የሚጠላው ሰው የለውም ዘዳግም 1 : 26 - 28 ፣ የዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 16 ፤ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 : 8 ፣ 16 ፤ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5 : 3 2ኛ ) ተማምኖ የሚኖርና በትከሻዎቹ መካከል የሚያድር ነው ዘዳግም 32 ፥ 10 - 12 ፤ ዘጸአት 19 ፥ 4 ፤ ኢሳይያስ 46 : 4 3ኛ ) ሕዝቡ ያልሆነውና ያልተወደደው ሕዝብ ሕዝቤ ተብሎና ተወድዶ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ የተጠራ ነው ሆሴዕ 2 : 1 ፣ 25 እና 26 ፤ ሮሜ 9 : 25 4ኛ ) እንደተወደደ መቅረት አለበት ነህምያ 13 : 16 5ኛ ) የሚጽናና እና እግዚአብሔርም የሚራራለት ነው ኢሳይያስ 61 : 2 ፤ ሉቃስ 4 : 17 - 19 6ኛ ) በእርሱ ላይ በተናገረ ቁጥር የሚያስበው ነው ኤርምያስ 31 : 20 7ኛ ) በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ ነው የሐዋርያት ሥራ 10 : 34- 35 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Monday 29 October 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 2 ) እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር 1ኛ ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ( የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16 ) 2ኛ ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ( ሮሜ 5 ፥ 8 ) 3ኛ ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 : 4 - 7 ) 4ኛ ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል ( 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 9 - 11 ) II - ሰዎች ሊለማመዱት ፣ ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 23 _ 35 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ትርጉም ፦ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ)ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ትርጉም ፦ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ) የቀደመችዋ ኦርቶዶክስ የያዘቻቸውን መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶች ለማሳየት ቅዳሴ ለኢየሱስ በሚል አርዕስት ከወንድማችን አባ ተክለማርያም ጋር በየሳምንቱ ቅዳሜ ባለን ፕሮግራም ጀምረን ቅዳሴ ሐዋርያትን በማጠናቀቅ ቅዳሴ እግዚእ ላይ ደርሰናል በዛሬው ዕለት የለቀቅነው ቪዲዮ ደግሞ በጣም አስደናቂና በውስጡም ትልቅ መልዕክት ያለው በመሆኑ ሰምታችሁ እንድትባረኩበት እነሆ ብለናል ትምህርቱ በየሳምንቱ ሳይቋረጥ ይቀጥላል ተባረኩ ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አዕምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን ዘወትር አንተን ያዩ ዘንድ ጆሮዎቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ ( ምንጭ ከቅዳሴ እግዚእ የተወሰደ) በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው የሉቃስ ወንጌል 24: 45 ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1 : 18 - 19 አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Zemary hawaz newest song MECHE NEW መቼ ነው መቼ ነው ያለቅድመ ሁኔታ መቼ ነው በእምነት የምሰብክህ ጌታ መቼ ነው የዙርያዬን ረስቼው መቼ ነው ስለ እውነት የማደላው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኔን እግዚአብሔር ይባርከው ወገኞቼስ ለእኛስ መቼ ነው ያለቅድመ ሁኔታ ጌታን የምንሰብከው ዘመኑ እኮ አጭር ነው የትኩረት አድማሶቻችንን ከሳበው ከንቱና ተራ ከሆነው ነገር ወጥተን እባካችሁ ይህንን ጌታን እንስበከው ኢየሱስ ያድናል እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር  1ኛ ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ( የዮሐንስ ወንጌል  3 : 16 ) 2ኛ ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ( ሮሜ 5 ፥ 8 ) 3ኛ ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፥ በጸጋ ድናችኋልና ፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች  2 : 4 - 7 ) 4ኛ ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል ( 1ኛ የዮሐንስ መልእክት  4 9 - 11 ) II - ሰዎች ሊለማመዱት ፣ ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር የማቴዎስ ወንጌል 18 ፥ 23 _ 35   አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ?


I - እግዚአብሔር ፍቅሩን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶ ተቀበለን



በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር



handGod.jpg
1 ) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና 


                               ( የዮሐንስ ወንጌል  3 : 16 )



2 ) ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል 

                                       ( ሮሜ 5 8 )


3 ) ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን በጸጋ ድናችኋልና በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ( ወደ ኤፌሶን ሰዎች  2 : 4 - 7 ) 


4 ) በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል 


                            ( 1 የዮሐንስ መልእክት  4 9 - 11 )




II - ሰዎች ሊለማመዱት ሊገልጹትና ሊያሳዩት ያልቻሉት የእግዚአብሔር ፍቅር 

የማቴዎስ ወንጌል 18 23 _ 35 



slide_2.jpg
Screen-Shot-2018-03-19-at-9.00.33-PM.png



አባ ዮናስ ጌታነህ 


ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት 

Saturday 27 October 2018

አጠር ያለ የግጥም መነባንብ :- የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የገድሉን ሐሰተኝነት በሚያጋልጥ መልኩ ከተክለሐይማኖት ገድል ተውጣጥቶ እና በወንጌሉ እውነት ተቃኝቶ የቀረበ የግጥም መነባንብ መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንልዎት!!! ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ ለሰዎች ብርሃን ያበራሁኝ መስሎኝ በጨለማ ኖሬ ለራሴ ጨለምኩኝ ከንቱ ግብዝነት ይዞኝ ስንቀባረር ክህነቴን በሰማይ አድርጌው ለመኖር ክንፎችን ገጥሜ በግራና በቀኝ የሰማይ ካህን ነው ራሴን አስባልኩኝ ነገር ግን ክንፎቹ የውሸት ነበሩ ለይምሰል ተስለው ተሰክተው የቀሩ እንደ ዶሮ ላባ ድንገት ሲነቀሉ በወንጌሉ እውነት ዳግም ላያበቅሉ እኔም ተሳቅቄ ወዮልኝም አልኩኝ ሥራዬን ገልጠውት ከሹመት ሲሽሩኝ የሰዎችን ኃጢአት ይቅርም ለማስባል የሚንበረከክ ነው ሲጸልይ የሚውል ማንም ያልሰራውን ሰርተኸዋል ሲሉኝ ተብዬ ስወደስ ሰዎች ሲያሞካሹኝ በጌቴሴማኒ የተንበረከከው ሥርየት ለማሰጠት ደሙን ያፈሰሰው ደም ሳይፈስ ሥርየት ፍጹም አይገኝም በመንበርከክ ጸሎት ማንም አያመጣም ብሎ ተናገረኝ ውሸታም ነህ ብሎ ሥራዬን አጋልጦ ተንኮሌን ፈንቅሎ ላሞች ባልዋሉበት የኩበት ለቀማ ራሴን ሰቅዬ በጸሎቱ ማማ እግሬ የተቆረጠው ስጸልይ ነው አልኩኝ በገድል በድርሣኑ ራሴን ከመርኩኝ እውነቱ ሲነገር ታሪክ ሌላ ሆነ እኔም ተጋለጥኩኝ ስሜም ተኮነነ መንግሥትን ከላስታ ወደ ሸዋ ምድር ለማዞር ፈልጌ ስዶልት ስመክር ገድለህ ንገሥ ብዬ ንጉሡን ሳሳብር የዶሮውን ጩኸት ትርጉሙን አውቃለሁ እያልኩ ስቀሰቅስ ሳዳምቅ እያለሁ ድንገት በጦርነት እግሬ ተሰበረ የጸሎት ሰው ሲሉኝ ስሜም የከበረ ዛሬስ ተዋረድኩኝ ገበናዬም ወጣ ብዬ አለቀስኩኝ ባመጣሁት ጣጣ የመጨረሻዬ የተቅማጥ በሽታ የመጨረሻዬ የወባ በሽታ ከዚህ ምድር ይዞኝ ሊወስደኝ በአንድ አፍታ እስቲ ስሜን ላድስ በፍጻሜው ሰዓት በዚህ በተቅማጡ ከመሞቴ በፊት ብዬ አሰብኩና ኪዳኑን በሰማይ ከኢየሱስ ደም ጋራ ላያይዘው በላይ መዋሸት ጀመርኩኝ ዳግመኛ ሳላፍር እንደ ስቅለቱ ደም ተቅማጤን ላስቆጥር በገዳም የሞተ በወባ በሽታ ይድናል አይጠፋም ይኖራል በደስታ በመላዕክት ዓለም በሆታ በእልልታ በመንግሥተ ሰማይ በላይኛው ጌታ ነገር ግን አንዳንዱ አቃሎት ነገሬን ከሰማኝ በኋላ የባልቴት ተረቴን በያደባባዩ ደግሞ ሊያሳፍረኝ መደበቅያ ሥፍራ ቦታም አሳጥቶኝ በወንጌሉ እውነት በርብሮ ገለጠኝ የመቀበርያዬም ጊዜያቱ ደረሰ ሳልፈልገው በግድ ጉድጓዴ ተማሰ እኔም ከዚህ ወዲያ ይበቃኛል አልኩኝ ዳግም ላልተነፍስ መቃብር ወረድኩኝ እፎይ ያለው ትውልድ ይኸው ተቀስቅሶአል የወንጌል ደመራው ችቦው ተለኩሶአል ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ያድናል ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ለግጥሞቹ የተጠቀምኩበት መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው ያንብቡአቸው ዕብራውያን 12 ፥ 24 , ቅዳሴ ሐዋርያት ገጽ 122 ፥ 106 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 214 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 2116 , ዕብራውያን 10 ፥ 29 - 31 , በ13ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በላስታ ያለውን የዛጉዬን መንግሥት ወደ ሸዋ ለመመለስ ባካሄደው መፈንቅለ መንግሥት , ገድለተክለሐይማኖት ምዕራፍ 27 ፥ 15 ፣ 17 , 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 7 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 , ኅዳር 24 ፥ ገጽ 78 , ዕብራውያን 9 ፥ 22 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 ፣ ሮሜ 5 ፥ 6 _ 10 , ገድለ ተክለሐይማኖት ምዕራፍ 57 , ገድለ ተክለሐይማኖት ትንሣኤ የመጻሕፍት አሳታሚ ድርጅት ሦስተኛ እትም 1973 የታተመ ምዕራፍ 56 ቊጥር 1 - 3 ገጽ 175 ,

Thursday 25 October 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 1 ) እግዚአብሔር እንዴት ተቀበለን ? ስለ ወደደን ተቀበለን :: ሀ ) መወደድ ( ትንቢተ ሚልክያስ 1 ፥ 2 ፤ ትንቢተ ዘካርያስ 10 ፥ 6 ) የዛሬው ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ የሚናገረው ስለ መወደድ ነው በማስተዋል ተከታተሉ :: መወደዱ የገባው ሰው ደግሞ በቅዱስ አጠራሩ ጠርቶ ያዳነውን ጌታ ይጠራል እንጂ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1 : 9 እንደገና ወደኋላ ተመልሶና የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መውደድ ረስቶ ወይንም በእግዚአብሔር እንዳልተወደደ አድርጎ ራሱን በመቊጠር ነይ ነይ እምዬ ማርያም ፣ ናና ሚካኤል ፣ ናና ገብርኤል ፣ ናና ኡራኤል እና የመሣሠሉትን እያለ ሲጣራ አይገኝም :: ነይ ነይ እምዬ ማርያም ፣ ናና ሚካኤል እና ሌሎችንም ቅዱሳን መላዕክትንም ሆነ ቅዱሳንን ሰዎች አለመጥራት እነርሱን መጥላትና እነርሱንም አለመፈለግ እንዳልሆነ ሕዝባችን ሊረዳ ይገባዋል :: እኛ አምላክ ያለን እና አምላካችንም ልጆቹ አድርጎ የተቀበለን ሕዝቦቹ ስለሆንን ( 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 16 _ 18 ) ማርያምን ቅዱሳን ሰዎችንና ቅዱሳን መላዕክትን ሁሉ ስማቸውን አድሬስ በማድረግ እየተጣራን ወደ ማርያም ወደ ፍጡራን ሰዎችና ወደ መላዕክቱም ጭምር እንድንጸልይ መጽሐፍቅዱስ አያስተምረንም ተባረኩ :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Sunday 14 October 2018

የተክለ ሃይማኖት ወዮታ 


የገድሉን ሐሰተኝነት በሚያጋልጥ መልኩ ከተክለሐይማኖት ገድል ተውጣጥቶ እና በወንጌሉ እውነት ተቃኝቶ  የቀረበ የግጥም መነባንብ 



መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንልዎት!!!




ወዮልኝ 

ወዮታ አለብኝ 

ለሰዎች ብርሃን ያበራሁኝ መስሎኝ 

በጨለማ ኖሬ ለራሴ ጨለምኩኝ 

ከንቱ ግብዝነት ይዞኝ ስንቀባረር 

ክህነቴን በሰማይ አድርጌው ለመኖር 

ክንፎችን ገጥሜ በግራና በቀኝ 

የሰማይ ካህን ነው ራሴን አስባልኩኝ 

ነገር ግን ክንፎቹ የውሸት ነበሩ 

ለይምሰል ተስለው ተሰክተው የቀሩ 

እንደ ዶሮ ላባ ድንገት ሲነቀሉ 

በወንጌሉ እውነት ዳግም ላያበቅሉ 

እኔም ተሳቅቄ ወዮልኝም አልኩኝ 

ሥራዬን ገልጠውት ከሹመት ሲሽሩኝ 

የሰዎችን ኃጢአት ይቅርም ለማስባል 

የሚንበረከክ ነው ሲጸልይ የሚውል 

ማንም ያልሰራውን ሰርተኸዋል ሲሉኝ 

ተብዬ ስወደስ ሰዎች ሲያሞካሹኝ

በጌቴሴማኒ የተንበረከከው 

ሥርየት ለማሰጠት ደሙን ያፈሰሰው 

ደም ሳይፈስ ሥርየት ፍጹም አይገኝም 

በመንበርከክ ጸሎት ማንም አያመጣም 

ብሎ ተናገረኝ ውሸታም ነህ ብሎ

 ሥራዬን አጋልጦ ተንኮሌን ፈንቅሎ 

ላሞች ባልዋሉበት የኩበት ለቀማ

ራሴን ሰቅዬ በጸሎቱ ማማ 

እግሬ የተቆረጠው ስጸልይ ነው አልኩኝ 

በገድል በድርሣኑ ራሴን ከመርኩኝ 

እውነቱ ሲነገር ታሪክ ሌላ ሆነ 

እኔም ተጋለጥኩኝ ስሜም ተኮነነ

መንግሥትን ከላስታ ወደ ሸዋ ምድር 

ለማዞር ፈልጌ ስዶልት ስመክር 

ገድለህ ንገሥ ብዬ ንጉሡን ሳሳብር 

የዶሮውን ጩኸት ትርጉሙን አውቃለሁ 

እያልኩ ስቀሰቅስ ሳዳምቅ እያለሁ 

ድንገት በጦርነት እግሬ ተሰበረ 

የጸሎት ሰው ሲሉኝ ስሜም የከበረ 

ዛሬስ ተዋረድኩኝ ገበናዬም ወጣ 

ብዬ አለቀስኩኝ ባመጣሁት ጣጣ 

የመጨረሻዬ የተቅማጥ በሽታ 

የመጨረሻዬ የወባ በሽታ 

ከዚህ ምድር ይዞኝ ሊወስደኝ በአንድ አፍታ 

እስቲ ስሜን ላድስ በፍጻሜው ሰዓት 

በዚህ በተቅማጡ ከመሞቴ በፊት 

ብዬ አሰብኩና ኪዳኑን በሰማይ 

ከኢየሱስ ደም ጋራ ላያይዘው በላይ 

መዋሸት ጀመርኩኝ ዳግመኛ ሳላፍር 

እንደ ስቅለቱ ደም ተቅማጤን ላስቆጥር 

በገዳም የሞተ በወባ በሽታ 

ይድናል አይጠፋም ይኖራል በደስታ 

በመላዕክት ዓለም በሆታ በደስታ 

በመንግሥተ ሰማይ በላይኛው ጌታ 

ነገር ግን አንዳንዱ አቃሎት ነገሬን 

ከሰማኝ በኋላ የባልቴት ተረቴን 

በያደባባዩ ደግሞ ሊያሳፍረኝ 

መደበቅያ ሥፍራ ቦታም አሳጥቶኝ 

በወንጌሉ እውነት በርብሮ ገለጠኝ 

የመቀበርያዬም ጊዜያቱ ደረሰ 

ሳልፈልገው በግድ ጉድጓዴ ተማሰ 

እኔም ከዚህ ወዲያ ይበቃኛል አልኩኝ 

ዳግም ላልተነፍስ መቃብር ወረድኩኝ 

እፎይ ያለው  ትውልድ ይኸው ተቀስቅሶአል 

የወንጌል ደመራው ችቦው ተለኩሶአል 

ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ያድናል  


ወስብሐት ለእግዚአብሔር 
ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል 
ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር 

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ 


ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት 

Monday 8 October 2018

የመልዕክት ርዕስ ፦———— ክፍል አንድ መልዕክት ፦ ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥየመልዕክት ርዕስ ፦———— ክፍል አንድ መልዕክት ፦ ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ ኢያሱም አካንን ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረግኸውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላምለእናንተ ይሁን በእነዚህ በሁለት ቀናት ማለትም ዛሬ ሰኞና ሐሙስ የምንመለከታቸው ሃሳቦች 1ኛ ) ክፍል አንድ መልዕክት ፦ ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ 2ኛ ) ክፍል ሁለት መልዕክት ፦ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረግኸውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ የሚሉ ናቸው የክፍሉም ምንባብ በአጭሩ እንዲህ የሚል ነው ኢያሱም አካንን ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረግኸውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው ( ኢያሱ 7 ፥ 19 ፣ ያዕቆብ 5 ፥ 16 ) የሃሳቡን ሙሉ ክፍል ለማግኘት ኢያሱ ምዕራፍ 7 ን በሙሉ አንብቡት በዛሬው ዕለት ግን የተመለከትነው ልጄ ሆይ ለእሥራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ የሚል ነው :: ይሁን እንጂ ታድያ ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት ብዙ ዓይነት ሲሆን አካን በኢያሱ አማካኝነት ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ የተባለበት እውነት ግን ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ፣ በዚህ ውስጥ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት ማለት ደግሞ መሸነፍም ሆነ መዋረድ አለመሆኑን ፣ ከዚህም ሌላ ሁሉም ነገር ከዚህ የሚጀምር መሆኑን ፣ በዚህም ጉዳይ ታድያ አሁንም ክብር የምንሰጠው እንደ አካንም ሆነ እንደ ዳዊት ክብር ስጡ ተብለንና ተወትውተን ፣ ግዴታም መጥቶብን ሳይሆን እራሳችን ገብቶንና ፈቅደን አውቀንም ክብር ስንሰጥ እግዚአብሔር ራሱ በአደባባይ እንደሚያከብረን ነው የተማማርነው :: ለዚህ መልዕክት አጋዥ የሚሆን ሰሙኑን የተለቀቀ ቪዲዮ አለ ሊንኩን ከመልዕክቴ ጋር አያይዤ ልኬላችኋለሁ ተመልከቱት ብዙ ትማሩበታላችሁ UNBELIEVABLE!! A FIGHT breaks out in AMI - Accurate Prophecy with Alph LUKAU https://youtu.be/0g20ezp91S0 ለቀጣዩ የትምህርት ክፍለ ጊዜ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ ተባረኩ በማለት የምሰናበታችሁ ወንድማችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ከጸአተ ግብጽ አኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Friday 5 October 2018

*⛪#በእንባቸው #ቤተክርስትያን #አደራ ይላሉ*��ብፁዕ አቡነ #ቀውስጦስ*��ማኅበረ ቅዱሳን ባዘጋጀው መናፍቃን ...ብጹዕ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ ዛሬም ይማልዳል የሚለው ሃሳብ በጣም ስለከበዳቸው እኔ ግን ይጨንቀኛል ልጆቼ እንዳትሠረቁ ራሳችሁን ጠብቁ ሲሉ ለተጨነቁበትና ላለቀሱበት ጥብቅ የሆነ አደራቸውንም ላስተላለፉበት ቃለ ምዕዳን የተዘጋጀ መጽሐፍቅዱሳዊ ምላሽ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ፣ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናንና የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በሙሉ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልን ብጹዕ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ እኔ ግን ይጨንቀኛል ልጆቼ እንዳትሠረቁ ራሳችሁን ጠብቁ ሲሉ ለተጨነቁበትና ላለቀሱበት የኢየሱስ ክርስቶስ የማማለድ ሥራ ትክክለኛውን መልስ ልንሰጣቸውና ከጭንቀታቸውም ሆነ ከልቅሶአቸው ልንታደጋቸው እንዲሁም ሰራቂው እንደገናም ሌባው ማን እንደሆነ በቃሉ መሠረት ልናመለክታቸው ጊዜው በመሆኑ ምላሹን ለመስማት በሰዓታችሁ እንድትገኙ ከወዲሁ ጋብዘናችኋል እኛም ይህንን ምላሽ በሰዓታችን ተገኝተን ወደ እናንተ እስክናደርስ ድረስ ብጹዕ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ እንዲህ ተጨንቀው ያለቀሱበትን ቪዲዮ እናንተም በአግባቡ እንድትመለከቱትና ከምንሰጠውም ምላሽ ጋር በማገናዘብ ትክክለኛ የሆነውን አባቶችም ጭምር በእምነት መግለጫቸው ላይ የዘገቡትን እውነት እኛም እናሰማለን ከዚህም ሌላ ይህቺው የመጀመርያይቱ ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቃሉን እውነት መነሻ አድርጋ በመጻሕፍቶችዋ ከዘገበቻቸው ሃሳቦች ጋር በጣምራነት አያይዘን ምላሻችንን ይዘን የምንቀርብ በመሆናችን ይህንን በመረጃ የተደገፈ ትምህርት ለመስማት በሰዓታችሁ እንድትገኙ ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን ወይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 3 October 2018

Hail Gebrselassie vs. Paul Tergat Sydney 2000 ሀይሌ በ ፖል ቴርጋት ሲገፋ የመልዕክት ርዕስ : — የሚያስቀሩ የመሰሉ ሰዎች አያስቀሩህም 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 1 — 58 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን :: ይህንን መልዕክት በፌስቡክ ላይቭ ላይ ሰርቼ ለቅቄዋለሁ ፣ በዩቲዩብ ፔጄም ላይ ተቀምጦላችኋልና መመልከት ትችላላችሁ :: ይሁን እንጂ መልዕክቱ ጠቀሜታነት ያለው ስለሆነ አሁንም በጽሑፌ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ :: ብዙ ጊዜ ሰዎችን በማስቀረት የሚታወቁ ሰዎች ከድልና ከማሸነፍ የቀሩ ፣ የማሸነፉም ሆነ የድሉ ተስፋ ያመለጣቸውና ሊሆንላቸውም ያልቻሉ ሰዎች ናቸው :: በዚህ ትምህርቴ ላይ የአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴና የኬንያዊውን ሯጭ ፖልቴርጋትን ውዽድር አስመልክቶ ባለቀ ሰዓት ኃይሌ ኬንያዊውን ሯጭ አልፎት ሊያሸንፈው በሮጠ ጊዜ የደረሰበትን ቡጢ አስመልክቶ በዩቲዩብ የተለቀቀውን ቪዲዮ ለትምህርታችን እንዲሆን እነሆ ብያለሁ :: ለተጨማሪ መረጃ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴን መጠየቅ ይቻላል :: ታድያ እንግዲህ ከሩጫው ፍጻሜ መልስ ያለውን የኃይሌና የኬንያዊውን ሯጭ ግንኙነት ባላውቅም ፣ አንዳንዶች እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በስንፍናቸው ምክንያት ካመለጣቸው ተደጋጋሚ ድል የተነሳ ሕይወታቸው በቊጭትና በንዴት ሳይቀር የተሞላ በመሆኑ ቀደመ ብለው ያሰቡትን ወንድማቸውን አይደለም ክርክር ፣ ጥል ፣ ድብድብ ጌታ አይፈቅድላቸውም እንጂ በሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስቀሩ ወደኋላ የማይሉ ናቸው :: ይህንን ያልኩበትን ምክንያት ከመጽሐፍቅዱስ አስረጂ አቀርባለሁና ተከታተሉኝ :: ከክፍሉ ምንባብ እንደምንመለከተው ዳዊትን ታላቅ ወንድሙ ኤልያብ ከድሉ ሠፈር በጥል ነበር ሊያስቀረው የተነሳው :: ቊጣው በዳዊት ላይ ነዶ ለምን ወደዚህ ወረድህ ?እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው ? እኔ ኲራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል አለው ይለናል :: ዳዊት ግን የነገሩን መንስዔ ወንድሙም ኤልያብ ይህንን የነደደ ቊጣ በላዩ ላይ ያወረደበትን መነሾ በትክክል የተረዳ በመሆኑ እኔ ምን አደረግሁ ይህ ታላቅ ነገር አይደለምን ? በማለት ከእርሱ ወደ ሌላ ዘወር አለ :: እንደዚህም ያለ ነገር ተናገረ :: ሕዝቡም እንደ ቀድሞ ያለ ነገር መለሱለት ይለናል :: ዳዊትስ በነደደበት ቊጣ ምክንያት በወንድሙ በኩል የመደመጥ ዕድሉን ባያገኝም ዘወር ብሎ ግን ሊሰሙትም ሆነ ሊያዳምጡት ከሚችሉ ጋር ተነጋገረ :: አንዳንድ ጊዜ እኮ ዘወር ልበል ቢባል እንኳ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ይገባል :: የሁለቱ ወንድማማቾች የያዕቆብና የኤሳው ሕይወት የሚያስተምረን ይህንን እውነት ነው :: ኤሳው ከቊጣና ከጥል ባለፈ ሁኔታ ያዕቆብን አባቱ ስለባረከው ብቻ በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘበት :: ዔሳውም በልቡ አለ ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል :: ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ አለ :: ታድያ ሁለቱ ወንድማማቾች ያዕቆብና ኤሳው በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ነው ለርብቃም ይህ የታላቁ ልጅዋ የዔሳው ቃል የደረሰላት :: ቃሉ እንደሚነግረን ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አስጠርታ አስመጣችው ፣ አለችውም :: እነሆም ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ፣ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ ፣ በእርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጥ ፣ የወንድምህ ቊጣ እስኪበርድ ድረስ ፣ የወንድምህ ቊጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ ፣ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ :: በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ ? በማለት ታናሹ ልጁዋን ስትማጸነው እንመለከታለን ዘፍጥረት 27 ፥ 41 _ 46 :: ውድ ወገኖቼ ሆይ ከዚህ ምንባብ እንደተመለከትነው ማስቀረትን በተመለከተ በተለይም በአንዳንዶች ዘንድ በአጭሩ ልንገታው አንችልም መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ካልመጣ በስተቀር እውነተኛ ፍቅር ፣ እውነተኛ እርቅና ስምምነት ጭምር አይመጣምና ፣ እውነተኛ ፍቅርና እውነተኛ እርቅ ትክክለኛም ስምምነት እናምጣ በማለት አንለውጠውም :: ከዚህ የተነሳ የሚያስቀሩ ሰዎች አይነኬ በመሆናቸው በልባቸው ከፍ ብለውና ቃላቸውንም አስረዝመው የሚናገሩ ናቸውና ወንድሞቻቸውን እስከመግደል ደርሰው በሞት ሊያስቀሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ :: ነገር ግን አሁንም መቅደም ያለባቸው ሰዎች መቅደም ያለባቸው ሆነው ከተገኙና ከእግዚአብሔር ከሆኑ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ቢሄዱ አልፈው ይቀድማሉ እንጂ የትኛውም ኃይል አቅም አግኝቶ እነርሱን የሚስቀራቸው አይሆንም :: የሐማና የመርዶክዮስ ታሪክም የሚያስታውሰን አሁንም ይህንኑ እውነት ነው :: ሐማም መርዶክዮስ እንዳልተደፋለት እንዳልሰገደለትም ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ፣ የመርዶክዮስንም ወገን ነግረውት ነበርና በመርዶክዮስ ብቻ እጁን ይጭን ዘንድ በዓይኑ ተናቀ :: ሐማም በአርጤክሲስ መንግሥት ሁሉ የነበሩትን የመርዶክዮስን ሕዝብ አይሁድን ሊያጠፋ ፈለገ ይለናል ( አስቴር 3 ፥ 1 — 7 ) ይህ ብቻ አይደለም ከዚህም ሌላ ሐማ መርዶክዮስን መናቁ ሳያንሰው ፣ በዓይኑ እንኳ ሊያየው የማይፈልገውና የጠላው መሆኑን ለመናገር ፈልጎ አስቴር ለግብዣ የጠራችው መሆንዋን ለዘመዶቹ በኩራት ሆኖ በማውሳት ፣ ንግሥቲቱ አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ ከእኔ በቀር ከንጉሡ ጋር ማንንም አልጠራችም ፤ ደግሞ ነገ ከንጉሡ ጋር ወደ እርስዋ ተጠርቻለሁ ፣ ነገር ግን አይሁዳዊው መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ካየሁ ይህ ሁሉ ለእኔ ምንም አይጠቅምም ሲል ተናገረ :: ሚስቱም ዞሳራና ወዳጆቹ ሁሉ፦ ቁመቱ አምሳ ክንድ የሆነ ግንድ ይደረግ፥ ነገም መርዶክዮስ ይሰቀልበት ዘንድ ለንጉሡ ተናገር፤ ደስም ብሎህ ከንጉሡ ጋር ወደ ግብዣው ግባ አሉት ነገራቸውም ሐማን ደስ አሰኘው፥ ግንዱንም አስደረገ ይለናል :: ይህንን ምንባብ ስናይ እንግዲህ ማስቀረት ክፉኛ በሆነ ጥላቻ ውስጥ ገብቶ ፣ ለዓይን እንኳ ሳይቀር ለማየት ባለመፍቀድና በመሣሠሉትም ጭምር የሚያባራ አለመሆኑንና እስከ ሞት ድረስ የሚሄድ መሆኑን ነው የምንመለከተው :: የሚያስቀሩ ሰዎች አይሆንላቸውም ፣ ጌታም አይፈቅድላቸውም እንጂ ልባቸው ትልቅ ነው :: ነገር ግን ሊያስቀሩ ባዘጋጁት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እነርሱ ይቀራሉ :: ከዚህ የተነሳ እናስቀራለን ሲሉ የተነሱ ሰዎች እናስቀራለን ሲሉ ያዘጋጁት ነገር ሁሉ ለእኛ የመሸጋገርያ ድልድይ ሲሆን ፣ ለእነርሱ ግን መቅሪያ ብቻ ሳይሆን መቀበርያቸውም ይሆናል :: ለዚህ ነው አንዳንዱ ሳያውቀው የራሱን መሞቻና የመቀበርያ ጉድጓድ የሚምሰው ( መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 5 ፤ 6 እና 7 ን በሙሉ ተመልከቱ ) :: ወገኖቼ ሆይ መልዕክቴን ስጠቀልለው ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን ለመጥቀም ለተነሱ ሰዎች በክፋታችን ምክንያት ሊደርሱ ካለው የራዕያቸው ፍጻሜ ደርሰው ለሕዝብ በረከት እንዳይሆኑ መንገዳቸው ላይ እየቆምን ተንኮል የምንሰራ ሰዎች ፣ የቱንም ያህል ተንኮል ብንሰራና ክፋትን ብንሸርብ ልናቆማቸው አንችልምና ፣ ሥራ ለሠሪው እሾክ ላጣሪው እንዲሉ ስለ ክፉ ሥራችን እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን ንስሐ እየገባን ፣ የእግዚአብሔርንም ምሕረት እየጠየቅን ለቀጣዩ ጉዞ ቅኖችና መልካም ሰዎች ሆነን ብንችል የመልካም ሥራ ሁሉ ተባባሪዎች እንሁን :: አለበለዚያ ግን በዚሁ በክፋታችን ከቀጠልን ፣ ጊዜ ይቆያል እንጂ በሐማ ላይ የመጣች የእግዚአብሔር ፍርድ በእኛም ላይ ትሆናለች በማለት መልዕክቴን እጠቀልላለሁ :: እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን :: ግልባጭ ለአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት

Thursday 20 September 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 5 ) በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? ሀ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ ለ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? ንኢ ኃቤየ ኦ ድንግል ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ለሚሉ ኦርቶዶክሳውያን እግዚአብሔር እንዴት እንደተቀበለን ግንዛቤ የሚሰጥ የቁጥር 5 ትምህርት በማስተዋል ተከታተሉ

Sunday 16 September 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 4 ) በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? ሀ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ ለ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? ንኢ ኃቤየ ኦ ድንግል ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ለሚሉ ኦርቶዶክሳውያን እግዚአብሔር እንዴት እንደተቀበለን ግንዛቤ የሚሰጥ የቁጥር 4 ትምህርት በማስተዋል ተከታተሉ Category Film & Animation

Saturday 15 September 2018

የመልዕክት ርዕስ ፦ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን ( መዝሙር 43 ( 44 ) ፥ 8የመልዕክት ርዕስ ፦ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን ( መዝሙር 43 ( 44 ) ፥ 8 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን ከክንፎቹ በታች መጠጊያን አግኝተን በእግዚአብሔር ጥላ ውስጥ የምንኖረው እኛ ክርስቲያኖች ሃይማኖተኞች ሆነን ሃይማኖታችንና ሥርዓታችን ስላስገደደን አይደለም :: ሁልጊዜ በእግዚአብሔር መክበር እንዳለ ስላመንንና ስላወቅን ነው :: የመረጥነው የእምነታችን መንገዱ እምብዛም የማይመች ቢመስለንም እንኳ የመረጠን ጌታ አክባርያችን ነውና ሁልጊዜ በእርሱ እንከብራለ :: ስሙንም ለዘላለም እናመሰግናለን :: ስለዚህ ክርስትና ያታከታችሁ ፣ በሰዎች በሁኔታዎችና በነገሮች ጭምር ተስፋ የቆረጣችሁ ብትኖሩ ዛሬ በእንዲህ ሁኔታ ላላችሁ ለእናንተ መልዕክት አለኝ :: ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን ነው የሚለን ቃሉ :: ታድያ አንዳንድ ጊዜ የሚያከብር ሲያሻው ደግሞ እንደፈለገ አድርጎ የሚዘረጥጥ ሰው ነው እንጂ እግዚአብሔር አይደለምና በአምላካችን በእግዚአብሔር ሁልጊዜ እንከብራለን ቅዱሳን በዚህ መልዕክት ተጽናኑ ተባረኩ ሰላም ሁኑ አባ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 13 September 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 3 ) በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? ሀ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ ለ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? ንኢ ኃቤየ ኦ ድንግል ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ለሚሉ ኦርቶዶክሳውያን እግዚአብሔር እንዴት እንደተቀበለን ግንዛቤ የሚሰጥ የቁጥር 3 ትምህርት በማስተዋል ተከታተሉ

ልዩ የአዲስ ዓመት ዝግጅት 2011 EC ETHIOPIAN NEW YEAR SPECIAL PROGRAM

Tuesday 4 September 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 2 ) በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? ሀ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ ለ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? 2ኛ ) እግዚአብሔር ልጆቹ አድርጎ ስለተቀበለን ድንግል ሆይ ወደኔ ነይ ወይንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ስንል የምንጠራት ድንግል የለችንም:: የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርቴ በቁጥር ሁለት ላይ የተመሠረተ ነው :: በቁጥር ሁለት ትምህርታችን የምንመለከተው እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እንደተቀበለን የሚገልጹ ሃሳቦችን በማንሳት ነው :: ውድ ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔርን እኛ አልተቀበልነውም ፣ እንደገናም ጽድቃችን የመርገም ጨርቅ ስለሆነና ኃጢአተኞችም ከመሆናችን የተነሳ የኃጢአት ደሞዝ የሆነውን ሞት በላያችን ላይ ተሸክመን የምንዞር ሰዎች ስለሆንን እግዚአብሔርን የሚቀበል ማንነት የለንም :: እርሱ ግን ይሄ ሁሉ ነገር በላያችን ላይ እንዳለ አውቆ እኔም እቀበላችኋለሁ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ አለን( 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 17 - ፍጻሜ ):: የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስንም በማመናችንና በመቀበላችን ምክንያት ልጆቹ አድርጎ ተቀበለን ( ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 11 እና 12 ):: ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲቀበለን እግዚአብሔር የላከውን ኢየሱስን እንደ እናቱ ማርያም ፣ ከኃጢአተኞች ዋና ነኝ እንዳለውና የጌታውንም ምህረት እንደተቀበለው እንደ ጳውሎስ ፣ እኛም ኃጢአተኝነታችንን አምነን ጌታንና የጌታንም ምሕረት ለሕይወታችን ወስነን መቀበል አለብን የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 47 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 12 - 17 :: ይህንን ጌታ በተቀበልን ጊዜ ደግሞ አባ አባት ብለን የምንጮህበትን የልጅነት መንፈስ እናገኛለን :: ይሄ መንፈስ ያለው እንደገና ለፍርሃት የባርነት መንፈስ የተቀበለ አይሆንም :: መንፈሱም ልጅ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ወራሽ መሆኑንም ይመሰክርለታል ( ሮሜ 8 ፥ 14 _ 17 ) :: ለዚህም ነው የገላትያ መጽሐፍ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባርያ አይደለህም ልጅም ከሆንክ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ ያለን ( ገላትያ 4 ፥ 4 - 7 ) :: ታድያ እግዚአብሔር እንደተቀበለው ያወቀና ልጁንም ኢየሱስን የተቀበለ ውስጡ ያለው የወራሽነት መንፈስ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የሆነ የባርነት መንፈስ ባለመሆኑ ነይ ነይ እምዬ ማርያም እና የመሣሠሉትን የሚልበት ማንነት የለውም :: ጌታን ያልተቀበለና ለፍርሃት በሆነ ማንነት ተውጦ የባርነት መንፈስ የሚሰማው ሰው ግን አይደለም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ማለት ገና እንደ ንጉሥ ሳኦል መናፍሥት ጠሪ ቤት ሄዶና የክፉ መንፈስ መጫወቻ እስከ መሆን ደርሶ ሊሞት ይችላል :: ይህ እንዳይሆን ነው እንግዲህ የተቀበለንን እግዚአብሔር በማወቅ እስከ ሞት ድረስ ወዶ ሕይወቱን በመስጠት ያዳነንን ጌታ ተቀብለን የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንሁን የምንላችሁ :: ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም እንደሚባለው ሆኖ ይህንን እኛ ያልናችሁን የእግዚአብሔር እውነት ቸል በማለት የሞተችዋን ፣ ያልተነሳችዋንና ያላረገችዋን ፣ በመሞትዋም ምክንያት ልትሠማን የማትችለዋን ድንግል ፣ የለም ትሰማናለች በሚል ድርቅና ተይዘን በየበዓላቱና በየገዳማቱ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ስንላት ብንውል ፣ አልፈን ሄደንም ሱባዔ ገብተንና በር ዘግተን ብንጠራት ፍጻሜያችን ክስረትና የጠረፍዋ ንግሥት መጫወቻም ሆኖ መቅረት ስለሆነ ከወዲሁ እናስብበት እላለሁ :: የበዓል ነቢያት በአንድ ወቅት ከነቢዩ ኤልያስ ጋር ፉክክር ገብተው አምላካቸውን ሊጠሩ በጣም ብዙ ደከሙ :: ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፥ ከጠዋትም እስከ ቀትር ድረስ፦ በኣል ሆይ፥ ስማን እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፥ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር በቀትርም ጊዜ ኤልያስ፦ አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል፥ ወይም ፈቀቅ ብሎአል፥ ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል እያለ አላገጠባቸው :: በታላቅም ቃል ይጮኹ፥ እንደ ልማዳቸውም ደማቸው እስኪፈስስ ድረስ ገላቸውን በካራና በቀጭኔ ይብዋጭሩ ነበር :: ቀትርም ካለፈ በኋላ መሥዋዕተ ሠርክ እስኪደርስ ትንቢት ይናገሩ ነበር፤ ድምፅም አልነበረም፥ የሚመልስና የሚያደምጥም አልነበረም ይለናል መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ  18 : 25 - 29 :: ይህን ከመሰለ ሁኔታ ለመውጣት ታድያ መጽሐፍቅዱሳችን የሚለንን መስማት አማራጭ የለውም ስለዚህ አሁንም መጽሐፍቅዱሳችን በአንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋር ተቀበልከኝ ይለናል :: እንደገናም አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው ከቤትህ በረከት እንጠግባለን በማለትም ይነግረናል ( መዝሙር 73 ፥ 24 ፤ መዝሙር 65 ፥ 4 ) ተባረኩ :: ሕዝቡም አውቀው ተከተሉት ተቀብሎአቸውም ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር መፈወስም ያስፈለጋቸውንም ፈወሳቸው ( የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 11 ) ለተጨማሪ መረጃ ው የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Thursday 30 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 1 ) የዛሬው አዲሱ ትምህርታችን በማስታወቅያው መሠረት አንድ ብሎ በክፍል ስድስት ተጀምሯል በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? 1ኛ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ 2ኛ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርታችን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ በሚለው የሰዓታት መጽሐፍ ቃል መሠረት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህናት ፣ የሰንበት ተማሪዎችና ሕዝበ ምዕመናን ጭምር ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም በማለት በመዝሙርና በአምልኮ ማርያምን ሲማጸኑና ሲጠሩ እንሰማቸዋለን :: በዚህ ትምህርት ውስጥ ግን ነይ ነይ እየተባለች የተጠራችው ማርያም በሞት የተወሰነችና ሞትም የከለከላት በመሆንዋ ልትመጣ እንደማትችል ትምህርቱ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት አብራርቷል :: ይሁን እንጂ ይህንን የቃሉን እውነት ካለመረዳት የተነሳ ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይንም ነይ ነይ እናቴ ማርያም እያሉ አሁንም የኦርቶዶክስ ካህናትም ሆነ ሕዝበ ምዕመናን በዚህችው በማርያም ፍቅር ከመያዛቸው የተነሳ ቢቀጥሉ ሳያውቁት ወደ መናፍስት ጠሪና ወደ ሙታን ሳቢ መንፈስ ውስጥ ገብተው የጠረፍዋ ንግሥት መጫወቻ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት ንጉሥ ሳኦል ሳይቀር ሕይወቱ የተጎዳው በመናፍሥት ጠሪዎች መሆኑን ትምህርቱ አሁንም ማከያ ሃሳብ ሰጥቶ በአጽንኦት ይናገራል 1ኛ ሳሙኤል 28 በሙሉ ፣ 1ኛ ዜና መዋዕል 10 ፥ 13 እና 14 ን ይመልከቱ :: የተወደዳችሁ ቅዱሳን የዚህ ክፍል ዋና ትምህርት እንግዲህ ድንግል ማርያምን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ወይንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ሲሉ በመጣራት የሚመጣውን አደጋ የጠቆመን ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውንም ዓይነት ደረጃ በደረጃ ነግሮናል 1ኛ ) በትንቢተ ኢሳይያስ 8 ፥ 19 መሠረት ከየትኛውም አቅጣጫ ጠይቁ የሚባል ነገር ሲመጣ ፣ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር መጠየቅ አለበት:: 2ኛ ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ መሄድ አለበት ( ትንቢተ ኢሳይያስ 8 : 20 - 22 ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ ስንል ፣ ጊዜ ወስዶ መጽሐፍቅዱስን ከሚያስጠኑና ከሚያስተምሩ ሰዎች በአግባቡ መማር ፣ በመጽሐፍቅዱስ ጥናቶች ሳይቀር ታማኝ ተማሪ መሆንን ያጠቃልላል :: 3ኛ ) ስንጠራው እግዚአብሔር የሚመልስልን አምላክ ነውና ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ከማለት ይልቅ እግዚአብሔርን መጣራት ዳግም ለተወለደ ለማንኛውም ክርስቲያን ድልን የሚያጎናጽፈው ነው በማለት የዛሬው ትምህርት በዚሁ ይደመደማል :: እነዚህ ጥቅሶች ለመጨረሻውና ለ3ኛው ቊጥር ማጠቃለያንና መደምደምያን የሚሰጡ ቊልፍ ሃሳቦች ስለሆኑ መጽሐፍቅዱሳችሁን በመግለጥ ጥቅሶቹን አንብቡአቸው ተባረኩ መዝሙር ( 91 ) : 15 እና 16 ፤ 2ኛ ሳሙኤል 22 ፥ 4 - ፍጻሜ ፤ 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 20 _ 46 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 6 ፥ 9 ፤የማቴዎስ ወንጌል 7 ፥ 7 _ 12 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 ፣ 14 ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Tuesday 28 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 8 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ  5 : 10 - 12 ፋሲካን የሚያከብር ሰው ከፍርድ ያመለጠ ነው :: ታድያ እሥራኤላውያን ከአንድ ዓመት በኋላ በሲና ተራራ ላይ ፋሲካን ከማክበራቸው በፊት በእግዚአብሔር ላይ አምጸው ስለነበረ ተቀጡ ዘኊልቊ 14 : 21 - 23 ፤ 29 _ 35 :: ይሁን እንጂ ከፍርድና ከኩነኔ ያመለጠ ሰው ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነው መኖር ያለበት :: ነገር ግን እሥራኤል ለእግዚአብሔር የታዘዙ ባለመሆናቸው በህይወታቸው ይሄ ሆነ :: ይህንን እውነታ ነበር አዲሱ ትውልድ በኢያሪኮ የፋሲካን በዓል ባከበረ ጊዜ ያልተገነዘበው :: ከዚህ የተነሳ ይህ አዲሱ ትውልድ ለሦስተኛ ጊዜ ፋሲካን በኢያሪኮ ሜዳ ያክብር እንጂ ለዚህ ለፋሲካው በዓል አከባበር በሕይወቱ ላይ ትርጉም መስጠት አቅቶት ነበር :: ፋሲካውንም በኢያሪኮ ሲያደርግ እንዲሁ በባህልና በቅብብሎሽ ላለመተው ሲል ብቻ አክብሮት አሳለፈው :: ይህ እንግዲህ የአዲሱ ትውልድ በራሱ ላይ ካለመጠየቅ ያመጣው የሕይወት ድክመት ነው :: ጠይቆ ቢሆን ኖሮ እውነታው ላይ በእርግጠኝነት ይደርስ ነበር :: በፋሲካ ምክንያት ከፍርድ ያመለጠ የመጀመርያውና ከግብጽም የወጣው የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ወደሚኖርበት ሕይወት መጥቶ ነበር :: ይሁን እንጂ በኢሳይያስ 1 ፥ 2 ላይ ልጆችን ወለድኩ አሳደግሁም እነርሱም አመጹብኝ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ፣ በእግዚአብሔር ላይ በማመጹ ምክንያት በምድረ በዳ ቀረ :: ጌታ እግዚአብሔር ከአመጽ ይጠብቀን :: በመሆኑም ለእግዚአብሔር ልጆች የሚበጀው መታዘዝ እንጂ ዓመጽ አይደለም :: መጽሐፍቅዱስ ትእዛዙን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና ትእዛዛቱ ከባባዶች አይደሉም ይለናል :: በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ስንሆን ትእዛዛቱን እንጠብቃለን :: ትእዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ሕይወታችንና የዘመናችንም ርዝመት ይሆናል :: እንደገናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ይወደናል ፣ ራሱንም ይገልጥልናል :: ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ደግሞ ትእዛዛቱ በእኛ ውስጥ ሊሆኑ ይገባል :: የዛሬው ትምህርት በአጭሩ የሚያስገነዝበን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው :: ለተጨማሪ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ :: ፋሲካን አስመልክቶ ከቊጥር 1 _ 8 የተሰጡ ትምህርቶች በዛሬው የመጨረሻና የማጠቃለያ መልዕክት ተጠናቋል :: ሐሙስ ዕለት ዋናው የትምህርት አርዕስቴ እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ ንዑስ ክፍልና የትምህርት ሃሳብ እቀርባለሁ:: ልባችሁን አዘጋጅታችሁና ሰፋ ብላችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ተባረኩልኝ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Sunday 26 August 2018

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ.. የንስሓ አባት መሆን ያለበት ማን ነው ? የመልዕክት ርዕስ የንስሐ አባት ኢየሱስ ወይስ ኦርቶዶክሳዊው ቄስ ? የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን አላችሁ :: የንስሐ አባቱ ኢየሱስ ወይስ የኦርቶዶክሱ ቄስ ? በሚል ርዕስ ዙርያ ያነሳናቸውን ነጥቦች እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ስናያቸው በጣም አስተማሪና ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን የምናገኝባቸው ጉዳዮች ሆነው አግኝተናቸዋል :: በመጀመርያው የጥያቄ መወያያችን ላይ ቄሶች የኢየሱስን ሥልጣነ ክህነት ለምን ይጋፋሉ ? ስንል በመጠይቅ መልክ ያነሳነው ሃሳብ ለቀሳውስቱ ምቾት ባይሰጥና ቀሳውስቱንም ሥልጣኔ ተነካ ፣ መብቴ ተደፈረ እያስባለ የሚያነጫንጫቸው ፣ የሚያተክናቸውና የሚያደብናቸው መሆኑን ብናውቅም እየተጋፉት ያሉት ፣ የማይጋፉትን ፣ ሊጋፉት ቢያስቡም እንኳ ጨርሶ ሊጋፉት የማይችሉትን እና የማይሆንላቸውን ከዚህም ሌላ በመጋፋታቸው ብዛት በራሳቸው ተጎድተው ከጥቅም ውጪ የሚሆኑበትን እውነት በመንገር ፣ የኢየሱስን የክህነት ሥልጣን ከሚጋፉበት ዓመጽ ወጥተውና አቅማቸውንም አውቀው በጨዋ ደንብ አርፈው እንዲቀመጡ ለማስገንዘብና ለመምከር ነው :: የኢየሱስን ሥልጣን በተመለከተ በተለይም የዛሬዎቹ ቀሳውስት ከእውቀት ነጻ በመሆናቸው መጽሐፍ ቅዱሱን በአግባቡ ሊያነቡት ቀርቶ የራሳቸውን የእምነት መግለጫ እንኩዋ ለማንበብ ጊዜ የሌላቸው:: በመሆኑ የእምነት መግለጫው ምን እንደሚልና በውስጡም ምን እንደተጻፈ አያውቁትም :: ምናልባትም እነዚህን ቀሳውስት እንዲህ ያባከናቸው የዝክሩና የተዝካሩ የድግሱም ብዛት ይሆናል ብዬ ገምታለሁ :: ዛሬ ግን ይህንን እውነት እኔ ወንድማቸው ላነቃቸውና ከተሳሳተው ተግባራቸውም ልመልሳቸው እናገረዋለሁ :: አመክንዮ ዘሐዋርያት የእምነት መግለጫ እንዲህ ይላል «ዘኪያሁ ይሴፈዉ ምጽአቶ ኲሎሙ አሕዛብ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሠረፀ እምይሁዳ ወእምሥርወ ዕሤይ ዘሥልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ሎቱ ስብሐት ወአኰቴት ዕበይ ወባርኮት ውዳሴ ወማኅሌት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን »ይህንን ወደ አማርኛው ስንተረጉመው «አሕዛብ ሁሉ መምጣቱን በተስፋ የሚጠባበቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ከዕሤይም ሥር የተገኘ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ የሆነ ነው ለእርሱ ምስጋና ገናንነት ክብር በረከት ውዳሴ ቃለ መዝሙርም ይገባዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን » ይለናል ::ከዚህ እንቊ ከሆነ እና መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት ሆኖም ከተጻፈ የቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫ ተነስተን ነው እንግዲህ እኔና አባታችን አባ ተክለ ማርያም የኦርቶዶክስ ቄስ ሆይ ሕዝቤን ልቀቅ ይልሃል !!እግዚአብሔር ያልነው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስን አይደለም ኦርቶዶክሳውያን አማኞች አሕዛብ ሳይቀር መምጣቱን በተስፋ የሚጠባበቁት ናቸው :: የመጣው ደግሞ ከሥልጣን ጋር ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ከሤይም ሥር የተገኘ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ የሆነ ነው ለእርሱ ምስጋና ገናንነት ክብር በረከት ውዳሴ ቃለ መዝሙርም ይገባዋል ሲል የእምነት መግለጫችን ነገረን:: ታድያ ይሄ ኢየሱስ ምስጋናና ገናናነት ሲባል ዝም ብሎ የተዘመረለት ጌታ እኮ አይደለም :: በሥልጣኑ የሠራው ትልቅ የማዳን ሥራ ስላለ ነው ውዳሴ ፣ ቃለ መዝሙርም ይገባሃል የተባለው :: በመሆኑም በሥልጣኑ ካደረገው የማዳን ሥራ አንጻር ዛሬ አይሁድ እንደሚገዘሩት እኛም እንደ አይሁድ አንገዘርም :: ለዚህም ነው ይኸው የእምነት መግለጫ ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ያለን :: ትርጉሙም እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን ማለት ነው :: አያ ቄሱ ግን ኦርቶዶክሳውያኑ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ ሆኖ ነፍሳቸውን ለማዳን የመጣላቸውን ኢየሱስን ብቻ ተስፋ እንዳያደርጉ ፣ ይሄ ኢየሱስ ኦሪትና ነቢያትን እንዳልፈጸማቸው አድርጎ በመቁጠር ፣ ወደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ተመልሶና የብሉይ ኪዳኑ የፍርባው ብዛትም ሆነ ተረፈ መስዋዕቱ ፊቱ ድቅን እያለበት ፣ ሽታውም ናላውን እያዞረው ፣ ውልም እያለው ስለተቸገረ ፣ ይህቺ ሁኔታ ደግሞ ለምዕመኑ ሳይቀር ምስጢር ሆና ለእርሱ ግን ትልቅ ጥቅም የምታስገኘው ፍርምባና ተረፈ መስዋዕት እንዳትቀርበት ፣ ኢየሱስ ሥልጣኔን እባክህ ተጋራኝ ወይንም አግዘኝ ያለው ይመስል ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ ከኢየሱስ ትከሻ ላይ ሥልጣኑን ሊያወርድ ሲጣጣር የኢየሱስንም ሥልጣን ሲጋፋ ይታያል :: ይህ ታድያ አንዳንድ ጩሉሌ የመርካቶ ኪስ አውላቂዎች በርቀት ሆነው በአንድ ሰው ላይ የሆነ ነገር ካዩ ፣ ጋሽዬ ይሄን ነገር እኮ እኔ ብይዘው ፣ ብረዳዎት እንደሚሉት ፣ ከቻሉም ደግሞ እንደ ጭልፊት ነጥቀው ለመብረር እንደሚጣደፉት ዓይነት በመሆኑ ፣ በኢየሱስ የክህነት ሥራም ላይ ያያቄሱ ድርጊት ከዚህ አይተናነስም እና እንዲሁ ነው :: እዚህ ላይ ለትምህርቴ ማጠናከርያ አንድ ምሳሌ በማከል መልዕክቴን እጠቀልላለሁ :: በአንድ መንደር ውስጥ ሕዝቡ የቅዳሜ ገበያ ሲል ከቤቱ እንደሚወጣ ያወቀች እብድ ማንም ሳይቀድማት በጠዋት ተነስታ « ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል አለች »አሉ :: መንደረተኛውም የዚህችን ዕብድ ብርቱ ማስጠንቀቅያ አላወቀም ፣ አልገባውምና ጀመራት ደግሞ ይህቺ ዕብድ ፣ ዛሬ ደግሞ ምኑን ከምን ይዛ ነው እንዲህ የሚያስለፈልፋት ? ብሎ ይህቺን ዕብድ ማንም ሰው አባከና ሳይላትና ቦታም ሳይሰጣት ሁሉም ወደ ገበያው ጥርግ ብሎ ሄደ :: ከዚያም መንገዱን እያጋመሰው እያለ ዕብዷ ሴት የእያንዳንዱን ሠፈረተኛ ሰው ቤት በእሳት ለኮሰችና እሳቱ ሲንቦገቦግና ቤታቸውን ሲያቃጥል ሠፈረተኛው ወየው ቤታችን ተቃጠለ ጉድ ሆንን ብሎና ከመንገዱም ተመልሶ ወደ ሠፈሩ ሲመለስ ይህቺ ዕብድ ጠዋት ማንም ከእንቅልፉ ሳይነሳ ትናገረው የነበረውን ቃል በመድገም «ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል » አለቻቸው ይባላል :: መልዕክቴን ስጠቀልለው እኔም ሆንኩ አባታችን አባ ተክለ ማርያም የምናስተላልፈው መልዕክት ዛሬም ይህንኑ ቃል በመድገም ነው «ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል » ተባረኩ እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ ፤ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች  5 : 13 - 15 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር አሜን

Thursday 16 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ  እግዚአብሔርን የተኩ  የአማልክት አምልኮዎች 

ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 5 )


ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ 
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ


ትርጉም  የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 )


5ኛ ) ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት ( ዘኊልቊ 9  12 ) 











ወንድማችን የጥንቱና የጠዋቱ መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው :: በመዝሙሮቹ ውስጥ ያሉት መልዕክቶች መጽሐፍቅዱሳዊና ከመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ከመሆናቸው የተነሳ ዘመናትን አቋርጠው አሁን ላይም እየተደመጡ ያሉ በመሆናቸው ትውልድን የሚመሠርቱ የሚያንጹና አቅጣጫንም ጭምር የሚያስይዙ መዝሙሮች ናቸው :: ታድያ እነዚሁ መዝሙሮች  መዝሙር ብቻ ሳይሆኑ   ስብከቶች መልዕክቶችና ትምህርቶችም ጭምር ናቸው :: በመሆኑም ዛሬ ላይ ባዘጋጀሁት ትምህርትም የወንድማችን መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ መዝሙር በእጅጉ የጠቀመኝ በመሆኑ ከትምህርቴ ጋር አያይዤ ይህን መዝሙር ለእናንተ ለአድማጮች ለመጋበዝ ወድጃለሁ እና እባካችሁ ተጋበዙልኝ ስል በፍቅር እጠይቃለሁ:: ወንድማችንንም ጌታ ይባርክህ ዕድሜና የአገልግሎት ዘመንም አብዝቶ አትረፍርፎ ይጨምርልህ በሉልኝ ተባረኩ 








በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ እግዚአብሔርን የተኩ የአማልክት አምልኮዎች 

( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 5 )


ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ 
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ


ትርጉም የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 )


5ኛ ) ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት ( ዘኊልቊ 9 12 ) 


የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ በዘኊልቊ 9 12 ላይ የተጻፈው የብሉይ ኪዳን ቃል በጥላነት የሚያመለክተን የፋሲካ በጋችን የሆነውን ኢየሱስን ነው ( የዮሐንስ ወንጌል 1 29 )::  ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ይለናል  ( 1 ቆሮንቶስ 5 7 እና 8 ) ::

እንደገናም በዘኊልቊ 9 12 መሠረት ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ :: ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ:: እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት የሚለው ቃል በዮሐንስ ወንጌል 19 36 እና 37 ለተጻፈው ቃል አሁንም በጥላነት የሚያገለግል ነው :: ቃሉም እንዲህ ይላል :: ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው :: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይለናል :: ይህ የሚያሳየን ታድያ ጌታ እኛን ከመውደዱና ለእኛም መሥዋዕት በመሆኑ  ምክንያት በኤፌሶን 5 2 ላይ በተጻፈው ቃል መሠረት ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ በፍቅር ተመላለሱ የሚለውን ቃል ያስጨብጠናል ::  ታድያ ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ምልልሳችንን ሳይቀር ለውጦ የፍቅር ምልልስ አደረገው :: ከዚህም ሌላ እኛም እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ተብለናልና በእግዚአብሔር በአምላካችን እንደተወደድን ገብቶን እግዚአብሔርን የምንከተል ሆንን :: ለዚህ ሁሉ ክብር የበቃንበት ምስጢር ግን  ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ነው :: 

ሌላኛውና ሁለተኛው ሃሳብ አሁንም  በዘኊልቊ 9 12 በተጻፈው ሃሳብ መሠረት እስከ ነገ ድረስ ከእርሱ ምንም ካላስቀሩ ከእኛም ምንም መቅረት የለበትም የሚለውን ሃሳብ እንድንይዝ ቃሉ ያስገነዝበናል :: ይህ ማለት ደግሞ እኛም ፈጽመን ወይንም ጨርሰን መለወጥ እንዳለብን የሚጠቁመን ቃል ነው :: 

በዘጸአት 12 14 እና 15 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን :: ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።

እርሾን በተመለከተ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ እርሾ በመጽሐፉ ቃል መሠረት ያልተፈለገ በመሆኑ ለብሉይ ኪዳኑ እሥራኤል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ የሚል ትዕዛዝ ተላለፈ :: ይህንን እውነታ አሁንም ወደ ሐዲስኪዳኑ ሕይወት ስናመጣው ፣ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም የሚለውን እውነተኛውን ትምህርታዊ የሆነ የሕይወት መርሆና ትርጉምን ይሰጠናል :: ዛሬ ታድያ ክርስቶስን ባመኑ ፣ በሚያገለግሉም ክርስቲያኖችና አገልጋዮች ሳይቀር  ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶ ሳለ በእነዚሁ ወገኖች ሕይወት ላይ ግን   ክፉ የሆነ አሮጌ  የግፍ ፣ የቅንዓት የክፋትና የዓመጸኝነት…. እርሾ አለ :: እንደገናም በእውነትና በቅንነት ቂጣ በዓልን ማድረግ የለም :: 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ፣ ደቀመዛሙርቱን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንዲጠበቁ አስጠነቀቀ ( የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 6 ፤ 12 ):: ለዚህም ነው ጳውሎስ በዘመናችን  ላለን  ጤናማ ክርስቲያኖች ጭምር መልዕክት ስለነበረው ፣ የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኛለሁና የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ፍርዱን ሊሸከም ነው በማለት የነገረን ( ገላትያ 5 ፥ 9 ) ::

በክቡር በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጀ ያወቀ ሰው በሕይወቱ እርሾ እንዲኖርበት አይፈቅድም ፣ መፍቀድም የለበትም ( ዘዳግም 16 ፥ 3 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 19 ) 

ከዚህ በመቀጠል ለዚህ ትምህርት ማጽኛ እንዲሆን ፣ ጌታ በሌሊት ከመኝታዬ ቀስቅሶ የተናገረኝን ቃል እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ ::


ለቤተክርስቲያንና ለቅዱሳን ዕድገት እንዲሁም የሕይወት ከፍታ አስቸጋሪ የሆኑ ፣ ለዘመናት አልለወጥ ብለው በቤቱ እንደ ጉቶ ተተክለው ለቀሩ ክርስቲያኖች ፣

1ኛ ) በግድ በመከራና በጣር እንደሚለወጡ ጌታ ይናገራል ( ዘፍጥረት 32 ፥ 22 _ ፍጻሜ ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 31 ፥ 18 _ 20 )::

2ኛ ) በበቃኝ እና በልመለስ እንደሚለወጡም  ጌታ ይናገራል ( የሉቃስ ወንጌል 15 ፥ 11 _ ፍጻሜ ፤ ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 በሙሉ )::

በመቀጠልም የተባረከው የጥንቱና የጠዋቱ ዘማሪ የሆነው መጋቢ ታምራት ኃይሌ ፦


በእንባና በጣር በጭንቅ በመከራ 

በእሳት ውስጥ አልፎ ሕይወቴ ተገራ 

ማዕበሉም ነፋሱም ሰራኝ ደህና አድርጎ 

ጠላት ለክፉ ሲል ሆነልኝ ለበጎ………. የሚለውን 

መዝሙር ከትምህርቴ ጋር ስለሚሄድ እርሱን በመጋበዝ 

የቊጥር 5 ትምህርቴን አጠቃልላለሁ ተባረኩ 





ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ 

አገልግሎት


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው