Wednesday 19 December 2018

December 18, 2018 በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 12 ) አለማፈርስ ያለው ማንን በማመን ነው ? ማርያምን ወይስ ኢየሱስን ? ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርም የሚለውንና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤቴ ሆይ ከአንቺ ዘንድ ሽቶ የወደደውን ሁሉ ያላገኘ ማነው? በአንቺ አምኖ ያፈረ ማነው ? አንቺን ለምኖ ወደ ገሃነም ያወረድሽው ማነው ? ወደ ሠርግ ቤት ማለት ወደ መንግሥተ ሰማይ አገባሽው እንጂ የሚለውን በ2007 እትም ተአምር 41 : 25 እና በተአምር 43 : 23 - 25 ማግኘትም እንችላለን :: የተአምረ ማርያም መጽሐፍ በተለያየ ዓመተ ምሕረት የተጻፈ በመሆኑ እንደየ ዓመተ ምሕረቶቹ ምዕራፎቹና ቁጥሮቹ ይለያያሉ ተባረኩ በባለፈው ትምህርታችን ላይ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ ርኢክሙኑ ኦ አኃው "እስመ ኩሉ ዘረሰየ ትውክልቶ ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ ወላዲቱ ኢይትኀፈር " ወደ አማርኛው ሲተረጐም :--- ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ብሎን ነበር ( ተአምር 31 : 25 ) እምነታችን የመጣው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ስለሆነ የማናፍረው እምነታችንን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ አድርገን ሳይሆን በትንቢተ ኢሳይያስ  28 ፥ 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም ይላልና የማዕዘኑን ድንጋይ የሆነውን ኢየሱስን አምነን ነው ዛሬ ደግሞ በተአምር 33 ፥ 23 - 25 ላይ ኦ እግዝእትየ ቅድስት ድንግል በ፪ ማርያም መኑ ዘኀሠሠ እምኔኪ ወኢረከበ ኮሎ ዘፈቀደ ወመኑ ዘተወከለ ኪያኪ ወተኀፍረ ወመኑ ዘጸውአ ኀቤኪ ወሰደድኪዮ አፍኣ ዘእንበለ ዘአባእኪዮ ውስተ ቤተ መርዓ ይለናል ወደ አማርኛው ስተረጉመው በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤቴ ሆይ ከአንቺ ዘንድ ሽቶ የወደደውን ሁሉ ያላገኘ ማነው? በአንቺ አምኖ ያፈረ ማነው ? አንቺን ለምኖ ወደ ገሃነም ያወረድሽው ማነው ? ወደ ሠርግ ቤት ማለት ወደ መንግሥተ ሰማይ አገባሽው እንጂ በማለት ይህንን ቃለ ተናገረ ይህ ማለት ታድያ ሰዎች ከማርያም እንዳይሄዱና እንዲታዘዙላት ፣ እንዲያመልኩዋት ፣ እንዲሰግዱላትና እንዲገዙላት ስለ ራሷም ታላቅነት ጭምር እንዲናገሩ ነው ይህ የስሕተት መጽሐፍ የሚያስተምረው በዚህም ምክንያት እንግዲህ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ ደፍሮ ማርያም ማለት መንግስተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው አለን ( የዘወትር መቅ፡ቁጥር፡ 5 ) እመቤታችንን የቤተክርስቲያን ልጆች አክብሩዋት ለእናንተ ለኃጥአን መድኃኒት ስለሆነች ሳትጠራጠሩ በፍጹም ልባችሁ እመኑባት እርስዋ መድኃኒታችሁ ናትና አለን ( የዘወትር መቅ፡ቁ፡ 34 ) የካቲት 16ቀን አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበት የጻድቃን ማረፊያቸው ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ሰማይ አሳረጉዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያው ድረስ ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ሁሉ ተቀበሉዋት ከአጽማችን አንችን አጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግ/ር ምስጋና ይግባው እያሉም ሰገዱላት ባንቺ ደህንነትን አገኘን የአምላካችን ልጅ ካንቺ ተወለደ ከጥፋት የሕይወት ወደብ የሆንሽን እያሉም ሰገዱላት አለን (12ኛ ተአምር ቁ፡12 - 13) እመቤታችንን የዓለም ሁሉ መድኃኒት አድርጎ እንደፈጠራት ልብ አድርጋችሁ እነሆ እወቁ አለን (12ኛ ተአምር ቁ፡ 62) ልመናንና አምልኮንም በተመለከተ ደግሞ አንቺ ከሰማያውያን መላእክት ልዕልት እንደሆንሽ ከመሬታውያን ጻድቃንም የከበርሽ እንደሆንሽ ያውቁ ዘንድ ይደረግልኛል ብሎ አምኖ አንቺን በእኔ ስም የለመነ ሰው ቢኖር ከሰማዕታት አንዱም ቢሆን ከቅዱሳንም ወገን ቢሆን የፈለገው ይደረግለታል (18ኛ ተአምር ቁ፡30_31) እንደኔ ያላችሁ ወንድሞቼ ሆይ ከእንግዲህ ወዲህ 16ቱን ሕግጋት ለመፈጸም የእግ/ር ባሮች ለመሆን አንሻ እሱ በቀትር ግዜ በመስቀል ላይ እመቤታችሁ እናታችሁ እነሆ እያለ የቃል ኪዳን እመቤት እሷን ሰጥቶናል ስለዚህ የእናታችን የድንግል ማርያም ባሮች ለመሆን ፈጽመን እንሽቀዳደም ብዬ እነግራችሁዋለሁ። (12ኛ ተአምር ቁ፡ 52_53) ከነዚህ ሃሳቦቹ የተነሳ ይሄ የተአምረ ማርያም ጸሐፊ እግዚአብሔር የለም ኢየሱስም ለእኛ አልሞተልንም እያለን ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚነግረን ግን 1ኛ ) አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ( 1ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 5 ) 2ኛ ) ወደ እግዚአብሔር የቀረብነው ፣ ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ ? ያልነው በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ግልጽ አድርጎ ነግሮናል ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም ( 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት  3 : 18 - 20 ) ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ ? የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው ፤ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ( 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች  15 : 55 - 57 ) 3ኛ ) በዚህም ምክንያት የምንንበረከከውም ሆነ የምንገዛው ለእግዚአብሔር አብ ክብር እየሰጠን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በመንበርከክ ብቻ ነው በመዝሙር 95 : 6 ላይ ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ ይለናል በመዝሙር 100 : 4 ላይ ደግሞ ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ በማለት ይነግረናል እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ይለናልና ( ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች  2 : 6 - 11 ) ታድያ ከዚህ ከተባረከው የእግዚአብሔር እውነት አንጻር የተአምረ ማርያምን መጽሐፍም ሆነ ጸሐፊውን ፦—————————— በማቴዎስ ወንጌል 4 : 10 በተጻፈው ቃል መሠረት ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና በማለት ገስጾ አባሮታልና እኛም እንዲሁ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ስንል እናባርረዋለን ደግሞም እናስወግደዋለን 4ኛ ) መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው ስለዚህ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ( የሐዋርያት ሥራ  4 : 12 ) እንደገናም ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎናል ( የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 ) በዕብራውያን 7 ፥ 24 ላይ ደግሞ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ይለናል 5ኛ ) ትዕዛዛትንም በተመለከተ እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ የማቴዎስ ወንጌል 5 : 18 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል የማቴዎስ ወንጌል 5 : 19 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም የዮሐንስ ወንጌል 14 : 24 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment