Saturday 27 October 2018

አጠር ያለ የግጥም መነባንብ :- የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የተክለ ሃይማኖት ወዮታ የገድሉን ሐሰተኝነት በሚያጋልጥ መልኩ ከተክለሐይማኖት ገድል ተውጣጥቶ እና በወንጌሉ እውነት ተቃኝቶ የቀረበ የግጥም መነባንብ መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንልዎት!!! ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ ለሰዎች ብርሃን ያበራሁኝ መስሎኝ በጨለማ ኖሬ ለራሴ ጨለምኩኝ ከንቱ ግብዝነት ይዞኝ ስንቀባረር ክህነቴን በሰማይ አድርጌው ለመኖር ክንፎችን ገጥሜ በግራና በቀኝ የሰማይ ካህን ነው ራሴን አስባልኩኝ ነገር ግን ክንፎቹ የውሸት ነበሩ ለይምሰል ተስለው ተሰክተው የቀሩ እንደ ዶሮ ላባ ድንገት ሲነቀሉ በወንጌሉ እውነት ዳግም ላያበቅሉ እኔም ተሳቅቄ ወዮልኝም አልኩኝ ሥራዬን ገልጠውት ከሹመት ሲሽሩኝ የሰዎችን ኃጢአት ይቅርም ለማስባል የሚንበረከክ ነው ሲጸልይ የሚውል ማንም ያልሰራውን ሰርተኸዋል ሲሉኝ ተብዬ ስወደስ ሰዎች ሲያሞካሹኝ በጌቴሴማኒ የተንበረከከው ሥርየት ለማሰጠት ደሙን ያፈሰሰው ደም ሳይፈስ ሥርየት ፍጹም አይገኝም በመንበርከክ ጸሎት ማንም አያመጣም ብሎ ተናገረኝ ውሸታም ነህ ብሎ ሥራዬን አጋልጦ ተንኮሌን ፈንቅሎ ላሞች ባልዋሉበት የኩበት ለቀማ ራሴን ሰቅዬ በጸሎቱ ማማ እግሬ የተቆረጠው ስጸልይ ነው አልኩኝ በገድል በድርሣኑ ራሴን ከመርኩኝ እውነቱ ሲነገር ታሪክ ሌላ ሆነ እኔም ተጋለጥኩኝ ስሜም ተኮነነ መንግሥትን ከላስታ ወደ ሸዋ ምድር ለማዞር ፈልጌ ስዶልት ስመክር ገድለህ ንገሥ ብዬ ንጉሡን ሳሳብር የዶሮውን ጩኸት ትርጉሙን አውቃለሁ እያልኩ ስቀሰቅስ ሳዳምቅ እያለሁ ድንገት በጦርነት እግሬ ተሰበረ የጸሎት ሰው ሲሉኝ ስሜም የከበረ ዛሬስ ተዋረድኩኝ ገበናዬም ወጣ ብዬ አለቀስኩኝ ባመጣሁት ጣጣ የመጨረሻዬ የተቅማጥ በሽታ የመጨረሻዬ የወባ በሽታ ከዚህ ምድር ይዞኝ ሊወስደኝ በአንድ አፍታ እስቲ ስሜን ላድስ በፍጻሜው ሰዓት በዚህ በተቅማጡ ከመሞቴ በፊት ብዬ አሰብኩና ኪዳኑን በሰማይ ከኢየሱስ ደም ጋራ ላያይዘው በላይ መዋሸት ጀመርኩኝ ዳግመኛ ሳላፍር እንደ ስቅለቱ ደም ተቅማጤን ላስቆጥር በገዳም የሞተ በወባ በሽታ ይድናል አይጠፋም ይኖራል በደስታ በመላዕክት ዓለም በሆታ በእልልታ በመንግሥተ ሰማይ በላይኛው ጌታ ነገር ግን አንዳንዱ አቃሎት ነገሬን ከሰማኝ በኋላ የባልቴት ተረቴን በያደባባዩ ደግሞ ሊያሳፍረኝ መደበቅያ ሥፍራ ቦታም አሳጥቶኝ በወንጌሉ እውነት በርብሮ ገለጠኝ የመቀበርያዬም ጊዜያቱ ደረሰ ሳልፈልገው በግድ ጉድጓዴ ተማሰ እኔም ከዚህ ወዲያ ይበቃኛል አልኩኝ ዳግም ላልተነፍስ መቃብር ወረድኩኝ እፎይ ያለው ትውልድ ይኸው ተቀስቅሶአል የወንጌል ደመራው ችቦው ተለኩሶአል ጆሮ ያለው ይስማ ኢየሱስ ያድናል ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ለግጥሞቹ የተጠቀምኩበት መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው ያንብቡአቸው ዕብራውያን 12 ፥ 24 , ቅዳሴ ሐዋርያት ገጽ 122 ፥ 106 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 214 , የተክለ ሐይማኖት ስብሐተ ፍቁር ገጽ 2116 , ዕብራውያን 10 ፥ 29 - 31 , በ13ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በላስታ ያለውን የዛጉዬን መንግሥት ወደ ሸዋ ለመመለስ ባካሄደው መፈንቅለ መንግሥት , ገድለተክለሐይማኖት ምዕራፍ 27 ፥ 15 ፣ 17 , 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 7 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 , ኅዳር 24 ፥ ገጽ 78 , ዕብራውያን 9 ፥ 22 ፣ ኤፌሶን 1 ፥ 7 ፣ ሮሜ 5 ፥ 6 _ 10 , ገድለ ተክለሐይማኖት ምዕራፍ 57 , ገድለ ተክለሐይማኖት ትንሣኤ የመጻሕፍት አሳታሚ ድርጅት ሦስተኛ እትም 1973 የታተመ ምዕራፍ 56 ቊጥር 1 - 3 ገጽ 175 ,

No comments:

Post a Comment