Thursday 13 December 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 11 ) ማንን ነው ማመን ያለብን ? በማን ስንታመንና ማንንስ ስናምን ነው የማናፍረው ? ጉደኛውና ተረተኛው የተምረ ማርያም መጽሐፍ ርኢክሙኑ ኦ አኃው "እስመ ኩሉ ዘረሰየ ትውክልቶ ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ ወላዲቱ ኢይትኀፈር " ወደ አማርኛው ሲተረጐም :--- ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ይለናል ( ተአምር 31 : 25 ) 1ኛ ) ማንን ነው ማመን ያለብን ? ለሚለው ጥያቄ ሀ ) መጽሐፍቅዱሳችን በእግዚአብሔር እመኑ ነው የሚለን ማልደውም ተነሡ፥ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፦ ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 : 20 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል የማርቆስ ወንጌል  11 : 22 - 23 ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ የዮሐንስ ወንጌል  14 : 1 - 3 ወንድሞች ሆይ አወቃችሁን እምነቱን በእናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ግን አላለንም ይህንን ያለን የተአምረ ማርያም መጽሐፍ ነው ለ ) እምነታችን የመጣው ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ስለሆነ እንዲሁ ዝም ብለን እንደ ደራሽ ውሃ ያመነው ወይም የምናምነው እምነት የለም ስለዚህ ፦———————— እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ይለናል ሮሜ 10 : 17 ሐ ) የአብርሃም እምነት በእግዚአብሔር ቃል የሆነ እምነት ነበር እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ኦሪት ዘፍጥረት  15 : 4 - 6 ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው ሮሜ   4 : 22 - 25 2ኛ )በማን ስንታመንና ማንንስ ስናምን ነው የማናፍረው ? ከዚህ ከተቆጠረልን ከእምነት የሆነ ጽድቅ የተነሳ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ነው የተባልነው :: ያም ያመነው ፣ ያላመንበት ብንኖር ደግሞ በእርሱ ብናምን የማናፍርበት ፣ የተመረጠና የከበረ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ነው ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም ትንቢተ ኢሳይያስ  28 :16 በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት  2 : 6 - 8 እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ ሮሜ 9 : 30 - 33 ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና ሮሜ 10 : 8 - 11 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

No comments:

Post a Comment