Tuesday 28 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 8 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ  5 : 10 - 12 ፋሲካን የሚያከብር ሰው ከፍርድ ያመለጠ ነው :: ታድያ እሥራኤላውያን ከአንድ ዓመት በኋላ በሲና ተራራ ላይ ፋሲካን ከማክበራቸው በፊት በእግዚአብሔር ላይ አምጸው ስለነበረ ተቀጡ ዘኊልቊ 14 : 21 - 23 ፤ 29 _ 35 :: ይሁን እንጂ ከፍርድና ከኩነኔ ያመለጠ ሰው ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነው መኖር ያለበት :: ነገር ግን እሥራኤል ለእግዚአብሔር የታዘዙ ባለመሆናቸው በህይወታቸው ይሄ ሆነ :: ይህንን እውነታ ነበር አዲሱ ትውልድ በኢያሪኮ የፋሲካን በዓል ባከበረ ጊዜ ያልተገነዘበው :: ከዚህ የተነሳ ይህ አዲሱ ትውልድ ለሦስተኛ ጊዜ ፋሲካን በኢያሪኮ ሜዳ ያክብር እንጂ ለዚህ ለፋሲካው በዓል አከባበር በሕይወቱ ላይ ትርጉም መስጠት አቅቶት ነበር :: ፋሲካውንም በኢያሪኮ ሲያደርግ እንዲሁ በባህልና በቅብብሎሽ ላለመተው ሲል ብቻ አክብሮት አሳለፈው :: ይህ እንግዲህ የአዲሱ ትውልድ በራሱ ላይ ካለመጠየቅ ያመጣው የሕይወት ድክመት ነው :: ጠይቆ ቢሆን ኖሮ እውነታው ላይ በእርግጠኝነት ይደርስ ነበር :: በፋሲካ ምክንያት ከፍርድ ያመለጠ የመጀመርያውና ከግብጽም የወጣው የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ወደሚኖርበት ሕይወት መጥቶ ነበር :: ይሁን እንጂ በኢሳይያስ 1 ፥ 2 ላይ ልጆችን ወለድኩ አሳደግሁም እነርሱም አመጹብኝ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ፣ በእግዚአብሔር ላይ በማመጹ ምክንያት በምድረ በዳ ቀረ :: ጌታ እግዚአብሔር ከአመጽ ይጠብቀን :: በመሆኑም ለእግዚአብሔር ልጆች የሚበጀው መታዘዝ እንጂ ዓመጽ አይደለም :: መጽሐፍቅዱስ ትእዛዙን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና ትእዛዛቱ ከባባዶች አይደሉም ይለናል :: በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ስንሆን ትእዛዛቱን እንጠብቃለን :: ትእዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ሕይወታችንና የዘመናችንም ርዝመት ይሆናል :: እንደገናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ይወደናል ፣ ራሱንም ይገልጥልናል :: ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ደግሞ ትእዛዛቱ በእኛ ውስጥ ሊሆኑ ይገባል :: የዛሬው ትምህርት በአጭሩ የሚያስገነዝበን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው :: ለተጨማሪ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ :: ፋሲካን አስመልክቶ ከቊጥር 1 _ 8 የተሰጡ ትምህርቶች በዛሬው የመጨረሻና የማጠቃለያ መልዕክት ተጠናቋል :: ሐሙስ ዕለት ዋናው የትምህርት አርዕስቴ እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ ንዑስ ክፍልና የትምህርት ሃሳብ እቀርባለሁ:: ልባችሁን አዘጋጅታችሁና ሰፋ ብላችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ተባረኩልኝ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

No comments:

Post a Comment