Sunday 9 February 2020




በአምላካችን በእግዚአብሔር/በአላህ እንደምናቹህ የሀገሬ ህዝቦች እንኳን ለብርሀነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳቹህ፡፡
በዛሬው ዕለት አንድ ብዙ ሰውን አየበጠበጠ እና እያስቸገረ ያለ ነገር አለ እሱም ምንድነው ተቀምቶ መሰረቅን ተጠንቅቀን እራሳችንን ልናድን እንችላለን ነገር ግን አፍዝዝ አደንግዝ ይዘው የሰውን ልብ እያፈዘዙ የሚሰርቁ ሰዎች በዝተዋል ዕቃ ብቻ አይደለም እየወሰዱ ያሉት አሁን አሁን የሴት እህቶቻችን ክብርም በዚህ እየወሰዱ ከሀጥያትም ሀጥያት እየሰሩ ሰውን እያሰሩ ይገኛሉ፡፡
እስኪ ወደ መፍትሔው ከመሄዴ በፊት ስለ አፍዝ አደንግዝ አስማት በመጠኑ ልንገራቹህ ፡ -
የአፍዝዝ አደንግዝ አስማት የሚሰራው ብዙን ጊዜ የሰውን ልብ የመስረቅ ሀይል ያላቸውን ዛር በመዋረስ ነው ፡፡ በብዙ አይነት መልኩ ይዋረሱታል ፡፡የሚገርማቹህ በአብዛኛው ዕፅዋት መልካም ናቸው አንዳንድ ዕፅዋት ግን ዛር ሊያድርባቸው ይችላል ፡፡ እናም አንዳንድ ዕፅዋቶች የዚህ የሚያፈዙ ዛሮች ያደሩባቸው አሉ እና ሲዋረሱት ዶሮ ያርዱለታል አረቄ ይቀቡታል 7 ቀን ወይም 40 ቀን ልክ እንደፈጣሪያቸው ይሰግዱለታል ከዛ በኋላ ያዛር ለዚ ሰው የማፍዘዝ ስልጣን ይሰጠዋል ሰወችንም ያፈዝለታል፡፡ ሌላ ደግሞ የተለያዩ የዛር ህቡዕ ስሞችን እየጠሩ ለወንዝ ሰግደው ስሙን ተዋርሰው ሰው የሚያፈዙም አሉ፡፡
ባጠቃላይ ሌቦች የሚሰሩት አፍዝዝ አደንግዝ ባብዛኛው እንደዚህ ከጥበብ የወጣ ነው፡፡
ታዲያ ወደመፍትሔው ስመጣ ከዚህ ምስሉ ላይ የምታዩትን ጥበብ ከብራና የሰለሞን መፅሐፍ ላይ ነው ያገኘሁት እና ጥበቡ ምንድነው አሰራሩ ፡ -
1፡ ድጋሙን በቀጭን ሸንበቆ(ቀስም) ፳፩(21) ጊዜ ደግማቹህ በጥቁር ሐር ጠምጥማቹህ በኪስ መያዝ ነው፡፡ከዛ በየ 7 ቀኑ በቃል መድገም ነው፡፡
2 ፡ ድጋሙን በዕለት በዕለት 7 7 ጊዜ ብትደግሙትም ሌባ አፍዝዞ አይሰርቃችሁም፡፡እርግጠኛ ነኝ፡፡
3 ፡ ድንገት ሌባ ሌላ ሰው አፍዝዞ ሲሰርቅ ካያቹህ ሄዳቹህ በቀኝ ጎኑ ቁማቹህ 3 ጊዜ ብትደግሙት ሌባው ያፈዘዘው ሰው ይነቃል ከመሰረቅ አዳናችሁት ማለት ነው፡፡ ይህንን ራሴም ሞክሬዋለው፡፡
በየትኘውም እምነት ያላቹህ ሰዎች ወንዶችም ሴቶችም ይህንን መጠቀም ትችላላቹህ፡፡
ጥበቡ ጉዳት የለውም ምንም አይነት የውርሻ ቃል የለውም፡፡
በሸንበቆ የምትሰሩት ከሆነ ግን በየ 41 ቀን በእሳት ሸንበቆውን ለብልበው ጥበቡ በእጥፍ ይታደሳል ይለዋል፡፡










Image may contain: text

No comments:

Post a Comment