Sunday 9 February 2020


ማለት ነው፡፡ መስተፋቅር በሁለት አይነት መንገድ ይከፈላል፡፡
ማለትም በነጭ አስማት የሚሰራና በጥቁር አስማት የሚሰራ
እያንዳንዳቸውን እንደሚከተለው እዘረዝራቸዋለው፡፡
እንግዲህ በነጭ አስማት የሚሰሩት መስተፋቅሮች
የእግዚአብሔርን ብቻ ህቡዕ ስሞች በመጥራት ወይም የአንዳንድ
ቅዱሳን መላእክትን ስም በመጥራት የማፋቀር ሀይል አላቸው
ተብለው የሚታመንባቸው ስሞች በመጥራትና በመጠልሰም
ይሰራል፡፡ ታድያ ነጭ አስማት ውስጥ ከሚመደቡት መስተፋቅሮች
መካከል የሚከተሉት ናቸው፡
 የማይስማሙ ባለትዳሮችን ለማስማማት የሚሰራ
(በጠልሰም፣በዕጽ፣በድጋም)
ፍቅር አሊዘው ላለ ሰው ማፍቀር እንዲችል ተፅፎ የሚሰጥ
በእድሜ በጣም የተራራቁ ሰዎች ሲጋቡ ለማዋደድ የሚሰጥ
ሚስት ወይም ባል ሲሄድ ለመመለስ የሚሰራ(እግረ መልስ፣
በወዝ)
ለማይስማማ ቤተሰብ ወይም ለቤተሰባዊ ፍቅር የሚሰራ
(በድጋም፣በጥምቀት)
ከሁሉም ተግባብቶ ለመኖር የሚረዳ( በጽሑፍ
የሚሰጥ፣በድጋም ወዘተ )
የነጭ አስማት መስተፋቅሮች እንግዲህ እነዚህና እነዚህን
የመሳሰሉ ናቸው፡፡
በጥቁር አስማት የሚሰሩ የመስተፋቅር አስማቶች አሰራራቸው
ያው ከርኩስ መንፈስ ጋር የተገናኘ ነው ማለትም መስተፋቅሩ
የሚሰራ የአጋንንት ወይም የዛር ወይም የሣጥናኤልን አስማቶች
በመድገም ርኩስ መንፈሱ ከተሳበ በኋላ የማን ስም እንደሆኑ
የማይታወቁ ስሞችን በመጥራት የሚሰራ ነው በጥቁር አስማት
የሚሰሩ መስተፋቅሮች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡
አንድን ሴት እቤት ድረስ መጥታ ተራክቦ እንድታረግ
የሚያረግ( በግብር)
በግራ እጅ ሰላም ያለው ሁሉ ተከትላው እንድትሄድ የሚሰራ
(በንቅሳት)
በስራ ቦታ በትራንስፖርት በትምህርት ቤት እንዲፈቀር
የሚያደርግ በአዩት ሁሉ እንዲወደድ የሚሰራ(በመቀባት፣በሽቶ )
ለዝሙት ስራ በተለይ ብዙ ሴቶችን ለመሳብና ለመሰብሰብ
የሚሰራ( በመፋቂያ፣በወርቅ ጥርስ ተደግሞ የሚሰጥ ወይም
በወርቅ ቀለበት የሚሰራ )፡፡
አንደን ሴት በፍቅር ለማሳበድ የሚሰራ( በሎሚ ተደግሞ
ወርውሮ በመምታት ወይም ውሀውን ተቀብቶ ሰላም በማለት)
የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
ታዲያ ምንዋጋ አለው የጥቁር አስማት ነገር ቤተክርስቲያን
በምትሄድና ከልብ አማኝ በሆነች ሴት ላይ በጭራሽ አይሰራም ይሄ
ማንም የማይክደው እውነት ነው፡፡
የብዙዎቻቹህ የመስተፋቅር ጥያቄዎች በጥቁሩ አስማት ላይ
ወደዘረዘርኳቸው ያደላሉ፡፡
ስለዚህ በኮሜንት ላይ ስለመስተፋቅር ያላችሁን አስተያየት
እንወያይ

No comments:

Post a Comment